Grace & Truth Ministry

@biruk351


እንኳን ወደዚህ ቻናል በሰላም መጡ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ በእውነት ቃልና በፀጋው መንፈስ ይታነፁ

Grace & Truth Ministry

11 Oct, 04:27


'ጸሎት የታዛዥነት የአኗኗር ዘይቤ አካል ነውመጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ነገሮች የሌሉን ስለእነርሱ እግዚአብሔርን ስለማንጠይቅ ነው ይላል (ያዕቆብ 4፡2 ተመልከቱ) እና ትላቁ የጸሎት ሚስጥር እርሱ አስቀድሞ ያዘጋጀልንን እንድጠይቀዉ መፈለጉ ነው። . #እግዚአብሔር_ሉዓላዊ_እና_የሚፈልገውን #ማንኛውንም_ነገር_በየትኛውም_ቦታ፣ #በማንኛውም_ጊዜ_በፈለገው_መንገድ #ማድረግ_የሚችል_እና_የማንንም_ፍቃድ #የማይፈልገው_እንድንጠይቀው_ይፈልጋል።

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ ጅማ

👉👉 @biruk351

Grace & Truth Ministry

09 Sep, 19:50


#ትምህርተ_ፀሎት


ጸሎት ጽናት ይጠይቃል፤ የሚጸልዩ የሚቀጥሉ እንጂ የሚያቋርጡ መሆን የለባቸውም። "ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንዲገባቸው" ጌታ ሲያስተምር የክፉውን ዳኛ ምሳሌ ነገራቸው። እርሱ መበለቲቱ ስላሰለቸችው ብቻ ፈረደላት፤ ለራሱ አስቦ ፍትሕን 'ፈጸመ'። ጌታም ስለ እንከን አልባው የሁሉ ዳኛ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? : ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን?" (ሉቃ 18፥7)። ነገር በከፋበት ጊዜ የፍትሕ ጩኸት አብዝቶ ይሰማል። ጩኸትን ማሻሻል ግን መፍትሔ ያመጣል፤ እግዚአብሔርን ታምኖና አምኖ መጮኽ!: በፀሎት የፀኑ በእምነታቸው የተመሠከረላቸው አባቶች አሉን ፤ ከእነርሱ በፀሎት መፅናትና አለመታከትን ልንማር ይገባል። ለብዞቻችን ፀሎት ያስፈልጋል፥ በፀሎት መካኒቱ ወልዳለች፣ በፀሎት ዳንኤል በአንበሳ ጉጉጓድ ውስጥ አድሮአል፣ ለአንበሳ ምግብ መሆኑ ሲጠበቅ እርሱ ግን በደህና አድሯል "እነ አብድናጎ ሰድያቅ ምስያቅ በፀሎት እሳት ውስጥ አምላካቸው አሳይተዋል: ባያድነንም ላቆምከው ለወርቁ ምስል አናመልክም ብሎ በፀሎት የመታመንን ውጤት አሳይተዋል ። በትጋት ያለመታከት የሚፀልይ ሰው ለቤተሰብ ለአገር መፍትሔ ይሆናል።

Luke 18:7
❝And will not God bring about justice for his chosen ones, who cry out to him day and night? Will he keep putting them off? ❞

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይሄንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

Grace & Truth Ministry

31 Aug, 14:54


#ትምህርተ_ፀሎት

ጸሎት የመንፈሳዊ ኅልውና መገለጫ ነው፤ ስለዚህ የሚቋረጥ አይደለም። መጸለይ ያቋረጡ ወይም የተዉ ሰዎችም መንፈሳዊ ጤንነታቸው ስለ ተጓደለ አፋጣኝ 'ሕክምና' ያስፈልጋቸዋል። ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው የመጀመሪያ መልእክቱ ላይ "ሳታቋርጡ ጸልዩ" ብሎ አሳሰባቸው (5፥17)። ይህንን ያለው ሐዋርያ የትም ቦታ ቢሆን—እስር ቤትም ጭምር—"ሌሊትና ቀን" ይጸልይ ነበር። ለእርሱ የሁኔታ መክፋት ፣ ተስፋ ማጣት ወይም 'ኵርፊያ' ሆኖ ጸሎት ማቋረጫ አይደለም፤ ይልቁንም አብዝቶ የሚጸልይበት አጋጣሚ እንጂ። ሳያቋርጡ ለመጸለይም ሁልጊዜ በጌታ መታመን ግድ ነው። እርሱን ለመታመን ደግሞ እርሱን መጠጋጋት አማራጭ የለውም። አንዱና ዋነኛው መጠጋጊያም ጸሎት ነው። የሚጸልዩ፣ ሳያቋርጡ የመጸለይ አቅም እያገኙ ይሄዳሉ። ሳያቋርጡ መፀለይ በየትም ቦታ የሚሆን በልብና በቃል የሚገለጥ መንፈሳዊ ቅኔ ነው። መፀለይ ልብን ከሚፈልግ ብዙ ነገር ተላቀን ለእግዚአብሔር ልብን መቀደስ ነው። ሌላ ነገር ልባችንን ሲፈልግ እምቢየው ብለን "ለእግዚአብሔር ሀሳብን" ማስገዣ መንገድ ነው። ያለማቋረጥ መፀለይ በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ ወይም በመንፈስ ሀሳብ ውስጥ መገኘትና መቃተት እንጂ ስርዓትና ደንብ የቃላት ጫጫታ አይደለም ።

(1 Thessalonians 5:17)
"pray continually,"

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይሄንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @birik351

Grace & Truth Ministry

30 Aug, 14:13


#ትምህርተ_ፀሎት

ጸሎት ቀላል ቢመስልም ቀላል ግን አይደለም፤ ምክንያቱም ስጋዊ አእምሮ ይሄን ለማድረግ መሰልጠንና መላመድ አለበት ። ብዙ ሐሳብ ማሰብ፣ ማውጣትና ማውረድ የሁልጊዜ ተግባር ነው፤ ከሌሎች—ከሚቀራረቡን ጋራ—ማውራት ባለማቋረጥ የምናደርገው ብቻ ሳይሆን የምንናፍቀውም ነው። ከአምላክ ጋራ ማውራት ሲሆን ግን 'ዳገት' ይሆንብናል—ወደ ሰማይ ማውራት ወደ ሰማይ እንደ መውጣት ይሆንብናል። ስጋ በመንፈስ ላይ ፥ መንፈስም በስጋ ላይ ቢቀወምም : የመንፈስ ቅዱስ በእኛ መኖር የመንፈሳዊ አቅማችን ትልቅ ምስጢር ነው ። አቅም ማጣትም አቅም በመቀበል ይተካል። መንፈስ ቅዱስ የጸሎት አጋዣችን የሆነው ለዚህ ነው፤ "በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመናበማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩይህንም በማሰብ ንቁስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ" (ኤፌ 6፥18)። የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ እግዚአብሔር በክርስቶ ኢየሱስ በኩል ለመቅረብ አቅሎንናል፣ ይሄ በመዳናችን ቅፅበት የተከናወነ ነገር ነው ። መንፈስ ቅዱስ በእኛ መኖር ውስጥን አረስራሽና ውጤታማ ያደርገዋል። በርሱ ወደ እርሱ መቅረብ፣ ለራስና ለሌሎችም መጸለይና መማመልድ ቀላል ብቻ ሳይሆን ምቹ፣ ተግባር ብቻ ሳይሆን ደስታም ይሆናል።

#Ephesians_6:18
And pray in the Spirit on all occasions with all kinds of prayers and requests. With this in mind, be alert and always keep on praying for all the Lord’s people.❞
#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ
#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን 🙏
ወደ ቻናላችን ለመቀላቀልና መንፈሳዊ ፀጋን ለመካፈል ይኼንን ሊንክ ሁለቴ ብቻ ይንኩ 👉 @biruk351

Grace & Truth Ministry

26 Aug, 11:04


#ትምሕርተ_ፀሎት

#ጸሎት_ይሰማል_ይታያልም፣ "እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል ልመናቸውንም አይንቅም" (መዝ 102፥17) እንደ ተባለ ከመለመናችን በፊት በልባችን ያለውን ማወቁ ማየቱ ነውጌታ በርግጥ ያያል፤ ላሳሰበን (#ላብሰለሰለን) ነገር ምላሽ ይሰጣል። በርሱ እየታዩ መደመጥ፣ እየተደመጡም መታየት ትልቅ ዕድል ነውትኩረት እንደ ተሰጣቸው የሚያውቁም አምላካቸውን ሁልጊዜ #በጸሎት_ያነጋግራሉ።

ስንፀልይ በራስ መተማመናችን ይጨምራል ፣ ስንፀልይ የመደመጥ #ቃል-ኪዳናችን ድፍረትን ይሰጠናልስንፀልይ በውስጥ ሰውነታችን ጠንካሮች እንሆናለን የውጩንንም ነገር እንደ ቀሊል እናያለን!

