EFFSAA Official

@effsaaofficial


A National Association of Professional Logisticians www.effsaa.org Contact us via [email protected] or +251 903 182525

EFFSAA Official

22 Oct, 13:15


#CapitalNews EFFSAA receives approval for FIATA Advanced Training Program to boost logistics sector skills

The International Federation of Freight Forwarders Associations (FIATA), a global logistics association, has given the Ethiopian Freight Forwarder and Shipping Agents Association (EFFSAA), the industry’s lobbying body, the go-ahead to offer internationally accepted advanced training in the logistics field.

It has been said that having skilled labor on hand will encourage potential investors, especially those from abroad, to make investments in the nation as it is one of the most important components.

Read More

Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube

EFFSAA Official

19 Oct, 09:47


ማኅበራችን የአገራችንን የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመወከል በብሪክስ አባል አገራት የቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳትፏል፡፡

ጥቅምት 07-08/2017 ዓ.ም በሩስያ፣ ሞስኮ በተደረገው የብሪክስ አባል አገራት የቢዝነስ ፎረም ላይ ማኅበራችን በፕሬዚደንቱ አማካኝነት በመወከል ተሳትፏል፡፡

የአገራችንን የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመወከል በመንግሥት የተመረጡት የማኅበራችን ፕሬዚደንት አቶ ዳዊት ውብሸት የብሪክስ ቢዝነስ ምክር ቤት (BRICS Business Council) ውስጥ አባል ከሆኑ ከሌሎች 8 አገራት ተወካዮች ጋር በመካተት የምክርቤቱ የቦርድ አባል ሲሆኑ ይህ ምክር ቤትም በብሪክስ አባል አገራት መካከል የሚታዩትን ችግሮች በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦችን የሚያቀርብ ነው፡፡ ም/ቤቱ በአባል አገራት የንግዱ ማኅበረሠብ ውስጥ ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች ተጠቅሞ የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ፣ ማጠናከር እና የብሪክስ አባላትን በሎጂስቲክስ ማስተሳሰር ዋነኛ ዓላማው ነው፡፡

በዚሁ መሠረትም አቶ ዳዊት ለፎረሙ ተሳታፊዎች ስለኢትዮጵያ የንግድ፣ የሎጂስቲክስ እና የኢንቨስትመንት ሁኔታ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በፓነል ውይይት ላይም ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የቀረቡት ሪፖርቶች ከጥቅምት 12-14/2017 ዓ.ም ካዛን፣ሩሲያ በሚደረገውና የየአገራቱ መሪዎች በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የሚፀድቁ ይሆናል፡፡

ቀዳሚዎቹ የብሪክስ አባል አገራት ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ እ.ኤ.አ ከኦገስት 2023 ጀምሮ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአባልነት መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡

EFFSAA Official

15 Oct, 09:51


https://capitalethiopia.com/2024/10/14/ethiopia-to-host-2027-fiata-world-congress/

EFFSAA Official

15 Oct, 09:45


https://capitalethiopia.com/2024/10/14/logistics-firms-urge-government-to-implement-incentives-ahead-of-full-liberalization/

EFFSAA Official

14 Oct, 07:48


https://www.ethiopianreporter.com/134261/

EFFSAA Official

11 Oct, 11:28


ጥቅምት 1፣2017

በሎጀስቲክስ ማቀላጠፍ ስራ ለተሰማሩ ኢንቨስተሮች የሚደረገው ድጋፍ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ተነገረ፡፡

የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ አለሙ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሀገሪቱ የወጪና ገቢ እቃ በሚገባ እንዲንቀሳቀስ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

ነገር ግን ለዘርፉ መንግስት የሚሰጠው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን አቶ አንተነህ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወቅት ቀይ ባህር አካባቢ ያለው ውጥረት በስራችን ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ቢሆንም አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ስራዎች እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን፤ ማህበሩ በተለያዩ ጊዜ ለመንግስት ጥናቶችን በግሉ በማድረግ የሚታዩ ችግሮችን እየተናገረ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለማድረግ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡

በሎጀስቲክስ ማቀላጠፍ ዘርፍ ላይ የተሰማራው ባለሃብት በቁጥር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አንተነህ የሚሰጠው ማበረታቻም ዝቅተኛ ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

