ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

@daewaselefiyaarbaminch


ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ
ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ !
"ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? "
ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል !

ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር
@JemalEndroAbuMeryem

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

23 Oct, 03:10


"አር ማረኝ"
~
ተውሒድን አጥብቀህ ተማር። ተውሒድ ለኣኺራ ብቻ አይደለም ፋይዳው። ለዱንያም መከበሪያህ ነው።
ተውሒድ ካልተማርክ

• ጉጉት ትፈራለህ፣
• አይጥ ትለማመጣለህ፣
• ውሻ አላዘነ ብለህ ትሸበራለህ፣
• የቁራ ድምፅ ከመንገድ ይመልስሃል፣
• እጅ ወይም አንገት ላይ በታሰረ እርባ ቢስ ክር ትተማመናለህ፣
• ዛፍ ላይ ክር ትተበትባለህ፣ ቅቤ ትቀባለህ፣
• እጅህን ስላሳከከህ ትደሰታለህ፣ (ሰዎች እጃቸውን ሲያሳክካቸው ምን እንደሚሉ አስታውስ።)
|
• ተውሒድ ካልተማርክ ከሶላት የተኳረፈ ገሪባ "ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው" እያለ ይጫወትብሃል። ጠንቋይና ወሊይ ይምታታብሃል።
• ሃያሉን ጌታ ጥለህ ሙታን ትማፀናለህ። (ይልቅ እነሱን መለመንህን ትተህ ለነሱ ዱዓእ አድርግላቸው።)
• ተውሒድ ካልተማርክ "ማርያም በሽልም ታውጣሽ"፣ "የማርያም መቀነት"፣ "የማርያም ፈረስ"፣ "ማርያም ስማህ ነው"፣… እያልክ ክርስትና ክርስትና የሚሸት ኹራፋት ታራምዳለህ።
• የአምስት ብር ጎመን የማያክል አረንጓዴ መርዝ (ጫት) መቶ ሁለት መቶ ብር ገዝተህ "የዱዓእ መሳሪያ" እያልክ ትጃጃላለህ።
• የሁለት አመት ህፃን "ካካ" ስትለው የሚፀየፈውን አፈር፣ "ቱራብ" እያሉ ከቀብር አካባቢ ቆንጥረው ሲሰጡህ በጥብጠህ ትጠጣለህ።
• አዎ ተውሒድ ካልተማርክ የተቀበረ ብር አገኛለሁ ብለህ ጠንቋይ እየቀለብክ በእጅህ ያለውን ገንዘብ ታጣለህ።
• ልጅህ ሲባልግ፣ ሲያፈነግጥ ዝም ብለህ ተውሒድ ሲማር፣ ሶላት ሲሰግድ፣ መስጂድ ሲያዘወትር፣ ጥሩ ጓደኛ ሲይዝ እሪ ትላለህ፣ (እንዲህ ነው የሸይጧን መጫወቻ መሆን።)
• ተውሒድ ካልገባህ ከሺርክ የሚያስጠነቅቁ ተቆርቋሪዎችን እንደ ጠላት እየቆጠርክና ጧት ማታ እያጠለሸህ ሶሐቦችን የሚያወግዙ፣ ቁርኣንን የሚያረክሱ ሺዐዎችን ታወድሳለህ። አልተማርክማ! እንዲሁ "ሲሉ ሰማሁ ብየ፣ እላለሁ ነብዬ" ብቻ!
• ተውሒድ ካልተማርክ ለቶንሲል ህመም "አር ማረኝ" እያልክ በአይነ ምድር ታሻርካለህ። ሰው እንዴት ካካውን ይማፀናል? ወላሂ ከእንዲህ አይነቱ ካካውን ዞሮ ከሚማፀን ጉደኛ ፍጡር፣ ካካውን የሚያቦካ የአእምሮ በሽተኛ ሺ ጊዜ ይሻላል።
ጎንበስ ብለህ ተውሒድህን ተማር። አካዳሚ ትምህርት ከሺርክ አያወጣህም። ስንት እንጨት፣ ላም፣ ድንጋይ፣ ሰው፣… የሚያመልኩ፣ ጠንቋይ ለጠንቋይ የሚርመጠመጡ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች አሉ መሰለህ?
\=\

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

22 Oct, 15:16


ጉራጌ አካባቢ ጅልባብ መልበስ የሚፈልጉ አሉ ብሎ ለጠየቀን ወንድማችን 7 ጅልባቦች ሰጥተናል በዚህ ስራ መሳተፍ የሁላችንም ሃላፊነት ነው ሌሎች ያልደረሳቸው እህቶች ዘንድ እንድናደርስ ከአሏህ በታች እንድታግዙን እንጠይቃለን
እዚህ ጋር የጎደላቸውን 3 ጅልባብ ለመግዛት ፍቃደኛ የሆናችሁ በዚህም በውስጥም መነየት ትችላላችሁ ባረከሏሁ ፊኩም