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀልና በመንፈሳዊ ፁህፎች ለመታነፅ ይሄንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ
👉 @biruk351

Grace & Truth Ministry

24 Aug, 04:11


ትምህርተ-ፀሎት

ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ።”  ኤፌ 1፥19

#ሃይል 🔥🔥🔥🔥🔥
👉ፍርሃትን ወደ ድፍረት ይቀይራል
👉በሽታን ወደ ጤና ይቀይራል፣ 
👉ደካማን ብርቱ ያደርጋል
👉ባሪያን ነጻ ያደርጋል
👉ፈሪን ደፋር ያደርጋል፣ 
👉የማይቻለውን ያስችላል
👉ጥላቻን ወደ ፍቅር ያለውጣል
👉ሽንፈትን ወደ ድል ይቀይራል
👉ድህነትን በብልጽግና ይተካል
👉አለማወቅን በእውነት ይሽራል። 
🗝ከሁሉ በሚበልጥ አሰራሩ ደግሞ ሃይል ሁኔታው ሳይቀየር የሁኔታውን ውጤት ያጠፋል
🗝ሃይል በክርስትና ህይወት ውስጥ መሰረታዊ ነገር የሆነው ለዚህ ነው

ረዘም ላለ ጊዜ በአንዳንድ ሁኔታዎች በመጥፋቴ ምክንያት ተቋርጦ ነበር: አሁን አለው : እግዚአብሔር ይረዳኛል

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ ⛪️

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን🙏

Grace & Truth Ministry

09 Jul, 11:36


ትምሕርተ-ፀሎት

ማቴዎስ 5:44 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ።

📌 የቀደመችው ቤተክርስቲያን አንዱ ተግባር ጸሎት ነው። እኛም እንደ አማኞች እንድንጸልይ በመልእክቶች ውስጥ ብዙ መመሪያዎችን እናያለን። ማንኛውም አማኝ በጸሎት የዘገየ በአለመታዘዝ ውስጥ እየኖረ ነው እና ለዛውም የአገልግሎትን ስራ ለመስራት እስከምን ድረስ ልንፀልይ ይገባል?!። ስለ ጸሎት ሆን ብለን እናስብ እና ሌሎች አማኞችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ማበረታታት አለብን። ይሁን እንጂ በአለም ላይ የሚጸልዩት ክርስቲያኖች ብቻ እንዳልሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል።

📌 በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት ይቻላል ይጸልያሉ፤ ይፀልያሉ የሚለው ቃል እስከ ማይገልጣቸው ድረስ ረዥም ሰዓት ባልተቋረጠ ሁኔታ ይፀልያሉ። ይህ ማለት መጸለይ አማኝ ለመሆን ማስረጃ አይሆንም። ስላለህበት ነገር ከአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ድምፅ በመቅዳት: መጸለይ የድንቁርና ጸሎት መሆኑን ባለፈው ጥናታችን አስረድተናል። እንደነዚህ ያሉት ጸሎቶች መጸለይ ስለሌለባቸው መልስ የላቸውም። ለማግኘት የምንጸልየው ነገር ሁሉ አይደለም። ቀድመን ልናገኛቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ እና እግዚአብሔርን ስለ እነርሱ ልናመሰግነው ይገባል። የተሳሳተ ጸሎት የሚባል ሌላ የጸሎት ዓይነት አለ።

  📌 ከእግዚአብሔር ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስለሆነ የተሳሳተ ጸሎት ልንለው እንችላለን። የማያደርገውን እንዲያደርግ እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ የተሳሳተ ጸሎት ነው። በ1ኛ ዮሐንስ 1፡5 ላይ “ስለ እርሱ የሰማናት ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት ይህች ናት፡- እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም” በማለት በአጽንኦት ተቀምጧል። ይህ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ክፋት የለም ማለት ነው።

📌 እግዚአብሔር ክፉ ወይም ጨለማ የሆነውን እንዲያደርግ የሚለምን ማንኛውም ጸሎት የተሳሳተ ጸሎት ነው። ከእንደዚህ ዓይነት ጸሎቶች ምንም ዓይነት ውጤት በእግዚአብሔር ዘንድ አይገኝም። .በመግቢያችን ላይ ኢየሱስ ጠላቶቻችን ከምንላቸው ሰዎች ጋር በተያያዘ የአምላክን ባሕርይ ገልጿል። የሚረግሙን እና የሚሰድቡን ወይም የሚያሰድዱን። እንዲሞቱ መጸለይ የለብንም።

📌  ሌሎች ሰውችን የሚጎዳ ጸሎቶች የተሳሳቱ ጸሎቶች ናቸው። ይህ አይነት የፀሎት ዘይቤ በቡሊይ ኪዳን ላይ በአንዳንድ ቦታዎች በተለይ በመዝሙረኛው ዳዊት ላይ አለ በተለይ መዝ ዳዊት (109:1-30 ተመልከቱ) አሁን ባለንበት አዲሱ ኪዳን :በእንደዚህ ዓይነት ጸሎት ምክንያት የሞተ ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር አልተገደለም። ነገር ግን ሰይጣን የሰውን ፈቃድ ተጠቅሞ ክፋትን ለማስፈጸም ተጠቅሞበታል። ሌላውን ሰው የሚረግም፣ ሌላውን የሚግደል፣ ጥፋትን፣ ውርደትን፣ ወይም ፍርድ በሌላ ሰው ላይ እንዲመጣ የሚጠራ ማንኛውም ጸሎት ሁሉም የተሳሳቱ ጸሎቶች ናቸው።

📌 እግዚአብሔር ጠንቋዮችን አይገድልም ሆኖም መዳን የሚችሉበትን ፀጋ ያበዛል እምቢ እያሉ ፅዋቸው ሲሞላ ያነሳቸዋል .. ብዙ ጊዜ እነዚህ ጸሎቶች የሚወለዱት ከራስ ወዳድነት እና እብሪተኝነት ነው። እግዚአብሔር ጠላቶቻችንን አይገድልም። ሳይገድላቸው ከጠላቶቻችን ያድነናል። በክርስቶስ በተገለጠው እንደ እግዚአብሔር ባሕርይ በፍቅር መጸለይ አለብን።

👉👉ህይወትን ላለማጥፋት ህይወትን ለማዳን እጸልያለሁ። ተጨማሪ ጥናቶች፡- ማቴዎስ 5፡43-48 የሐዋርያት ሥራ 10:38 2ኛ ተሰሎንቄ 3፡1-2

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ተከታታይ በሆነ መልኩ የቀረቡ መልዕክቶችን ለመጎብኘት ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