በዚህ ሰዓት የሎጀስቲክስ ስራውን በሚገባ ለመምራትና ገቢና ወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ እንዲረዳ እንደ ሀገር የተሽከርካሪ ኢንቨስትመንት ያስፈልገናል በማለት አሳስበዋል፡፡

የሎጂስቲክስ ዘርፍ ሰፊ የመሬት አቅርቦትና ማሽነሪ መጠቀም የሚፈልግ ዘርፍ ነው ይህንና ሌሎችም በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶች በጋራ ተነጋግሮ መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/mr9d24nf

በረከት አካሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የኢትዮጵያ_የዕቃ_አስተላላፊዎችና_የመርከብ_ወኪሎች_ማህበር #ቀይ_ባህር

EFFSAA Official

11 Oct, 11:01


የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር፤ መንግስት የሎጀስቲክ ዘርፍን “ለጊዜው”  ለውጭ ባለሃብቶች “ክፍት እንዳያደርግ” ጠየቀ። ማህበሩ ይህን ጥያቄ ለመንግስት ማቅረቡን ያስታወቀው፤ ትላንት ሐሙስ መስከረም 30 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው።

ለጋዜጠኞች መግለጫውን የሰጡት የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ውብሸት፤ ኢትዮጵያ ከ3 አመት በኋላ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን የሎጀስቲክ ጉባኤ እንድታዘጋጅ መመረጧን አስታውቋል። እስከ 2 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች እንደሚሳተፉበት በሚጠበቀው በዚሁ ጉባኤ ላይ፤ የሎጀስቲክስ ኢንዱስትሪው ላይ ትኩረት  ያደረገ ምክክር ይደረጋል። 

ማህበሩ የኢትዮጵያ የሎጀስቲክ ዘርፍን በተመለከተ ለመንግስት ጥያቄ ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በተካሄደ ውይይት ላይ እንደነበር አቶ ዳዊት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። “የሎጅስቲክ ዘርፍን እንዴት ማዘመን ይቻላል?” በሚል ርዕስ በተካሄደው ውይይት፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር፣  ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ነው።

የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር የሎጀስቲክ ዘርፉ “ለጊዜው ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት እንዳይደረግ” የጠየቀው፤ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ከውጭ አቻዎቻቸው ጋር ለመወዳደር “የመዘጋጃ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው” እንደሆነ አቶ ዳዊት አስረድተዋል። የውጭ ባለሀብቶች በባንክ እና በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፉ መንግስት ሲፈቅድ፤ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የመዘጋጃ ጊዜ መስጠቱን ያስታወሱት አቶ ዳዊት፤ “እኛም [ዘርፉ] ሙሉ ለሙሉ ለውጭ ከመከፈቱ በፊት የጎደለንን እንድናሟላ ድጋፍ እንዲደረግልን ጥያቄ አቅርበናል” ሲሉ አብራርተዋል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews

EFFSAA Official

10 Oct, 11:36


መስከረም 30፣2017

ኢትዮጵያ ከ3 ዓመት በኋላ (እ.አ.አ በ2027) የሚደረገው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ጉባኤ ለማስተናገድ መመረጧን ተነገረ።

የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር በሰጠው መግለጫ ይህን አለም አቀፍ ጉባኤ ለማዘጋጀት 4 ጊዜ ውድድሮች ማድረጓንና ሳይሳካ መቅረቱን ተናግሯል።

ለዚህም እንደምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ያለው ጦርነትና የሰላም እጦት፣ ተፎካካሪ ሀገራት የተሻለ የውድድር ሃሳብ ይዘው ይገኙ ስለነበር መሆኑን በመግለጫው ተነስቷል።

ዓለም አቀፉ የዕቃ አስተላላፊዎች ማህበር ፌዴሬሽን እንደ ጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ1926 ጀምሮ ይህንን ጉባኤ ሲያካሄድ ነበር ያለው ማህበሩ በዚህ ጉባኤ በተለያዩ የሎጀስቲክስ ኢንዱስትሪው ዐቢይ ጉዳዮች ላይ ይመክርበታል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ ስታስተናግድ ኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎች ከአለም አቀፍ የዘርፉ ባለሞያዎች ጋር እንዲገናኙ እድል ይከፍታል የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ የአፍሪካ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ማዕከል ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ጥሩ እድል ይሰጣል ሲል ማህበሩ አስረድቷል።