አድሚናቶች

https://t.me/NikabJilbab

https://t.me/nikab_jilbab_group

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

22 Oct, 14:30


የብዙ ባለትዳሮች ትልቅ ችግር ስልክ ነው በተለይ ባሎች። ባሎች ስልጋቸው ላይ ይቀመጡና ለሚስታቸው በቂውን ጊዜ አይሰጡም፣ትኩረቷን አያዳምጡም፣ችግሮቿን አይሰሙም ።በየ አጋጣሚው ስልካቸው ላይ ማፍጠጥ ፣ስልካቸውን በፓስወርድ መቆለፍ ፣ሚስታቸው እንዳታውቅባቸው መከልከል ነው። ባሎች ሆይ ! ይህ ነገር ካልተስተካከለ ትዳራችሁን ያበላሽባችኋል፣ በባለቤታችሁ በጥርጣሬ ዓይን እንድትታዩና እንዳትታመኑ ያደርጋችኋልና .... እናም ይስተካከል

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

22 Oct, 12:06


ሃኪም ወይም ሩቃ አድራጊ እና ታማኝነት
     -----------------------
አንድ ዶ/ር  ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት። ሩቃ የሚያደርግም ሰው ልክ እንዲሁ¡ አላህን ሊፈራ እና

* የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም።

* ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር ከገጠመው ወደተሻለ ቦታ መጠቆም እንጂ የሰውን ልጅ መለማመጃ ሊያደርግ አይፈቀድም። ከባድ ወንጀል ነው።

* ገንዘቡን ያላግባብ ሊያስወጣው አይፈቀድም።

የሰው ገንዘብ ሐራም የሚሆነው በስርቆትና በዝርፊያ ብቻ አይደለም። ምርመራና የሚሆነውንም የማይሆነውንም መድሃኒት በማዘዝ፣ አስተኝቶ በማከም፣ በቀዶ ህክምና፣ በየትኛውም መንገድ ባልተገባ መልኩ የታካሚውን ገንዘብ ያስወጣ ሰው የሰው ገንዘብ እየዘረፈ ነው።

ይህን ያደረገ ሰው እያንዳንዱ ሰው ገንዘቡን እንዴት እንዳመጣው እና በምን እንዳወጣው በሚጠየቅበት አስፈሪው የቂያማ ቀን ወዮለት።

ዛሬ ያላግባብ ለተወሰደ ገንዘብ ሁሉ ነገ ጥብቅ ሂሳብ አለ። ብር በብር አይመለስም። ከመልካም ስራህ ነው ተላልፎ የሚሰጠው። እሱ ካልበቃ የተበዳይ ወንጀል ነው ባንተ ላይ የሚጣለው። ለማይረባ አላፊ ዱንያ ዘላለማዊ ህይወትን ከማጨለም መጠንቀቅ ይገባል።

=
ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ላይ የተወሰደ እና ትንሽ በኡስማን ሰዒድ(አቡ አመቲረህማን) የተጨመረበት

•════•••••••🌺🍃••••••════•
https://t.me/alruqyehsheriyeh
•════•••••••🌺🍃••••••════•

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

20 Oct, 04:18


ራሳችንን በጥልቀት እንፈትሽ!!