Grace & Truth Ministry

07 Jul, 14:04


ትምህርተ-ፀሎት

 📌 ጸሎት በአማኙ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ መንፈሳዊ ልምምድ ነው*። በጸሎት ሥልጣናችንን በክርስቶስ ያገኘነውን መንፈሳዊ ልዕልና በይበልጥ እንጠቀማለን፣ በጸሎት የአገልግሎትን ሥራ ለመሥራት ድፍረትን እናዳብራለን፣ በጸሎት ስለ ሕይወት እና አገልግሎት መመሪያዎችን  እንቀበላለንስንጸልይ በመንፈስ እርስ በርስ እንተባበራለን: ቋሚ እና ከልብ ለመነጨ የጸሎት ህይወት ካልተሰጠህ በአገልግሎት ስራ ውስጥ ሊኖርህ የማይችላቸው የተፅዕኖ መጠኖች አሉ!: ኢየሱስ የጸሎት ጊዜያት ነበረው እና ሐዋርያትም የጸሎት ጊዜያት ነበሯቸው

📌 የመንፈስን ሥራ ለመሥራት ትጋትና ስደትን ለመጋፈጥ መጽናት የሚገኘው በጸሎት ነውምክንያቱም በጸሎት በውስጣችን ባለው ሰው እንበረታለንየእግዚአብሔርን ቃል ባጠናን መጠን መጸለይ አለብንበመንፈስ ብዙ ለማነጽ እና ለመበረታታት በልሳን አብዝተን መጸለይ አለብን

📌ጸሎት አስፈላጊ ቢሆንም የእግዚአብሔርን ቃል አለማወቅ የተሳሳቱ ጸሎቶችን እንድትጸልይ ሊያደርግ ይችላልበቀደመው ጥናታችን እግዚአብሔር ኃይልን እንዲሰጥህ መጸለይ ስህተት እንደሆነ አስተምረናል: ምክንያቱም አንድ አማኝ ለሁሉ ነገር የሚፈልገው ኃይል ሁሉ አስቀድሞ የተሰጠው በመዳን ጊዜ ነውበጸሎት ውስጥ በእኛ ውስጥ ያለውን ኃይል እንጠቀማለንበክርስቶስ በነፃ የተሰጡን ነገሮች አሉ*። እነዚህ ነገሮች ለእኛ እና በእኛ ውስጥ ናቸውበድነት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተሰተውናል ስለዚህ የጸሎት ርዕስ ሊሆኑ የማይገባቸው ነገሮች አሉን። እግዚአብሔር ጻድቅ ያደርግህ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር እንዲልህ፣ እግዚአብሔር መንፈሱን እንዲሰጥህ፣ ለእግዚአብሔር መገኘት እና እግዚአብሔር እንዲወድህ ፣ እግዚአብሔር እንዲቀባህ፣ ስልጣንና ሞገስ እንዲሰጥህ....ወዘተረፈ መፀለይ አይጠብቅብህም።

📌 መነጠቅን ወይም መንግሥተ ሰማያትን እንዳያመልጥን ወይም ስማችን በሕይወት መጽሐፍ እንዲጻፍ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ሁሉም በኪዳናችን ያልተገቡ ጸሎቶች ናቸው። እነዚህ ሁሉ በክርስቶስ ይገኛሉ። ክርስቶስን በተቀበልንበት ቀን በኃጢአት ስርየት ምክንያት ብዙ ነገር ሆኖልናል ። ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ቤተክርስቲያን በኤፌሶን 1፡18 ጸልዮአል “የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ። የመጥራቱ ተስፋ ምን እንደ ሆነ በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስቱ ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው።

📌 ልንጸልይ የሚገባው የማስተዋል ዓይኖቻችን እንዲበሩ በክርስቶስ ያለንን እንድናውቅ ነው። ችግሩ በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን በእኛ ድንቁርና ውስጥ ስላለ ነው። ለመደሰት በክርስቶስ ያለውን ርስታችንን ማወቅ አለብን። እግዚአብሔር እንዲሰጠን መጸለይ የለብንም። እግዚአብሔር አስቀድሞ በልጁ ሰጠን ፡ በእርሱ ለመደሰት: እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የሰጠንን ለማወቅ እናጠናለን እንጸልያለን፣ በተረፈ መንፈስ ቅዱስ በሚያመለክተን አቅጣጫ በሚቃትተበት መለኮታዊ ምሪትና ስለ ቅዱሳን ወንድሞቻችንና ስለ ሐገር መሪዎች እንፀልያለን።

👉👉 በክርስቶስ ውስጥ ያለኝን እንዲኖረኝ አልጸልይም በማለት ጠንካራ አቋም ሊኖረን ይገባል። ተጨማሪ ጥናቶች፡- ኤፌሶን 1፡3-21 ፊልሞና 1፡6 ቆላስይስ 1፡12-14

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️

ወደዚህ ቻናል ለመቀላቀልና ወጥነት ባለው መልኩ የተለቀቀቁ ተከታታይ መልዕክቶች ለማግኘት ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ 👉@biruk351

Grace & Truth Ministry

05 Jul, 05:53


ትምህርተ-ፀሎት

  ✍️✍️የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች"።”(ያዕቆብ 5፥16)
በእያንዳንዱ አማኙ ውስጥ ገደብ የለሽ ኃያል አለ። ይህ በአማኙ ላይ የተቀመጠው ሃይል መታየትና መገለጥ አለበት። ምንም እንኳን ይህ እጅግ ታላቅ ​​ኃይል በውስጣችን ቢኖረንም፣ ካልተገለጠ ግን ኃይል እንደሌለን እንመስላለን። አንዳንድ አማኞች አቅመ ቢስ እንደሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ኃያላን እንደሆኑ እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው በእኛ ውስጥ ያለው የኃይሉ መግለጫ መንገዶች ላይ ባለን እንቅስቃሴ ነው።

 ✍️የመጀመሪያው ደረጃ በእኛ ውስጥ ያለውን ኃይል በቅዱሳት መጻሕፍት በመገለጥ እውቀት ማግኘት አለብን። ይህ የመገለጥ እውቀት በግሪክ “#ኤፒግኖሲስ” ይባላል። በውስጣችን ያለውን ኃይል ስናገኝማመን ወይም ግንዛቤ እስኪሆን ድረስ በዚያ ንቃተ ህሊና ውስጥ በየቀኑ መኖር መጀመር አለብን። ያ እውቀት በግሪክ "#ኢዶ" ይባላል። በውስጣችን ያለውን ይህን ሃይል ልክ እንደ ጾታችን ወይም ስማችንን እንዴት እንደምናውቅ ማወቅ አለብን
📌 በውስጣችን ያለውን ኃይል ኤፌሶን 1፡19 ለእኛ ለምናምን እንደ ኃይሉ አሠራር የኃይሉ ታላቅነት ምን ያህል ነው? : ሰው ወንጌል አምኖ ዳግመኛ ሲወለድ በረከት ወይም በብርሃን የቅዱሳን ርስት እየተባለ በሚጠራው ተካፋይ ወይም ተጠቃሚ ይሆናል። እነዚህ በረከቶች ቀስ በቀስ በሚመጣው ሰማይ ውስጥ አይደሉም። ሁላችንም በክርስቶስ አንድ ርስት አለን። ከእነዚህ ከተገለጡት መንፈሳዊ በረከቶች ጥቂቶቹ፦

  📌 የዘላለም ሕይወት፣ መጽደቅ፣ የኃጢአት ስርየት፣ ስልጣን፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እና ሌሎችም ናቸው። ለመቀበል የምንለምነው ወይም የምንጸልይባቸው  ነገሮች አይደሉምበድነት ጊዜ በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመን ጋር አብረው የመጡ መንፈሳዊ በረከቶቻችን ናቸውማንም አማኝ ከሌላ አማኝ በላይ የለውምእነዚህ በረከቶች አይጨምሩም አይቀንሱምእንደ አማኞች ካሉን በረከቶች አንዱ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ለውጦችን የማምጣት እና ነገሮችን የማከናወን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ችሎታ ነው።

