ዲኔን በብዕሬ✍🏼

@dinen_be_biere


#ጌትየ..

{ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ሰይፍ #የሰላ አድርግልኝ።}
_______________________________
ምስጋና ይድረሰው ቀለም ለፈጠረ፥
ያደረከን ጌታ ጥበብ የቋጠረ።
💜💜💜

For any comment👇 @muslimah85

For Spam👇 @dinen_be_biere12_bot

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

10 May, 11:00


"ከቻልክ አዋቂ ሁን፤ ይህን ማድረግ ካልቻልክ ለማወቅ ጣር፤ ይህንንም ማድረግ ካልቻልክ አዋቂን ውደድ፤ ያን ካልቻልክ ደሞ አዋቂውን (ዓሊሙን) አትጥላ፡፡"
.
©ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ(ራ.ዓ)

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

10 May, 10:52


'
እንቅልፍ የወሰደው ሰው ከእንቅልፉ እስኪነቃ ድረስ ህልም ላይ መሆኑን አይገነዘብም፣
አኼራን የዘነጋ ሰውም እንደዚሁ ብዙ ያመለጠውን ነገር የሚያስተውለው ከሞተ በኋላ ነው።

ኢላሂ! ከዘንጊዎቹ አታድርገን!🥺

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

08 May, 18:43


ባል:👳
ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን
የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን
ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር
አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር😍


ሚስት:🧕
እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር
እሾህ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር
የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና
አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና

በህልም ሳይሆን በ እውን የምንገጥምበትን እለት ቅርብ ያድርግln😂 ጀሊሉ ምን ይሳነዋል ?ምንም

زوجتي أمي الثانية 😍

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

08 May, 18:43


ከህይወታችን የሄደ ላይመለስ በህይወታችን የገባ ከህይወታችን ላይወጣ ቢሆን ኖሮ....

መለያየቶች ባልበዙ እና ልቦች ባልተሰበሩ ነበር 🥀

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

08 May, 18:43


☆ጭንቀትህ ሁሉ የአሏህን ውዴታ
ማግኘት ሆኖ መኖር በጣም ደስ ይላል☆

♡ልብህ በአሏህ ፍቅር እየመታ ምላስህ አሏህን ማውሳት ሲያዘወትር ዱንያ ውስጥ ሆነህ ሌላ ዓለም ውስጥ እንዳለህ ይሰማሃል♡

انقطع الرجاء إلا منك يا الله، وخابت الآمال إلا فيك، وانسدت الطرق إلا إليك، وأُغلقت الأبواب إلا بابك، فلا تكلنا إلى أحدٍ سواك !!
رحماك يا الله😔

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

06 May, 12:32


ሰዎች ዘንድ ጥፋት አጥፍተህ ይቅርታ ቢያደርጉልክም እንኳን እንደበፊቱ ቅርብ እና ተወዳጅ አትሆንም!💔
አላህ ጋር ግን ወንጀል ሰርተህ ስትሄድ ምህረቱን ስትጠይቀው እጅጉን ይደሰትብሀል ድሮ ከነበራችሁ ቅርበት እጥፉን ይቀርብሀል!❤️‍🩹
ምርጫው ያንተ ነው!

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

06 May, 12:32


«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

03 May, 06:40


♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️🥀♥️

🥀“ …ከኡመቶቼ መሀከል አንዱ ሲራጥ  (ጀሀነም ላይ የተዘረጋን ድልድይ) ለመሻገር አንዴ እየዳኸ፣   አንዴ እየተንፋቀቀ ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ሊወድቅ እየተንጠለጠለ ሲሰቃይ አየሁ፤ በዚህ የጭንቅ ወቅት ታዲያ በኔ ላይ ያወረደው ሰለዋት ከገባበት መከራ ታድጎ በሁለት እግሩ አቆመው … ”
               {ነብዩ ﷺ ❤️}

♥️ያ አላህ በሱናቸው ላይ አኑረን፤
🥀በመንገዳቸውም ላይ ግደለን፤
♥️ከጭፍራዎቻቸውም ጋር ቀስቅሰን፤
🥀ከስብስባቸውም ውስጥ አድርገን🤲🥺

♥️ከቀናት ሁሉ አውራና ምርጥ በሆነው ጁመዐ ቀን በታላቁ ሰው ﷺ ላይ ሰለዋት ማለት በቀጥታ ነቢ ጆሮ ነው የሚደርሰው።

🥀እከሌ የእከሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሰለዋት አውርድዋል ተብሎ ስምህ የዓለማት ነቢይﷺ ፊት
መነሳቱ ምን ያማረ ነው🥰🤗

            🕊የአላህ ሰለምና ውዳሴ🕊

♥️በዚያ በጨለማ ዘመን ብርሀን በሆነ፤
🥀በዚያ ፍቅርን ባስተማረ ፤
♥️በዚያ ልቦችን በወንድማማችነት ባስተሳሰረ፤
🥀በዚያ በሁሉም ነገር መልካምነትን ባሳየ፤
♥️በዚያ በጭንቅ ቀን ኡመቴን በሚለው ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰

        🤍🤍መልካም ጁመዐ🤍🤍

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

16 Apr, 13:13


🇱🇧🏴‍☠️ ሰበር


የሊባኖስ ኢስላማዊ ተቃውሞ ሂዝቦላህ በሁለት ዙር የጥቃት ድሮኖችን በመጠቀም የአየር ጥቃትን ከፍቷል፣ በበይት ሂላል የሚገኘውን የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ኢላማ በማድረግ፣ የእስራኤል የአይረን ዶም መከላከያ ስርዓትን እና  ወታደሮቻቸውን በመምታት ጉዳት አድርሷል።




ወታደራዊ መግለጫዎች፡-

ሙጃሂዲን ብርጌድ - ዌስት ባንክ፡- ታጋዮቻችን በአላህ ሃይል እና እገዛ በትላንትናው እለት በተገቢ የጦር መሳሪያዎች ናብሉስን ከወረሩ የጽዮናውያን የጠላት ሃይሎች ጋር ከባድ ውጊያ አድርገዋል፡፡

ሙጃሂዲን ብርጌዶች - ዌስት ባንክ፡- ታጋዮቻችን በአላህ ችሮታ እና እገዛ ከናብሉስ በስተምስራቅ በሚገኘው አስካር ካምፕ የነበረ የጽዮናውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪን በአካባቢው በተሰራ ፈንጂ በተሳካ ሁኔታ አፈንድተዋል።

አል-አሲፋህ ሀይሎች፡- ከኑሰይራት ካምፕ በስተሰሜን በሚገኘው አልማሊክ ወታደራዊ ቦታ አካባቢ የነበሩትን የጽዮናውያን የጠላት ወታደሮችን እና ተሽከርካሪዎችን በከባድ የሞርታር መሳሪያ ደብድበናል፡፡

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

15 Apr, 13:31


እስራኤል ሳኡዲ አረቢያን #አመሰገነች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በዛሬው እለት ባወጣው የምስጋና የኢራንን የሚሳኤል ጥቃት በመከላከል በኩል ከፍተኛ እገዛ ላደረጉ ሀገራት ምስጋና አቅርቧል ። በዚህም መሰረት ከአረብ ሀገራት ሳኡዲ አረቢያን እና ጆርዳንን ያመሰገነ ሲሆን ከምእራባውያን ሀገራት ደግሞ አሜሪካን እንግሊዝን እና ፈረንሳይን አመሰግኗል ።

እስራኤል ከኢራን የተሰነዘረባትን የሚሳኤል ጥቃቶች በመመከት በኩል የሳኡዲ አረቢና የጆርዳን ሚና የማይተካ ነበር ብላለች ፅዮናዊቷ ሀገር ።  ወልስትሪት #ዶርናልና_ዶይቸቬለ እስራኤልን ከኢራን ሚሳኤሎች በመጠበቅ ረገድ የሳኡዲ አረቢያንና የጆርዳንን ሚና በተነተኑበት ሀተታቸው #ካለሁለቱ_ሀገራት አስተዋፅኦ እስራኤል የሚደርስባት ውድመት ከዚህም የከፋ ነበር ብለዋል ። ሁለቱ ሀገራት ለአሜሪካና አጋሮቿ መረጃዎችን በማቀበል የአየር ክልላቸውን ለእስራኤልና አጋሮቿ በመክፈት ፤ የነ አሜሪካ የጦር አይሮፕላኖች አየር ላይ በመከላከል በቆዪበት ወቅት ነዳጅ በመሙላት ከዚያም ሲያልፍ የኢራን ድሮኖችን መቶ በመጣል ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ የእስራኤልን ኪሳራ ቀንሰዋል ብለዋል ።

እስራኤልም ለነዚህ ሀገራት ምስጋናዋን አቅርባለች።
ሳኡዲ አረቢያ ኢማራትና ጆርዳን የየመን ሁቲዎች #ለጋዛዊያን አጋርነት የእስራኤልን የንግድ መስመር ሲቆርጡ ግዛታቸውን በመክፈት #በፍልስጤማውያን ላይ ክህ*ደት የፈፀሙ ሀገራት ናቸው ።

አንድ ቀን ግን ታሪክ ይፋረዳል😔 !!