ደግሞም በዱዓ ላይ ችክ እንበል (እንጠንክር እንበርታ)
~~~~
ሼይኹል  ኢስላም ኢብን ተይሚያ
ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ


" አጋሪዎች(ሙሽሪኮች) ጭንቅ በገጠማቸው ጊዜ አላህን ለምነው(ዱዓእ ) አድርገው ዳአቸው ተቀባይነት ያገኝ ከነበር

አማኝ (ሙወሂድ)  ከሆነ
(የበለጠ ተቀባይነት አለው።)

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

19 Oct, 15:02


ለሺዐ መነሳት ሰበቡ በኑ ኡመያ ናቸው የሚል አየሁኝ። ይሄ ጥላቻ ወይም አለማወቅ የወለደው ድምዳሜ ነው። የሺ0 አሰተሳሰብ ጥንስሱ በዐሊይ ዘመን ነው። 0ሊይኮ በኸዋሪጅ ላይ እንኳ ያላደረጉትን ከባድ እርምጃ የወሰዱት እሳቸውን ጌታ አድርገው እስከማመን በደረሱ ድንበር አላፊ ሺዐዎች ላይ ነው። ከመግደልም ባለፈ በእሳት ነው ያቃጠሏቸው።
አንዳንድ ሰዎች ለበኑ ኡመያ ያረገዙት ጥላቻ ብዙ ርቀት እየወሰዳቸው ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

19 Oct, 05:41


لا يسخر قوم من قوم

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

18 Oct, 17:12


🌹خطبة الجمعة🌹

📌لا يسخر
قوم من قوم
...💥

🌷فضيلة الشيخ الدكتور🌷
💐محمد بن سعيد رسلان
(حفظه الله تعالى) 💐

الجمعة 15 من ربيع الثاني 1446هـ
الموافق 18-10-2024م


🔊🖥تلجرام📲

https://t.me/elkhotab/9025

الموقع الرسمي

https://www.rslan.com/vad/items_details.php?id=13363

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

18 Oct, 15:42


ቀጥታ ስርጭት ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=

https://t.me/IbnuMunewor?livestream

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

18 Oct, 03:59


አንድ ሸይኽ ወይም ሌላ ከሞተ በሗላ ይጠቅማል ብለው  የሚያስቡት
ሲሞት አይቶት   ልብሱን አውጥተው ከፍነውት  ሙቶል ብሎ ሶላተ ሰግዶበት ከዚያ እለህድ አስገብቶ ደፍኖት፥ ንብረቱን ተከፋፍለውት   ሲበቃ  ሀብት ይሰጣል ልጅ ይሰጣል ይጠቅማል ይጎዳል ምናምን    ልብሱን ማውለቅ አቅቶት አውልቀህ አጥበህ ስታበቃ  ልጅ ሌላም ነገር ከሱ እደት  ይከጀላል
አላህ  በዚህ ጉዳይ የተዘፈቁትን ያውጣቸው ሞት ሳይመጣ  እኛንም በተውሂድ ያፅናን


አሚን

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

17 Oct, 13:37


የሪባ (የአራጣ ) አይነቶች

https://t.me/Muhammedsirage

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

17 Oct, 13:25


....✍️መቼ ነው አንድ ተቋም የሚኖረን⁉️

ከአመታት በፊት ዳዕዋ ለማድረግ ፈተና ነበር።
በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ግን የዳዕዋዎች ብዛትና መነቃቃት መልካም ነበር።

...... አሁን ላይ በሚያሳዝን ሁኔታ ዳዕዋው በጥቂት ሰዎች ጫንቃ ላይ ብቻ ጭላንጭሉን እያየን ነው።

የነገን አላህ ያውቃል..! ገጠሩ ከምንጊዜውም በላይ የአክፍሮተ ሀይላት እና የተለያዩ የሽርክና የቢዲዓ አደጋዎች አንዣበውበታል።

መሬት ላይ ያለው ሐቅ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንደምናየው አይደለም፣ መሬት ላይ ያለው ነገር ፈጽሞ የተለየና እጅግ የከፋ የስፈሪ ሁኔታ ነው።

በተቻለ መጠን ጥረቶች ቢኖሩም ቀረብ ብለን ስናየው ግን በተቃራኒ በኩል የኢስላም ጠላቶች እና ከጥመት ቡድኖች የሚሰራጨው ሰፊ ስራ ያስደነግጣል።

የኛን ሁኔታ ላስተዋለ ደግሞ ተስፋ ያስቆርጣል።
ከጊዜያዊ ምቾታችን ስንባንን እንዳያረፍድብን ያሰጋል።