📌 የኤፌሶን ምዕራፍ 1 ቁጥር 20 ይህ ኃይል ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው ያው ሃይል ነው ይላል። እርሱ እጅግ ታላቅ ​​ብርቱ ኃይል ነው። እያንዳንዱ አማኝ በእሱ ወይም በእሷ ውስጥ ያለው ይህ ታላቅ ኃይል አለው። አጋንንትን የማስወጣት፣ የታመሙትን የመፈወስ እና ተአምራትን የማድረግ ኃይል።

📌 ሁላችንም በክርስቶስ እኩል ኃይል አለን የመግለጥና የአለመግለጥ ጉዳይ ግን ሌላ ርዕሰ ይፈጥራል። እንደ ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ወይም እንደ ጴጥሮስ ኃያላን ነን። አንተ እንደ ነብይ ኤኬሌ ኃይለኛ ነህ፣ አንተ እንደ ፓስተርህ ሀይለኛ ነህ Wow : ይህ እውነት የእለት ተእለት ንቃተ ህሊናችን ወይም ግንዛቤያችን መሆን አለበት

📌 ይኼ ኃይል እንዳለን ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም መገለጥና መታየት አለበት፣ ይህ የሚገኘው በጸሎት ነው። በውስጣችን ያለውን ኃይል ለሥራ ዝግጁ የምናደርገው በጸሎት ነውበውስጣችን ያለውን ኃይል ለመግለጽ ድፍረትን የምናዳብረው በጸሎት ነውበዚህ በክርስቶስ ባለን ወሰን በሌለው ሃይል እራሳችንን መግለጽ እንድንችል በቅዱሳት መጻህፍት እውቀትና ወጥ በሆነ የጸሎት ህይወት ራሳችንን መገንባት ይኖርብናል

✍️ አማኝ ከሌላው የበለጠ ኃይል ያለው እንዲመስለው የሚያደርገው እውቀትና በእምነት የተመሠረተ የጸሎት ሕይወት ነውብዙ የህይወት ሁኔታዎች ኃይላችንን እና ስልጣናችንን በክርስቶስ መጠቀምን ይጠይቃሉ። በመክፈቻ ጥቅሳችን "የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ኃይልን ታደርጋለች የሚል ነው!! ፅድቅ ከእምነት ጋር የሚገናኝ ነገር ነው : እምነትም እግዚአብሔር በልጁ በኩል ባደረገው ነገር ላይ ነው። ስለዚህ ፀሎትህ ኃይል አለው ምክንያቱም ፀሎትህን የሚሰማው ኃይልን የሰጠህ ነውና !

✍️ በአንተ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ኃይል ባየህ መጠን በራስ የመተማመን መንፈስ ይጨምራል። በአንተ ውስጥ ያለውን ኃይል ለመግለጽ አትፍራ። በውስጣችሁ ያለውን ኃይልና ስልጣን ተጠቀሙት ፣ ተለማመዱት አጋንንትን አውጡ፣ የታመሙትን ፈውሱ እና ሰዎችን ከችግር ነፃ አውጡ፣ መንፈሳዊነታችሁን፣ ስራዎቻችሁን፣ ጤንነታችሁን በሀይሉ ችሎት ተቆጣጠሩት ኃይሉ በእናንተ ውስጥ አለ!

#የእምነት_ፀሎት
በዚህ እውነትና ቃል አጋንንትን አስወጣለሁ፣ የታመሙትን እፈውሳለሁ እናም ሰዎችን ከችግር እና ከጭቆና ነፃ አወጣለው! በወንጌል በኩል ይኼንን ድል በብዙ መንገድ ያለማመድከኝ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እወድሃለሁ፣አባት ሆይ ይኼንን ሕይወት በልጅህ በኩል ስላካፈልከኝ አመሠግናለሁ፣ አሁንም አይኖቼን እየከፈትክ የሰጠኸኝን ሙሉ ሕይወት እንድጠቀም ታደርገኛለህና እባርክሃለሁ🤲

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ በመንካት በተከታታይ መልዕክቶች ይታነፁ👉@biruk351

#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን 🙏

Grace & Truth Ministry

04 Jul, 05:08


ትምህርተ-ፀሎት

📌 የሐዋርያት ሥራ 2፡42 "ሐዋርያትም በትምህርትና በኅብረት እንጀራም በመቍረስ በጸሎትም ይተጉ ነበር"

📌 በመንፈሳዊ ሕይወት ለማደግ ልንሳተፍባቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ። እነዚህ ነገሮች ለግል እድገታችን እና ኃላፊነቶቻችን እጅግ ጠቃሚ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በአገልግሎት ውስጥ እያደግን መሆናችንን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው እና ኃላፊነት ሊሰጡን ይችላሉ። ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የእድገታችን ተግባራት ናቸውጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለእያንዳንዱ አማኝ ነውእያንዳንዱ አማኝ መጸለይ እና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይጠበቅበታልየጸሎት ስጦታ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚባል መንፈሳዊ ስጦታ የለም

📌 የጸሎት ወይም የምልጃ አገልግሎት ተብሎ የተለየ የአገልግሎት ጥሪ የለምበአገልግሎት ቢሮዎች ውስጥ የጸሎት ተዋጊዎች ወይም አማላጆች የሉም*። ይኼ አመለካከት ምንም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና ድጋፍ የለውም! : ሁላችንም መጸለይ እና መጽሃፍ ቅዱሳችንን ማጥናት ይጠበቅብናልእያንዳንዱ አማኝ የመጸለይ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት**። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት፣ መጸለይ፣ መስጠት፣ ወንጌልን ማስፋፋት ወዘተ የሁሉም አማኝ የጋራ ግዴታዎች ናቸው።

📌 በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተመረጡት ጥቂቶች አይደሉም። *,በመክፈቻው ጥቅስ ላይ ሁሉም አማኞች ከሐዋርያት በመማርና በጸሎት ይሳተፉ ነበርሰዎች ወንጌላዊነት የወንጌላዊው ሥራ ነው ይላሉያ ትክክል አይደለምወንጌላዊው በውስጣቸው ካለው ፀጋ የተነሳ በተግባር የስብከተ ወንጌልን ስራ እንድንሰራ ያስታጥቁናልፓስተሩ በማስተማር እና በተግባር እንድንጸልይ ያስታጥቀናል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጸሎት ተዋጊዎች ወይም የስብከተ ወንጌል ቡድኖች የሚባል ልዩ ቡድን መኖሩ አማኞች ጸሎትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለአንዳንድ አማኞች ልዩ ጥሪዎች እንደሆኑ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል: እያንዳንዱ አማኝ የራሱን ኃላፊነት መሆኑን በማወቅ ከዚህ አመለካከት ነፃ-ይውጣ! በቅዱሳን ሕብረት ውስጥ ሲፀልዩ የተለየ ስጦታ ያለቸው የሚመስሉ ፀሎታቸው የሚርክ አሉይሄ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸው ግላዊ ግንኙነት ያዳበሩት መንፈሳዊነት እንጂ ስጦታ አይደለም!: ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለቸው ልባዊ ትስስር በጆሮአችን ቃላቸው እንዲጣፍጥ እኛ ውስጥ ረሃብ የመክተት አቅም አላቸውስለዚህ ይሄንን በመረዳት በግል ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለንን ቀረቤታ እናበርታ🙏

ተጨማሪ ጥናቶች፡- ሉቃስ 18:1፣8 ማቴዎስ 28፡19-20 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15

#ፀሎት
አባት ሆይ በጌታ በኢየሱስ ስም የፀሎት ሕይወቴ እንዲዳብር እንዲነቃቃቃ ዘወትር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለምታነቃቃኝ አመሠግንሃለው 🙏 እንድፀልይ የምታበረታኝ ከአንተ ጊዜ እንድወስድ የምታደርገኝ አንተ ነህና ስም ይባረክ ፣ አሁንም በፀሎት ሕይወታቸው ወደ ኋለ እንደቀሩ የሚታወቃቸውን ሁሉ በመልዕክቶቼ ወደፊት መሄድ የሚችሉበት ፀጋ ስለምታበዛ እወድሃለሁ

