HHSC_Student service & provision_D

@edu_ssdu


Educational Channel

HHSC_Student service & provision_D

13 Sep, 21:06


Better late than never, but wisdom is best shared by those who practice it.😷😷

HHSC_Student service & provision_D

09 Sep, 15:32


በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።
     -------------------------------------------------
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት ለአገር አቀፍ ፈተና ከተቀመጡ 674,823 ተማሪዎች ውስጥ 36, 409 ወይም 5.4 በመቶ የማለፊያው ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ9,114 ተማሪዎች ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።

በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 28,158 ወይም 9 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ 8,251 ወይም 2 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አመላክተዋል።

በፈተናው 1,221 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በባለፈው  ዓመት ከተመዘገበው 220  አንጻር የተሻለ ውጤት መሆኑም ተገልጿል።  ቀደም ሲል በነበረው የመሰናዶ ትምህርት በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ከትግራይ ቀላሚኖ ት/ቤት አንድ ተማሪ 675 ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ፈተናቸውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዲስ አበባ አግዚሊየም ካቴድራል ት/ቤት 575 (በሴት ተማሪ) በማህበራዊ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ 538 (በሴት ተማሪ) ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ።

በዚህ ዓመት ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ከአምናው በተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ 1,363 ት/ቤቶች ግን ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በመጨረሻም 50 በመቶና በላይ ያመጡት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ጠቅሰው የተወሰኑ ተማሪዎችም በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

HHSC_Student service & provision_D

05 Sep, 16:02


የተግባር ምዘና ፈተና ለምትወስዱ የአንስቴዥያ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ 19/2016 ዓ.ም በተሰጠው የመውጫ ፈተና አልፋችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የተግባር ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ፈተናው በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ለመሰጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከጷግሜ 1/2016 ዓ.ም - መስከረም 5/2017 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ፈተናውን የምትወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦

እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

HHSC_Student service & provision_D

08 Jul, 18:58


Dear department heads, please share these 👆 HPLE infoemation booklets with your staffs as well as the students.

HHSC_Student service & provision_D

08 Jul, 13:49


መድሃኒተኛውን እናሳክመው!

ወንድማችን አቤል ተሾመ ከ1 አመት በፊት 2015 ሀምሌ በClinical Pharmacy ከሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በከፍተኛ መዓረግ ተመረቆ የልፋቱን ፍሬ እንኳ ሳያጣጥም ከሰባት ወር በፊት በድንገኛ አጣዳፊ የኩላሉት ጉዳት (Acute kidney injury) እና የደም ግፊት ፣ ገለምሶ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ወዲያው ወደ ጥቁር አንበሳ Refer ይባላል ፤

በጥቁር አንበሳ የውስጥ ደዌ ፣ የኩላሊት ስፔሻሊቲ ንዑስ ክፍል (Nephrology Department) ላለፉህ 7 ወራት የህክምና ክትትል ሲያረግ፣ ጎን ለጎንም ላለፉት 3 ወራት በመቻራ (ዳሮ ለቡ) ሆስፒታል በተመረቀበት ሞያ ህዝቡን እያገለገለ ሳለ፣ ከወር በፊት ህመሙ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ክትትል ከሚያረግበት ክፍል፣ የኩላሊቶቹ ጉዳት የመጨረሻ ደረጃ End Stage Renal Disease እንደደረሰ እናም የኩላሊት እጥበትና ንቅለ-ተከላ እንደሚያስፈልገው ተወስኗል።

ለዚህም ህክምና ቢያንስ እስከ 2 ሚሊየን እና ከዚያም በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮ ፤ አሁን ላይ ወደ ቅዱስ ጷውሎስ ተዘዋውሮ የቅድመ ንቅለ ተከላ ሂደት ጀምሯል::

ሆኖም የዚህ ህክምና ወጪ ከአንድ ፋርማሲስት እና መንግስት ሰራተኛ ቤተሰቡ አቅም በላይ ስለሆነ ውድ ኢትዮጵያዊያን የበረከት እጃቹሁን እንድትዘረጉልን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

CBE Bank Account
1000055874895 Abel Teshome

📞 0942909490 አቤል

___
👉 ለተከታታይ የጤና መረጃዎች
በTelegram-  t.me/Thequorachannel
በGroup t.me/Ethiopianquora
በFb  https://www.facebook.com/Doctorsonlineeth/
በWhatsapp Channel
https://tinyurl.com/4934hfbf
በwebsite https://doctorsonlinee.com
ይከታተሉን።

➡️ Share

HHSC_Student service & provision_D

29 Jun, 20:29


The deadline for applications is rapidly approaching, so don't miss out on this fantastic opportunity to advance your career.

HHSC_Student service & provision_D

28 Jun, 14:17


ማስታወቂያ
የፋርማሲ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን (Exit Exam) አስመልክቶ የተዘጋጀ ተጨማሪ ማብራሪያ
የ2016 ዓ.ም የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሚ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በጠዋትና በከሰዓት በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ ማሳወቃችን ይታወቃል።
ሆኖም ከተፈታኞች ቁጥር አንጻር ፈተናው በተጠቀሰው ቀን ጠዋት ከ2:30 ሰዓት ጀምሮ ለግማሽ ቀን ብቻ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ የሚከተለው ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
1. በዚህ ፈተና የሚቀመጡት ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች (First seater) እና ፣

2. ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተና ተፈትነዉ የማለፊያ ውጤት ያላገኙ ተፈታኞች (re-takers) ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን የመውጫ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች መውጫ ያዘጋጀው መሆኑ ታውቆ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች በጤና ሚኒስቴር የሚዘጋጀውን የላይሰንሰር ፈተና በሌላ ጊዜ እንደሚሰጣችሁ እንድትገነዘቡ እያሳወቅን ጊዜው ወደፊት በሚወጣ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።

HHSC_Student service & provision_D

27 Jun, 15:46


የ2016ዓ.ም የፋርማሲ የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ለተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ
    …………………………………………….
ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ. ም በ 244 ፕሮግራሞች በ57 የመንግስትና በ124 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለስድስት ቀናት ያለምንም እንከን የተሰጠው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የተሰጠዉ የፋርማሲ ፈተና ብቻ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል። ስለሆነው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ፈተናውን በድጋሜ እንዲወስዱ አመቻችቷል።
በዚሁ መሰረት ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከ 3:00 ሰአት ጀምሮ እና ከሰአት ከ 8:00 ሰአት ጀምሮ ስለሚሰጥ ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ Source: Ministry of Education