የሱናው ሰው ቴሌግራምና መሰል ሚዲያወች ላይ ተጥደን እዚህም ላይ ጦርነታችን እርስ በርስ ሆኗል ጠላቾቻችን ግን ድምፅ አጥፍተው ከላይ እስከታች ተናበው ሙስሊሙን ከመንግስት መዋቅር እስከ ቀበሌ ሊቀመንበር ድረስ እያጠመቁ እምቢኝ ያላቸውን እያስጨነቁ ብዙ እርቀት ሔደዋል።

«የዚህ መሰል መሰሪ ተግባር በመንግስት ይሁንታና ድጋፍም ጭምር የሐዋሳን ከንቲባ ጨምሮ ጴንጤወች ሲደቀኑብን...!!

...በሌላ በኩል ኦርቶዶክስና ሲኖዶሱ ደግሞ ለስብከት አቋም ባይኖርም ሙስሊም ጠል የሆነ የፋኖ አይነት መሀይማን መንጋ አሰማርቶ ከግራና ከቀኝ አህባሽና አላዋቂ ሙስሊሞን በዘርና በስልጣን በጥቅምም ጭምር እየደለለ የትላንቱን በዳይና አግላይ የአፄ ስርዓት ለመመለስ እየተጋጋጠ ነው።

«ሙስሊሙ አሁንም ቁጭ ብሎ ይመለከታል የነቁ ጥቂቶች ቢኖሩም ማን ሰምቷቸው⁉️»

በተቻለን ለራሳችን ስንል እንንቃ የተጋረጠብን አደጋ ዘርፈ ብዙ ክስተት ነው እባካችሁ ህሌናችን እንጠይቅ ግራ ቀኝ እንመልከት እላለሁ

....✍️ኑር

https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

17 Oct, 08:38


ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ ነበር። ዛሬ በአንፃሩ ለውጥ አለኝ አልሐምዱ ሊላህ። ህመም ጋር በተያያዘ ጥሩ ያልሆነ ልማድ አለኝ። ሃኪም ቤት መሄድ አልወድም። ህመሜ ከባድ ደረጃ ሲደርስ ወይም መንቀሳቀስ ሲያቅተኝ ግድ ሲሆን ነው የምሄደው። እንደተለመደው መቋቋም ሲያቅተኝ በአቅራቢያ ያለ ሃኪም ቤት ገባሁ። ሳውቀው በጣም ህዝብ ይርመስመስበት ነበር። ፀጥ ረጭ ብሏል። ከኔ ውጭ ሁለት ታካሚ መሰለኝ ያየሁት። ያውም አንዷ ድንገተኛ። ለህክምናዬ ያወጣሁትን የገንዘብ መጠን ሳይ ሰውን ያሸሸው ይሄ የተጋነነ ዋጋ ዋና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ።
ሰው አማራጭ ስለሌለው ወይም አማራጩ ስለሚያንስ ብቻ በዚህ ልክ መጨከን ጥሩ አይደለም። በርግጥ እኔ የሄድኩበት የሙስሊም ቤት አይደለም። ነገር ግን የሙስሊሞቹም የባሱ እንጂ የተሻሉ እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁም። ለዚህ የዋጋ ንረት የተጠቃሚውም ድርሻ ቀላል አይደለም። የህክምናውን ጥራት በሚከፍለው ብር መጠን የሚለካ አለ። ክፍያው ዝቅ ሲል ለተቋሙ የሚሰጠው ግምት አብሮ ዝቅ ይልበታል። እንዲህ አይነቱን ሳይነቃ እንደነቃ የሚያስብ ወይም ጥጋበኛ እንተወውና ለሰፊው ህዝብ ግን አንድ ነገር ማለት ጥሩ ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠማችሁ በስተቀር ህክምናችሁን በመንግስት ተቋማት አድርጉ። ለዚህ አንዱ ምክንያት የህክምና ዋጋ ነው። ከዋጋ ያለፉ ሌሎችም ምክንያቶች በተጨባጭ አሉ። ለነገሩ ህዝባችን አሁን በመንግስት ተቋማት ለመታከምም የሚያቅተው ደረጃ እየደረሰ ነው። አላህ ይድረስልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

17 Oct, 03:22


በአመጽና በአላዋቂነት የተሰበረ ስብእና ሰዎችን አለ አግባብ በመተቸት አይጠገንም ። አላህን ባለመፍራት የወረደ ማንነት የስራ ሰዎችን ነጋ ጠጋ በመዘርጠጥ ሽቅብ ሊወጣ አይችልም ።

አማኞች ያለ አግባብ መተቸት ስርአት አልበኝነት ነው ! ሰዎችን በሌሉበት ነገር መውቀስ ብልግና ነው ! እውቀትን እና ፍትሕን መሰረት ያደረገው ትችት ሌላ በሰዎች ወሰን ማለፍና ተራ ዝርጠጣ ሌላ ! በሁለቱ ላይ ውሸት ሲታከልበት ደግሞ ሰዎችን ይበልጥ ያከረፋል !
ኢብኑ ሙነወርን አላህ ይጠብቀው !

ከኢብኑ ሙነወር እጅጉን ከማወቃቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ - ውሸትን አጥብቆ ይጠላል ! በአላህ እምላለሁ! ይቅርና ሊገባበት !

https://t.me/Muhammedsirage

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

16 Oct, 13:08


ሰዎች ማልቀስና መጨነቀ በነበረባቸው ቀን ልደታቸው እያከበሩ እንኳን ደስ አለህ ፣እንኳን ደስ አለሽ ይባባላሉ።