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ ⛪️

ወደ ቻናሉ ለመቀላቀልና ለመታነፅ ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351

#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን

Grace & Truth Ministry

03 Jul, 05:08


ትምሕርተ-ፀሎት
#ጾም_ለኃይል

   ✍️ማርቆስ 9፡28-29 ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ። እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው? እንዲህም አላቸው። ይህ ዓይነት በጸሎትና በጾም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም

  ✍️ ሰይጣንን ማባረር፣ የታመሙትን መፈወስ እና የተጨቆኑትን ነጻ ማውጣት የሚመጣው በአማኙ ውስጥ ባለው አንድ ጊዜ በክርስቶስ በመሆኑ ውስጡ በሚኖረው በእግዚአብሔር ኃይል ነው። ነገር ግን፣ ብዙዎች አጋንንትን ለማስወጣት፣ የታመሙትን ለመፈወስ ወይም የሆነ ተአምራት ለማድረግ ...ኃይል ለመቀበል መጾም እንዳለበት ለማስተማር የመክፈቻ ጽሑፉን ይተረጉማሉ።

✍️በብዙ ቸርቾች ውስጥም አጋንንትን ለማውጣት ጾም እንደሚያስፈልግ ባለማወቅ ያስተምራሉ። ለእነሱ፥ ጸሎት በጾም ሲደረግ ኃይለኛ ይሆናል። አንዳንዶች ተአምራትን ለመስራት ኃይል ለማግኘት ሲሉ እንደ 40 ቀናት፣ 70 ቀናት ወይም 90 ቀናት ባሉ ረጅም ጾም ይሄዳሉ። አንዳንዶች ደግሞ የእግዚአብሔርን ኀይል መግለጽ በጾም ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።

✍️ለመክፈቻ ጽሑፋችን ለመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የሚያገለግሉ አብዛኞቹ ዘመናዊ ቅጂዎች ጾም እንደ አንድ አካል እንደሌላቸው ልብ ማለት ያስፈልጋል። NIV፣ ESV፣ NLT፣ ASV እና ሌሎች በውስጣቸው ጾም የላቸውም። በማቴዎስ 17፡21 ዘገባ ውስጥ፣ አብዛኞቹ አስተማማኝ ትርጉሞች ስለ ጾም የሚናገረው ቁጥር 21 የላቸውም። ይህም ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ኪጄ ተርጓሚዎች በሃይማኖት ተጨምሯል ማለት ነው።

✍️ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ኪጄቪ በዕድሜ የገፋ ቢሆንም፣ ለትርጓሜያቸው ጥቅም ላይ የዋለው የእጅ ጽሑፍ በጣም ጥንታዊው አይደለም ይላሉ። ጥንታዊው የእጅ ጽሑፍ የበለጠ ትክክለኛ መሆን እንዳለበት ይታመናል። ስለዚህ፣ አከራካሪ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ ላይ አስተምህሮ ማዘጋጀት አስተማማኝ አይሆንም። በመልእክቶች ውስጥ በጾም አጋንንትን የማስወጣት ኃይል ጋር የሚያያይዘው ምንም ዓይነት የማረጋገጫ ጽሑፍ የለንም። የአዲስ ኪዳን ፀሀፊዎች ይሄንን በተመለከተ አንዳች በመልዕክታቸው ውስጥ አልተውሉንም ።

✍️በመልእክቶቹ ውስጥ ያለው አጽንዖት የተሰጠው ጸሎት ነውበክርስቶስ አጽንዖት የተሰጠው ጸሎትና እምነት ነውኃይል ለማግኘት ጾምን የሚጠይቅ ትምህርት በክርስቶስ የለምጾም እግዚአብሔር ምንም እንዲሰጥህ ተጽዕኖ አያደርግምጸሎታችሁን ኃይለኛ አያደርገውም

✍️ ለመጾም ስንወስን ራሳችንን ለመጸለይ ትኩረት ለማግኘት እንረዳለን: ነገር ግን ጸሎቱ ቶሎ እንዲመለስ ወይም ኃይል ለማግኘት አይደለም፣ ስንፆም ራስን ለመንፈሳዊነት እናሰለጥናለን ..ከእግዚአብሔር ብዙ ስናሳልፍ አለማመንን ከስጋዊ ጭንቅላታችን እንቃወማለን ፤ አጋንንትን የማውጣት ኃይል እና ስልጣን በክርስቶስ ያለውን ማንነትህን በማወቅና በእምነት ላይ በሚደረግ ፀሎት እንጂ እና በጾም ፀሎት የምትቀበለው ኃይል አይደለም።

✍️ በክርስቶስ ላንተ ያለውን ለማግኘት መጾም ስሕተት ነው። #በጸሎት፣ ሥልጣናችንን እንጠቀማለን እናም በውስጣችን ያለውን የእግዚአብሔርን ኃይል ለመግለጽ ድፍረትን እናዳብራለንለስልጣን አንጾምም አንጸልይምበክርስቶስ ኃይልና ሥልጣን አለኝአጋንንትን የማስወጣት ኃይል ለማግኘት አልጾምም፣ ይሄንን በውስጤ ያለውን መለኮታዊ ሕይወት ለማወቅ የውጩን ጫጫታ ፀጥ ለማሰኘትና ከእግዚአብሔር ጋር ብዙ ለማሳለፍ ከእርሱ እውነቶች ጋር ለመዋሃድ እፆማለው ፣ ያንን ማድረጌ ለራሴ ይጠቅመኛል እግዚአብሔር ግን ስለፆሞክ አይንቀሳቀስም እርሱ አስቀድሞ በክርስቶስ ተንቀሳቅሷል ።

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️

ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ያለማቋረጥ ትምህርተ-ፀሎት የተሰኘ ተከታታይ መልዕክቶችን ለመጎብኘት ይሄንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ 👉 @biruk351

#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን 🙏

Grace & Truth Ministry

21 Jun, 09:05


ትምሕርተ-ፀሎት

ጸሎት የገነትን ኃይል ወደ ምድር ያመጣል። #የጌታ_ጸሎት “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” ይላል። በዚያ መንገድ ስንጸልይ እርሱ በመንፈሳዊው ዓለም ያለው ዓላማ እና ዕቅዶች በምድር ላይ - በሕይወታችን እና በዙሪያችን ባሉት ሰዎች ሕይወት ውስጥ እንዲፈጸሙ ከእግዚአብሔር ጋር አጋር እየሆንን ነውየመንግስተ ሰማያትን ፈቃድ ወደ ተግባር ለማድረግ በምድር ላይ ስልጣን አለን 🙏 #Joyce_Meyer

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

#ተባርካችኋል

Grace & Truth Ministry

17 Jun, 07:43


ትምህርተ-ፀሎት

እግዚአብሔርን የመስማትና የመረዳት ጊዜ ይሁንልን 🙏

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️
#ሼር 🙏
ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይሄንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351

Grace & Truth Ministry

10 Jun, 15:21


ትምህርተ-ፀሎት
🤲 እንጸልይ 🤲

አብዛኞቻችን ቤተክርስቲያን የምንደርሰው አምልኮ ሲጀምር ነው ምክንያቱም ከአምልኮው በፊት ያለውን ጸሎት ቀጣይ ላሉት ፕሮግራሞች የሚያዘጋጀን መሆኑን በቅጡ ስላልተረዳን ነው። በጸሎት ስፍራ የማናውቀው እግዚአብሔር በአምልኮ ስፍራ አይገኝልንም!