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

13 Apr, 05:46


✔️✔️እርምጃ  ውሰድ✔️✔️

መርከቡ ወደ አንተ ካልመጣ አንተ ወደ መርከቡ አየዋኘህ ሂድ!
              ጆናታን ዊንተር

ወደሚጠብቋቸው ሰዎች ሊመጡ የሚችሉት በተጣደፉ ሰዎች የተተው ነገሮች ብቻ ናቸው ።

አለም የሚከፍልህ ለምታውቀው ነገር ሳይሆን ለምትሰራው  ስራ ነው።

እርምጃ  ስትወስድ ወደ ሰኬት የሚወስዱ ነገሮችን ሁሉ በማያጠራጥር ሁኔታ አነሳሳሃቸው ማለት ነው።   መልካም ነገሮች ሁሉ ወደ አንተ አቅጣጫ መፍሰስ ይጀምራሉ።

ስኬታማ ለመሆን ስኬታማ ሰዎች የሚሰሩትን መስራት አለብህ።

ስኬታማ ሰዎች በሙሉ  ድርጊት ተኮር ናቸው።

እርምጃ መውሰድ እስካልቻልክ ድረስ ምንም ነገር አትፈጥርም❗️                                                                                                         

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

12 Apr, 19:13


እሷ🧕፦ሀቢቢ ተነስ መስጂድ ሂደህ ስገድ
እሱ👳፦እዚሁ ቤት እሰግዳለሁ ሁቢ
እሷ🧕፦ግን እኮ ውዴ ሀዲሱ መስጂድ🕌 ሄዳችሁ ስገዱ ነው የሚለው
እሱ👳፦እንደዛ ካልሽማ ሀዲሱ 4 ሚስት ማግባት ትችላላችሁ ይላል እኮ ውዴ😍
እሷ🧕፦የኔ ውድ ና እሺ እዚሁ በጀመዓ እንስገድ ተነስ

😂😂

https://t.me/halal_mem1

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

12 Apr, 06:43


فَإِذَا فَرَغْتَ فَانصَبْ

በጨረስክም ጊዜ ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡(ሱረቱ ሸርህ 7)

የኢስላም ልዩ ባህሪው እረፍት አያውቅም ሁሌም አንድን ነገር ስንጨርስ እንድቀጥል የሚያዝ ድንቅ ዲን ነው 💚💚💚
ከተናፋቂው ወር በኋላ የመጀመሪያ ጁምዓ ረመዳን ሄዷል ሰላቱ፣ ቁርዓኑ፣ ዚክሩ፣ዱዓው ሁሉም በረመዳን የሰራናቸው ኢባዳዎች አሁንም አሉ እና አትረፉ ቀጥሉ ልፉ።

❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️

ኢባዳችንን የምናስቀጥልበት ለመልካም የምንሽቀዳደምበት ፣ በዛች በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ ራህመት የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የፈካ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

11 Apr, 06:14


አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ   ?

ሴት ልጅ ቢኖረህ እና እንደ
#አንተ አይነት ወንድ ቢወዳት

አንተ እንዲያገባት
#ትፈቅድለታለህ ?

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

09 Apr, 16:28


ማራኪ የዒድ ተክቢራ

الله أكبر الله أكبر الله أكبر،
لا إله الا الله والله أكبر الله ولله الحمد.

الله أكبر الله أكبر الله أكبر،
لا إله الا الله والله أكبر الله ولله الحمد.

الله أكبر الله أكبر الله أكبر،
لا إله الا الله والله أكبر الله ولله الحمد

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

06 Apr, 10:22


👨የሕፃኑ አስደናቂ ታሪክ
•┈┈•❈••✦✾✦••❈•┈┈•
☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር         አመት ታዳጊ ነው
ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።
ነገሩ እንዲህ ነው:

ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል
ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

🔴ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

🤔ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...
   🗣«እኔ ምጮህው አለ......
እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው አልቅሦ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

🚫ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!

♥️ሱብሃን አላህ
  በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ ነው
【 ሼር】በማድረግ አስተላልፉት።

         

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

06 Apr, 05:45


ረመዳን 😔

ታስታውሳላቹ ረመዳን ከሪም ስንባባል😔

እስኪ አሚን በሉ😭😭

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

05 Apr, 17:36


👨የሕፃኑ አስደናቂ ታሪክ
•┈┈•❈••✦✾✦••❈•┈┈•
☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር         አመት ታዳጊ ነው
ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።
ነገሩ እንዲህ ነው:

ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል
ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

🔴ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

🤔ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...
   🗣«እኔ ምጮህው አለ......
እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው አልቅሦ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

🚫ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!

♥️ሱብሃን አላህ
  በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ ነው
【 ሼር】በማድረግ አስተላልፉት።

         

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

05 Apr, 17:36


<< አንቱ ሰው ምን ይመክሩኛል? >>
<< ውብ ጊዜ ይኑርህ! >>
<< እንዴት ማለት? >>
<< ከጊዜ ሁሉ የተዋበው ከጌታህ ጋር የምትሆንበት ነው። ውብ ጊዜ እንዳታጣ። >>
<< አንቱ ሰው እወዶታለሁ። >>
<< ከተዋበው ጊዜዬ ላይ ዱዓ አደርግልሀለው። >>
    (አብዱልሀኪም ሰፋ)
:

ዲኔን በብዕሬ✍🏼

04 Apr, 11:57


ልብ ውስጥ የሚገባ ቲላዋ 🎧

ሼይኽ ማሂር.....🔊

3,790

subscribers

38

photos

7

videos