በጉባኤው ሁሉም አባል ሀገራት እንደመገኘታቸው ግዙፍ አለም አቀፍ የሎጀስቲክስ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉድርጅቶች ጋር አብረው እንዲሰሩም እድል ይሰጣል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/2dakzmyn

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ዓለም_አቀፍ_የሎጂስቲክስ_ጉባኤ

EFFSAA Official

08 Oct, 13:18


#CapitalNews | Ethiopia selected to host 2027 FIATA World Congress

International Federation of Freight Forwarders Associations (FIATA), the world’s largest logistics organization, has chosen Ethiopia to host the FIATA World Congress in the new century, the largest event in the industry, after many unsuccessful attempts.
Addis Ababa has been chosen to host the 64th FIATA World Congress for 2027 by the congress that convened in Panama City last week for the 61st FIATA World Congress.

Read More

EFFSAA Official

07 Oct, 10:09


የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና የማኅበሩ ጽ/ቤት ሠራተኞች የቀድሞ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በነበሩት በኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ይገልጻሉ፡፡
ኢንጅነር ጥላሁን በማኅበራችን በተከናወነው የአራተኛው ዙር የአሠልጣኞች ሥልጠና ፕሮግራም ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ሥልጠናውንም በአግባቡ በመፈጸም ከፊያታ ዲፕሎማ ሥልጠና ኮርሶች መካከል አንዱ የሆነው የባቡር ትራንስፖርት አሠልጣኝ ነበሩ፡፡
ማኅበራችን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸውና ለወዳጆቻቸው በሙሉ ልባዊ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ለነፍሳቸው የሰላም እረፍት ይሁን!


The Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) is deeply saddened by the passing of Engineer Tilahun, the former CEO of Ethio-Djibouti Railway S.C.
Engineer Tilahun was a valued participant in our association's 4th round Train the Trainer (ToT) program and a certified trainer for the FIATA Diploma Training program's Rail Transport course.
EFFSAA extends its heartfelt condolences to Engineer Tilahun's family, relatives, and friends.

May his soul rest in eternal peace!

EFFSAA Official

02 Oct, 08:54


𝗖𝗢𝗡𝗙𝗜𝗥𝗠𝗘𝗗!!!
𝗙𝗜𝗔𝗧𝗔 𝗪𝗢𝗥𝗟𝗗 𝗖𝗢𝗡𝗚𝗥𝗘𝗦𝗦 𝟮𝟬𝟮𝟳 𝗪𝗜𝗟𝗟 𝗕𝗘 𝗛𝗘𝗟𝗗 𝗜𝗡 𝗔𝗗𝗗𝗜𝗦 𝗔𝗕𝗘𝗕𝗔!
We are thrilled to announce that Ethiopia has been selected to host the FIATA World Congress in 2027. EFFSAA would like to express its deepest gratitude to all stakeholders whose support played a crucial role in our successful bid. An official press conference will be held by the association shortly.

https://fiata.org/n/ethiopia-to-host-2027-fiata-world-congress-in-addis-ababa--highlighting-africas-growing-role-in-global-logistics/

EFFSAA Official

10 Sep, 09:41


ማኅበራችን እንኳን ለ2017 ዓ.ም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም እና ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁም ይመኛል፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!

EFFSAA Official

09 Sep, 06:41


𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 #𝐅𝐈𝐀𝐓𝐀𝐃𝐢𝐩𝐥𝐨𝐦𝐚 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐚𝐧𝐝 𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐚𝐫𝐞𝐞𝐫 𝐢𝐧 𝐋𝐨𝐠𝐢𝐬𝐭𝐢𝐜𝐬!

𝓔𝓿𝓮𝓷𝓲𝓷𝓰 𝓪𝓷𝓭 𝓦𝓮𝓮𝓴𝓮𝓷𝓭 𝓢𝓮𝓼𝓼𝓲𝓸𝓷𝓼 𝓐𝓿𝓪𝓲𝓵𝓪𝓫𝓵𝓮!