🎙በኡስታዝ አቡል ዐባስ ሀፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

16 Oct, 03:37


ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሙሀመድ አህመድ ለሱንናው ዓለም ያበረከተውን 1/100ኛውን ያልሰራ ሁላ እኮ ነው እየተነሳ ሙነወር/የሙነወር ልጅ/ እያለ የሚያላዝነው!

በል እንዳውም ለሱና አንድ ቀን አስተዋፅዖ በዳዕዋም ሆነ በተግባር አድርጎ የማያውቀው ሁላ በሱ ላይ ለመዝመት ተጠራርተው ሲነሱ ስታይ ምን ያክል ጥላቻ ያሰከረው ቡድን እንደሆነ ትታዘባለህ !

ሰው በድንህ ላይ ድንበር አትለፍ ተብሎ ሲመከር ይሄን ያክል ያዋራጫል እንዴ !?

ይህ ማለት ጥፋት ካጠፋ ዒልሚይ የሆነ ምላሽ አይሰጥ ማለት አይደለም ግና እስካየነው እስከ አሁን ሁሉም  እሱ ባልዋለበት የሚከሱት፣ ባላጠፋው የሚወነጅሉት በራሳቼው ግምት ጠምዝዘው በዚያው በጠመዘዙት ላይ ተንጠልጥለው ከፊሎቹ የምቀኝነት በሚመስል ከፊሎቹ ለምን በኛ ሳንባ አይተነፍስም ከፊሎቹ ለምን እኛ ያልነውን አይልም ተከታዮቻቼው ደግሞ ለምን እንደኛ ለመሻኢኾቻችን ሙሪድ አይሆንም እያሉ በየቦታው የሚያቀነቅኑት እየታዘብናቼው ያለውም ይሄንኑ ነው !

እወቁ አላህ ከፍ ያድርገውን ማንም ዝቅ አያደርገውም። አላህ ዝቅ ያደረገውን ማንም ከፍ ሊያደርገው አይችልም።


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15141

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

15 Oct, 17:05


ለ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁላህ
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
የኛ ጀግና ኡስታዝ ባለግርማሞገስ፤
ሽርኩና ቢድዐው ባንተ ሰበብ ይፍረስ፥
ንግግርህ ጣፋጭ ከውብ  እርጋታ ጋ፤
አውዳሚ ነው ብዕርህ ለቢድአ መንጋ፥
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
አንድ ፁሁፍ ስትለቅ ይናጋል ሀገሩ፤
ለምን እንደሆነ ገብቶናል ሚስጥሩ፤
ለስሜት ተከታይ ሀቅ መማረሩ ፤
የማይቀር ነውና በርታልን አብሽሩ።.

     አቡ ሩመይሷ

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15140

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

15 Oct, 02:58


👉ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሙሀመድ አህመድ አቡ ሁዘይፋ https://t.me/IbnuMunewor ማለት:–
...........................................
~ከድሮም ጀምሮ ለራሱ በማይነቃነቅና በፀና አቋም ላይ መሰረቱን የተከለ፣በዳዕዋ ሂደቱም ላይ በመረጃ የተገነባ የሚጓዝበት መርህ ያለው አስታዋይና አርቆ አሳቢ፣በጣም ጥንቁቅ ሰው ከመሆኑም ባለፈ በየጊዜው ለሚፈለፈሉ የቢድዐ አንጃዎች ሁሌም ምላሽ በመስጠት የእግር እሳትና የተሰላ ሰይፍ ነው።
ለአህባሽ፣ለሱፍያ፣ለኢኽዋን፣ለተብሊጝ፣ለተክፊር፣ለሀጁርያ ኧረ ምን የቀረው አለ!!

ብቻ አረህማን በራህመቱ ይጠብቅልን ከመልካም ስራ ጋር ዕድሜውን ያርዝምልን እንቁ እና የአይናችን ማረፊያ ኡስታዛችን ነው ።

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15139

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

14 Oct, 06:59


الحمد لله=====الحمد لله
አልቡኮ ወረዳ የነበረው የደዕዋ ፕሮ ግራም
ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል አካባቢው ትንሽ ሰላም ይጎድለዋል አሏህ ሰላም ያርገው ከዚሁ በመነሳት ኔት እንኳ ተዘግቷል።

ሲቀጥል የመስጂዱ ኸዳሞች ያላቸው አክብሮትና ፍቅር የተለዬ ነው አሏህ ይጠብቃቸው።
ሙሓደራዎቹ በወንድም አሕመድ አቡ ሹራ በኩል ይለቀቃሉ

t.me/abumuazhusenedris

2,333

subscribers

1,945

photos

512

videos