📌 ለአንድ ክርስቲያን: በጣም ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ መጸለይ ነው። የማይጸልይ ክርስቲያን ወይም የጸሎት ሕይወቱን ለማሳደግ የማይተጋ ክርስቲያን በክርስትና ህይወቱ ውጤታማ እና ስኬታማ አይሆንም። ምክንያቱም ውጤታማነት እና ስኬት ከእግዚአብሔር ጋር ባለን የጠለቀ ህብረት የሚወሰን ነው።

ከማመስገን ጋር ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ።” (ቆላስይስ 4፥2 (አዲሱ መ.ት)

ዲያቢሎስ በዋናነት ክርስቲያን ላይ አነጣጥሮ ከሚሰራባቸው መንገዶች አንዱ የጸሎት ሕይወታችንን እንዲደክም ማድረግ ነው። ክርስቲያን ደግሞ የጸሎት ሕይወቱ ከተመታ አጠቃላይ ሕይወቱ ይመታል።

ስለዚህ ነቅተን በትጋት ልንጸልይ እና ከመንፈሳዊ አለም ጋር ሁሌ የተገናኘን እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት መሆን የምንችል መሆን አለብን። ምክንያቱም ክርስቲያን ክርስቲያን መሆኑን በሚገባ የሚረዳው ከጌታ ጋር ህብረት ማድረግ ከቻለ ብቻ ነው።

NO PRAYER NO VOICE!
NO PRAYER NO POWER!
NO PRAYER NO ENERGY!
NO PRAYER NO LIFE!

“የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥7 (አዲሱ መ.ት)

💎( ከፓስተር ተዘራ ያሬድ :የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን መጋቢ ገፅ የተወሰደ)

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ ⛪️
#ሼር 🙏

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

Grace & Truth Ministry

08 Jun, 11:07


ትምሕርተ-ፀሎት
📌የሚፀልይ ሰው አይጨነቅም📌የሚጨነቅ ሰው አይፀልይም!

"#ጌታ_ቅርብ_ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:6)

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

Grace & Truth Ministry

02 Jun, 12:47


ትምሐርተ-ፀሎት ባለማቋረጥ የቀጠለ ያለ..

"- - - ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና:
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩበሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ- - - ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁንየዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።" (ማቴዎስ 6፥8-11)

እግዚአብሔር ሳንለምን  የሚያስፈልገንን ካወቀ እንዲሰጠን መጠየቁ ለምን አስፈለጊ ሆነ?
📌#እግዚአብሔር_ሃያል_ነው_ 📌አምባገነን ግን አይደለም
📌 እግዚአብሔር ነገሮችን የሚሰራውና የሚያደርገው ስለሚያውቅና ስለሚችል ሳይሆን በደነገገው ሕግ አማካይነት ነው።(#መርህ)
እግዚአብሔር ሃያል ስለሆነ ብቻ መቻሉን ተጠቅሞ  ከሰው ፈቃድ ውጭ በዚች ምድር ላይ ነገሮችን አይሰራምያለ ሰው ተሳትፎ የሚሠራ ቢሆን ኖሮ ምድር ልክ እንደሰማይ እንከን አልባ ሰላም የሰፈነባት ትሆን ነበርሰዎች ለሰይጣን ሀሳብ ይተባበራሉእግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን ለጨለማው አለም ይማረካሉ:እናም ምድር ከበደል ውጭ የሆነ ፍትህ የሰፈነባት: ሕፃናት የተረጋጉና የወደፊት ሕይወታቸው የጨለማ ጥላ የሌለበት ይሆን ነበር

እውቁ ሴሴሽኒስት Daniel #B.Wallace በልጁ ላይ የገጠመውን ከባድ ሁኔታ ተከትሎ፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማሰብ ከጀመረ በሗላ ፡ በሴሴሽኒስታዊ ምልከታ ያያቸውን ክፍተቶች የገመገመበትን ባለ 11 ነጥብ አቋም ውስጥ 1ዱን አለፍ አለፍ እያልኩ ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ( ይህቺን ትርጉም #ኢዮዮሲያስ_ኢዩኤል: ከሚባል ልጅ ወስጄ ነው)

ነጥብ ፩
በእኛ በሴሴሽኒስታዊያን ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር ከሚገባ ግንኙነት በላይ በእውቀት ላይ ማተኮር አለ፥ ይህም በእኛ ዘንድ ለመጽሐፍት አምልኮ (bibliolatry) ዳርጎናል፥ 

ሴሴሽኒስት እንደመሆኔ መጠን.......  ብዙ ጊዜ እንደውም በእግዚአብሔር ሉዐላዊነት ላይ በመነሳት በውስጤ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነት ካለኝ ግንዛቤ የተነሳ ለሌሎች አልጸልይም። “የሚሆነው ነገር ሁሉ መሆን ያለበት በመሆኑና የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለማስቀየር አንድም ነገር ማድረግ አልችልም*።” እላለሁ። 👉ጸሎት ያለመጸለይ ጉድለታችንን በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ እናላክካለን••• የአንዳንድ ካሪዝማዊያን ችግር የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት መተላለፍ ሲሆን የአንዳንድ ሴሴሽኒስታዊያን ችግር ደግሞ የእግዚአብሔርን መልካምነት አልያም መቻል መካድ  ነው። ሁለቱም ቡድኖች ለእግዚአብሔር ሀቀኞች አይደሉም። ሁለቱም በእግዚአብሔር በታማኝነት የሚታዘዙ አይደሉም። ይለናል !

ጳውሎስ በሥራ መፅደቅ በመፈለጋቸው ወደ ትክክለኛ ፅድቅ መድረስ ስላልቻሉት በሥጋ ዘመዶቹ ለሆኑት እንዲህ ብሎ ነበር👉በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና
  — ሮሜ 10፥2
በዚህም ዘመን ለእግዚአብሔር የቀኑ እየመሠላቸው ያለ እውቀት የሆነ ቅናት የሚቀኑ አማኞች: ቅናታቸው ያለ እውቀት በመሆኑ መቼውኑም ትክክል ወደ ሆነውና ወደሚለውጠው እውቀት መድረስ አይችሉም

ሰማይ ከራሱ ከሥርዓት ውጭ እንደማይንቀሳቀስ ባለማወቅ ዛሬ በአለም ላይ የምናየውን መዐት ሁሉ እግዚአብሔር ለቅጣት በሰው ልጅ ላይ ያወረደው ቁጣ እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩ አሉእነዚህ ግን የእግዚአብሔር የመቅጫ መሣሪያዎች ሳይሆኑ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ የተሰጠውን የመግዛት ስልጣን በአግባብ ባለመጠቀምና ብሎም ተፈጥሮን ለመንከባከብ የተቀበለውን ሃላፊነት ባለመወጣት ተፈጥሮ በምላሽ ለሰው ያበረከተችው የአመፅ ውጤቶች ናቸው

መልስ ያለጥያቄ አይታሰብምና ብዙ መልስ የሚሻ ብዙ መጠየቅ ግዴታው ነው። እስኪ ቆሞ ብላችሁ አስቡ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት አትጨነቁ እርሱ እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል: ያለው ጌታ መልሶ "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚል የፀሎት መርሕ ሲያሳይ ..ለማመናፈስና "የዕለት እንጀራ መንፈሳዊ ቃል" ለማድረግ አስቦ አይደለም ! ይልቁኑም በቀን ፍላጎታችን ላይ ያለውን በጎ ፈቃድ ጠይቆ መቀበል እንደሚችል ማሳያ እንጂ።
እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው።”(ኤፌሶን 3፥20)
📌ከምንለምነው አብልጦ ማድረግ ቢችልም ጥያቄአችን አቅርቦቱን ይወስናል

