Ethiopian Broadcasting corporation ®

@ebc_tv


Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media.

https://telega.io/c/EBC_TV
ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!!
https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:43


#ማስታወቂያ #እንሸልሞት

ሰላም የethiocryptohunter ቤተሰቦቻችን ቻናላችንን ለማሳደግ giveaway አዘጋጅተናል።

❇️ giveaway መሳተፍ ምትፈልጉ  በሚሰጣቹ ሊንክ ብዙ ሰው የጋበዘ አሸናፊ ይሆናል ሽልማቱ 0.5 Ton ወይም 400 Birr ነው እንደፍላጎቱ🥳🎁🎁

❇️ Giveaway ሚጠናቀቀው ቻናላችን 1000 member ሲገባ ነው በየመሀሉ በደረጃ እየመሩ ያሉትን ሰዎች የምናሳውቅ ይሆናል

የራሳቹን መጋበዣ ሊንክ ለመቀበል Dm🏃‍♂🏃‍♂
      👇👇👇👇👇

@Crytoking1212 በዚህ አውሩኝ

👇👇ቻናላችንን join አርጉ👇👇

@ethiocrytohunter
@ethiocrytohunter

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:30


በወልዲያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች
******

በወልዲያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም መገላገሏን የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገለጸ።

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚድዋይፍሪ ባለሞያ የሆኑት ወጋየው ገብሬ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር እንደገለጹት፤ሰላማዊት ደርቤ የተባለች የ31 ዓመት እናት በትናትናው እለት ንጋት ላይ 4 ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ በሰላም ተገላግላለች፡፡

ከተወለዱት ሕጻናት መካከል የሁለቱ ክብደት ከመጠን በታች በመሆኑ በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ አራቱ ልጆች እና እናታቸው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የሕጻናቱ ወላጅ እናት ከዚህ ቀደም አንድ ልጅ እንዳላትም ጠቁመዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም 3 ልጆችን የወለደች እናት መኖሯን አስታውሰው፤ይህ ክስተት ግን ለሆስፒታሉም ሆነ ለአከባቢው አዲስ ነው ብለዋል፡፡

በሜሮን ንብረት

#ETV#etv

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:29


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመርኩ ነው - የአዲስ አበባ ፖሊስ
*****

በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ መንስኤ እየመረመረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከል እና በአካባቢው በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁሟል፡፡

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ላይ ቀላል በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱንም አመላክቷል፡፡

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍ እና ተባባሪነትም ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደ ፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:28


የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ሽኝት ተደረገላቸው
*******

የዓለም እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ለፕሬዚዳንቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ፣ የካፍ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ የፊፋ ዋና ፀሐፊ ማትያስ ግራፍስትሮም፣ የካፍ አባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች፣ የቀጣናዊ እግር ኳስ ማኀበራት ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:28


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ
******

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አግዷል፡፡

ቦርዱ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዳስታወቀው የታገዱት ፓርቲዎች የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ናቸው።

በፓርቲዎቹ ላይ የተሰጠው የዕግድ ውሳኔ ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለጊዜው ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ የሚያደርግ ነው።

በመሆኑም ቦርዱ የሰጠውን የዕግድ ውሳኔ እስከሚያነሳ ድረስ ከላይ የተገለጹት ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በሚያዘጋጃቸው ጉባዔዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡም ሆነ ሊመረጡ እንዲሁም በኮሚቴ አባልነት ሊያገለግሉ አይችሉም ተብሏል።

የጋራ ምክር ቤቱ የዕግድ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ፓርቲዎች ከማንኛውም የምክር ቤቱ ሥራዎች እና እንቅስቃሴዎች እንዳይካፈሉ እንዲያደርግም ቦርዱ አሳስቧል።

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 17:27


የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅነት ጥያቄ በካፍ የአሰራር ስርዓት ይታያል - የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ
**

የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅነት ጥያቄ በካፍ የአሰራር ስርዓት እንደሚታይ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ተናግረዋል፡፡

የካፍ መስራች አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ሚና እንዳላትም አውስተዋል፡፡

ለአፍሪካ ነጻነት ትልቅ አቅም የነበረችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ በትክክለኛ ጊዜ ለካፍ ጥያቄ ማቅረቧንም አንስተዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን ለእግር ኳስ ያላቸውን ከፍ ያለ ስሜት እረዳለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ እግር ኳስን ህዝባዊ አንድነትን ለመፍጠር መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስጎበኟቸው በግንባታ ላይ ባሉ ስታዲየሞች እና የስፖርት መሰረተ ልማቶችም መደሰታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ጥያቄ በካፍ የአሠራር ሂደት እንደሚታይም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Ethiopian Broadcasting corporation ®

22 Oct, 10:03


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ ጉባዔ ለመሳተፍ ሩሲያ ገቡ
***

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ ጉባዔ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን በሩሲያ ካዛን መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