More Information?

📱+2️⃣5️⃣1️⃣ 9️⃣0️⃣3️⃣ 1️⃣8️⃣2️⃣5️⃣2️⃣5️⃣

📞+2️⃣5️⃣1️⃣ 1️⃣1️⃣5️⃣ 5️⃣8️⃣9️⃣0️⃣4️⃣5️⃣

📧 [email protected]

📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)

EFFSAA Official

05 Sep, 13:18


𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 #𝐅𝐈𝐀𝐓𝐀𝐃𝐢𝐩𝐥𝐨𝐦𝐚 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐚𝐧𝐝 𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐚𝐫𝐞𝐞𝐫 𝐢𝐧 𝐋𝐨𝐠𝐢𝐬𝐭𝐢𝐜𝐬!

𝓔𝓿𝓮𝓷𝓲𝓷𝓰 𝓪𝓷𝓭 𝓦𝓮𝓮𝓴𝓮𝓷𝓭 𝓢𝓮𝓼𝓼𝓲𝓸𝓷𝓼 𝓐𝓿𝓪𝓲𝓵𝓪𝓫𝓵𝓮!


More Information?

📱+2️⃣5️⃣1️⃣ 9️⃣0️⃣3️⃣ 1️⃣8️⃣2️⃣5️⃣2️⃣5️⃣

📞+2️⃣5️⃣1️⃣ 1️⃣1️⃣5️⃣ 5️⃣8️⃣9️⃣0️⃣4️⃣5️⃣

📧 [email protected]

📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)

EFFSAA Official

02 Sep, 11:37


𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 #𝐅𝐈𝐀𝐓𝐀𝐃𝐢𝐩𝐥𝐨𝐦𝐚 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐚𝐧𝐝 𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐚𝐫𝐞𝐞𝐫 𝐢𝐧 𝐋𝐨𝐠𝐢𝐬𝐭𝐢𝐜𝐬!

𝓔𝓿𝓮𝓷𝓲𝓷𝓰 𝓪𝓷𝓭 𝓦𝓮𝓮𝓴𝓮𝓷𝓭 𝓢𝓮𝓼𝓼𝓲𝓸𝓷𝓼 𝓐𝓿𝓪𝓲𝓵𝓪𝓫𝓵𝓮!


More Information?

📱+2️⃣5️⃣1️⃣ 9️⃣0️⃣3️⃣ 1️⃣8️⃣2️⃣5️⃣2️⃣5️⃣

📞+2️⃣5️⃣1️⃣ 1️⃣1️⃣5️⃣ 5️⃣8️⃣9️⃣0️⃣4️⃣5️⃣

📧 [email protected]

📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)

EFFSAA Official

29 Aug, 06:58


𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 #𝐅𝐈𝐀𝐓𝐀𝐃𝐢𝐩𝐥𝐨𝐦𝐚 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐚𝐧𝐝 𝐀𝐝𝐯𝐚𝐧𝐜𝐞 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐚𝐫𝐞𝐞𝐫 𝐢𝐧 𝐋𝐨𝐠𝐢𝐬𝐭𝐢𝐜𝐬!

𝓔𝓿𝓮𝓷𝓲𝓷𝓰 𝓪𝓷𝓭 𝓦𝓮𝓮𝓴𝓮𝓷𝓭 𝓢𝓮𝓼𝓼𝓲𝓸𝓷𝓼 𝓐𝓿𝓪𝓲𝓵𝓪𝓫𝓵𝓮!


More Information?

📱+2️⃣5️⃣1️⃣ 9️⃣0️⃣3️⃣ 1️⃣8️⃣2️⃣5️⃣2️⃣5️⃣

📞+2️⃣5️⃣1️⃣ 1️⃣1️⃣5️⃣ 5️⃣8️⃣9️⃣0️⃣4️⃣5️⃣

📧 [email protected]

📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)

EFFSAA Official

27 Aug, 13:20


𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐞𝐞𝐬 𝐨𝐟 𝐍𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐂𝐮𝐬𝐭𝐨𝐦𝐬 𝐏𝐫𝐨𝐜𝐞𝐝𝐮𝐫𝐞𝐬 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