“#እነሆ_በደጅ_ቆሜ_አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥#ወደ_እርሱ_እገባለሁ - - -።”(ራእይ 3፥20) 📌አምላክ የሚያንኳኳው መግባት ስለማይችል ሳይሆን የራሱን ሕግ በራሱ ስለማይጥስ ሁሌም የሰውን ፈቃድ መጠየቁን ማሳያ ነው። እስኪ በጳውሎስ ሕይወት የመጣውን መለኮታዊ ጥሪ አስቡ:እግዚአብሔር የጳውሎስን ልብ በፀጋ ማንኳኳት ጀመረ : አንድ አማኝ በሰማዕትነት(እስጢፋኖስ)እየሞተ ለሚገድሉት ሰዎች ልብስ እየጠበቀ ሳለ: እስጢፋኖስ "የይቅርታ ፀሎት" ሲፀልይላቸው ሰማ። የሆነ ጥያቄ ሳይፈገርበትማ አልቀረም ! እናም ሊገድል ሊያስር ደብዳቤ ይዞ እየተጓዘ እያለ : ክርስቶስ ተገለጠለትና "ከዚህ በኋላ ብትሄድ ውጤቱ ክፉ ነው : ከእኔ ጋር ተስማማ አለው : እናም ጌታ ጳውሎስን አሳመነ" እሺ ብሎ ፈቃዱን ባይሰጠው ስለጳውሎስ ምንም ከዚያ በኋላ የምናውቀው በጎ ነገር ባልኖረ ነበር ። ኢየሱስ አስገድዶት ወይም ተጭኖት ወደልቡ ኃይሉን ተጠቅሞ አልገባም : የፍቅር ኃይሉን ተጠቀመ እናም ጳውሎስ ተሸነፈ። ብፀልይ ባልፀልይ የሚል ድርቃንህን አቁመው ! ለሆኑ ግሩፖች አመለካከት ሳይሆን : ለእግዚአብሔር ተገዛ ዲያብሎስንም ተቃወም !

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351 #ሼር🙏

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

Grace & Truth Ministry

30 May, 04:42


#ትምህርተ_ፀሎት_የቀጠለ_ያለ

የዛሬው መልዕክት በፍፁም ጥሞናና ረጋ ባለ ልብ እዩት #አመሠግናለሁ🙏

"- - - ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩበሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ- -ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁንየዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።" (ማቴዎስ 6፥8-11)

እግዚአብሔር ሳንለምን  የሚያስፈልገንን ካወቀ እንዲሰጠን መጠየቁ ለምን አስፈለጊ ሆነ?: እግዚአብሔር ሁሉን የሚቆጣጠርና ያለ እርሱ ፍቃድ ምንም የማይሆን ከሆነ የእኛ መፀለይ ምን ፋይዳ አለው? : የእኛ ፀሎት እግዚአብሔርን አይጠመዝዘው ብንፀልይ ባንፀልይ ያለ እርሱ ምንም አይሆንምና የመፀለይ ትርጉሙ ምንድነው?: ይኼ ጥያቄ እርሱ ሁሉን ይቆጣጠራል ያለ እርሱ ፈቃድ ምንም አይሆንም የሚል ፅንፍ የወጣ የሴሺኒስታውያን አቃንቃኞች ምጥ ነው። #ወደ_እውነታው_እንሂድ ➙ እየሆነ ያለው እግዚአብሔር ያለው ብቻ ነውን? : እግዚአብሔር ያለው ብቻ የሚሆን ቢሆን ኖሮ መፅሐፍ ቅዱስ ማጥናት*፣ ፀሎት መፀለይ፣ በአዕምሮ መታደስ ሆነ ቤተክርስቲያን መሄድ ባላስፈለገን ነበር። "እግዚአብሔር ያለው ብቻ ነው የሚሆነው" የሚለው አረፍተ ነገር በሀይማኖት ቤት ውስጥ ያለ: የፀሎትየመሰጠት ነገርህን የሚመታ አደገኛ አደንዛዥ አመለካከት ነው

በምድር ላይ እግዚአብሔር ካለው ውጪ ብዙ ይሆናልለምሳሌ አንተ ያልከው ይሆናልእግዚአብሔር በህይወትህ ለማድረግ የፈለገውን ትተህ በምኞትህ ሙጭጭ ካልክ ለምኞትህ ይተውሃል እንጂ ፍቃድህን ጥሶ ሃሳቡን በአንተ ላይ አይፈፅምም

ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር በማይስማማ ሁሉ ላይ የራሱ ወይም የሌሎች ወይም የዲያቢሎስ ሀሳብ ይሆናልበኑሮህ ላይ የሚሆነው አንተ የተስማማህበት እንጂ የተባለው ሁሉ አይደለምየተባለውን ነገር ከተቃወምክ አይሆንም

ብዙ ሰዎች ሰይጣን ህይወታቸው ላይ እየተጫወተ "እግዚአብሔር ያለው ነው የሚሆነው" ይላሉ። በህይወትህ ላይ ያሉ ክፉ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ፈቅዶ እንደሆኑ ማሰብ ማቆም አለብህ: እግዚአብሔር እንድትፀልይና እንድትቃወም እየመራህ ሳለህ : ነገሮችን ሁሉ ወስዶ ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋርና: ከእርሱ ፅንፍ ከወጣ ሉአላዊነት ጋር ማገናኘት: ላለመለወጥና ለመሸነፍ ለውድቀትህም ምክንያት ነው

ሁሉም መጥፎ ነገር እየደረሰብህና በጫና ውስጥ እያለፍክ: ከእግዚአብሔር ነው ብለህ ከመለጠፍህ በፊት ነገሩ የሆነው በምን ምክንያት ነው በማለት መንፈስ ቅዱስን ጠይቅየዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የነገሩን ምንጭና ነገሩን የምታመልጥበት መውጫ ቀዳዳውን ይነግርሃል

እግዚአብሔር ላለው ነገር ራስህ ዝቅ ስታደርግ ያለው ይሆናልፈቃዱን ስትዋሃደው የእግዚአብሔር ነገር አያመልጥህም!!: መክፈቻ ጥቅሳችን ሳትለምኑት የሚያስፈልጋችሁን ያውቃል: የሚያውቅ ከሆነ መፀለዩ ለምን አስፈለገ የሚል ነበር? : የዛ ንግግር አንኳር መልዕክት ከመፀለያችሁ በፊት ፍላጎታችሁን በቃላት ከማሰረዳታችሁ በፊት እርሱ በሁሉ አዋቂነቱ ያውቃችኋል: ይሄን ማወቃችሁ ልባችሁን ለምስጋናና ለእምነት ያነሳሳዋል ... እንዲህ ካልሆነ መልሶ በሰማይ ያለው ፈቃዱ በምድር እንዲሆን ፀልዩ ማለቱ ምን ፋይዳ አለው?: እርሱ ሁሉን ለልጆቹ ያውቅ የለ?..ይኼ ነገር ሳንጠይቅ አይገባውምን?

እግዚአብሔር በአዕምሮ ታደሱ የሚለን ሀሳቡን በእኛ ላይ ለመፈፀም ምቹ ዞን እንዲፈጠርለት ነውያልታደሰ አዕምሮ የሰይጣን ፍቃድ መፈንጫ ነው ያልታደሰ አዕምሮ የራስ ሀሳብ ባሪያ ነውያልታደሰ አዕምሮ የሰዎች ፍላጎት ተከታይ ነው

እግዚአብሔር ያለው ሁሉ አይሆንም የሚለው እውነታ ክፍ ነገር በድጋሚ ወደ አንተ እንዳይመጣ የምታደርግበት የመጀመሪያው ደረጃ ነውሀሳብህን ለመመርመርዲያቢሎስን ለመቃወም እና መንገድህን እንድትቀይር እድል ይሰጥሀል: ይኼን ማወቅህ የተረጋጋህና ንቁ በፀሎትም የምትበረታ ያደርግሃል #ነገ_ይቀጥላ......
  
ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉@biruk351

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️

Grace & Truth Ministry

28 May, 03:28


#ትምሕርተ_ፀሎት_ባለማቋረጥ_እየቀጠለ_ያለ

ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልባዊና እውነታዊ ጸሎት: ለመንፈሳዊውነት በእውነት ትልቅ ሥፍራ ያለው መሆን አለበት። በሕይወታችን ውስጥ ሁል ጊዜም የእግዚአብሔር ቃል ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዝ መኾን ያለበት ቢሆንም: ጸሎት ደግሞ ከቃሉ ቀጥሎ ሥፍራ ሊኖረው ይገባልከዚህ ባለፈ ደግሞ ቃሉን መረዳት እንችል ዘንድና: በእውነተኛ መታዘዝ ቃሉን በሕይወት መግለጥ እንችል ዘንድ: የእግዚአብሔርን ቃል በጸሎት ማጥናት ያስፈልገናል

በሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል ውስጥ የእግዚአብሔርን ሰዎች መጸለይ እንደሚገባቸው ይናገራሉበጳውሎስ መልእክቶች ውስጥ ደግሞ ጸሎት ምክንያት ተሰጥቶት እናያለንበመልዕክታቱ ውስጥ ለመጸለይ ከመቼውም ጊዜ የላቀ ማበረታቻን እናገኛለን:-  #ይህም “#ሁል_ጊዜ” “#በሁሉም_ነገር” “#ሳታቋርጡ_ፀልዩ፣ አመስግኑ የሚሉ ትዕዛዝ መሰል ምክሮችን እናገኛለን። የጌታችን ሕይወትና ምልልስ፣ #የመጀመሪይቱ ቤተክርስቲያን የፀሎት ትጋት በተለይም የጳውሎስ ሕይወት ለጸሎት ሕይወት ኹነኛ ምሳሌ ነው

የትኛውም ለእኛ የሚያስፈልግ ነገር፣ #የኑሮ_ጭንቀት፣ #ማንኛውም_ህመም #የጸሎት_ሕይወትን_ይሻል። ለእያንዳንዱ ፈተናለእያንዳንዱ ተግዳሮት እና ለእያንዳንዱ ድል: ምሪትንና ፀጋን ለመታጠቅ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያስፈልገናልስለዚህ እንደ ክርስቲያን የፀሎት ሕይወት አስፈላጊ መሆኑ አያጠራጥርም!

#ሆኖም_ግን_ረጅም_ሰዓት፣ ብዙ ቀናትን መጸለይ ወይም በጸሎት ብዙ ሳምንታትን ማሳለፍ በራሱ የእውነተኛ መንፈሳዊነት ማረጋገጫ ሊሆን አይችልምብዙ ሥጋውያን በክርስቶስ ሕፃናት የሆኑ ክርስቲያኖች፣ #እንዲሁም_ሃይማኖተኞች_ፈሪሳውያን እና ሌሎች ያልዳኑ ሰዎችም በጸሎት ብዙ ጊዜን ያሳልፋሉነገር ግን እውነተኛው መንፈሳዊ አማኝ ከሐዋርያው ​​ጳውሎስ አሳብ ጋር የሚተባበር ነው። #ይህም “በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ” (1ቆሮ. 14፡15) ከሚለው ቃል ጋር ማለት ነው።

“#በመንፈስ_እጸልያለሁ” ማለት በቅንነት፣ በተሰጠኝ አዲስ ቋንቋ በጋለ ስሜት፣ አምልኮቴን፣ ልመናዬን እና ምስጋናዬን ለእግዚአብሔር ማፍሰስ ማለት ነው። “#በአእምሮ_እጸልያለሁ” ማለት ደግሞ በማስተዋል፣ በጥበብ፣ በአግባቡ የቅዱሳት መጻሕፍትን መልእክት በመረዳት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን እንደሚሉ በግልፅ በመረዳት እጸልያለሁ ማለት ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ደግሞ በጸሎት ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚነግሩን እና ለጸሎት ሕይወት የሚያስፈልገንን የእግዚአብሔር ጸጋ መቅዳት የምንችልባቸው ናቸው

ስለዚህ ጸሎት በመፈስም በአእምሮም መሆን አለበትበመንፈስ ብቻ ካልን ብዙውን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንስታለንበአእምሮ ብቻ ደግሞ ካልን እውቀት ብቻ ይሆንብን እና የእግዚአብሔርን ሕልውና እንዘነጋለንሁለቱን በሚገባ አጣጥሞ መሄድ ግን ከአንድ መንፈሳዊ ክርስቲያን የሚጠበቅ ተግባር ነው

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️

Grace & Truth Ministry

26 May, 11:05


#ተፈቃሪዋ_ጎሜር
ወጣቱን ነብይ እንዴት አመንዝራይቱ ጎሜር አፍቅሮ እንዲኖር: እግዚአብሔር አዘዘ?.... በዛ ውስጥ እውነተኛው የእግዚአብሔር ፍቅር ለእኛ ምን ያስረዳናል? ሕይወት ለዋጭ ቃል ሳያደምጡ ሼር አያድርጉ🙏

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351

Grace & Truth Ministry

24 May, 15:33


ትምሕርተ-ፀሎት የቀጠለ ያለ   

#መልካም_እና_ደስ_የሚያሰኝ_ጸሎት

ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት መልዕክት ውስጥ  እንግዲህ በቤተክርስቲያን አስቀድሞ ከሁሉ በፊት ለነገስታት ለባለ ስልጣናትና ለሰዎች ሁሉ ልመናና ጸሎት ምልጃና ምስጋና እንዲደረግ አሳስባለሁ ይለዋልለነገስታት እና ለባለ ስልጣናት ጸሎትና ምልጃ መደረግ ያስፈለገበት ምክንያት 
እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ነው ይለናል።(1ኛጢሞ2:4)

#በአዲሱ_መደበኛ_ትርጉም_በእውነተኛ መንፈሳዊ ህይወትና በቅድስና ሁሉ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው ይለናልስለሰዎች ሁሉ ምልጃና ጸሎት በቤተክርስቲያን መደረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ደግሞ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ነው

አንዳንድ ጊዜ እንደ አገልጋይ ክርስቲያኖች የተወሳሰበን ነገር ይዘው እንድትጸልዩላቸው ወደ እናንተ ሲመጡ ተቀብሎ ማስተናገዱ በጣም አሰልቺ ይሆናልብዙውን ጊዜ እንደዚህ አይነቶቹ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ውስጥ (#የቅዱሳን_ሕብረት) ረዘም ላለ ሰአት ወደሚደረገው የጸሎት ፕሮግራም መጥተው ስለራሳቸው እንዲጸልዩና መጸለይን እንዲለማመዱ ሲጋበዙ በፍጹም መገኘትን አይፈልጉምስለራሳቸው ከመጸለይ  በሚመጣባቸው ችግር ውስጥ መውደቅን  ይመርጣሉ
በምታናግሯቸው  ጊዜ ደግሞ የምትነግሯቸውን ነገር ከማድመጥ ይልቅ እንደ ህጻን የራሳቸውን ጩኸት ብቻ ደጋግመው መጮህ ነው የሚፈልጉትጸ ል ይ ል ኝ... ጸ ል ይ ል ኝ : ለራሳቸው ከመጸለይ ይልቅ ለምን እንደዚህ አይነቱን መንገድ እንደሚመርጡ አይገባኝም

እንደዚህ አይነት ክርስቲያኖች : አይደለም ስለ ባለስልጣናት እና ስለ ሰዎች ሁሉ ምልጃና ጸሎት ሊያደርጉ ይቅርና እነርሱ በሌሎች ሰዎች ጀርባ ላይ ታዝለው ወይንም ሌሎች ሰለ እነርሱ እየጸለዩላቸው መኖርን ነው የሚፈልጉት

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ሌሎች እንዲጸልዩልን ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ራሳችን መጸለይ እንዳለብን ከራሳችንም አልፈን ለነገስታት ለባለስልጣናትና ለሰዎች ሁሉ እንድንጸልይና ወደ እንደዚህ አይነቱ የጸሎት ሕይወት እንድንመጣ ያስተምረናል! በእውነተኛ መንፈሳዊ ህይወት በቅድስና ሁሉ በሰላምና በጸጥታ ለመኖር እንዲሁም ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይህ አይነቱ  ምልጃና ጸሎት በቤተክርስቲያን መደረጉ: እጅግ አስፈላጊና ከሁሉ በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
    በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ   ነው 1ኛ ጢሞ 2፥4 ተብሏል።

ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ይኼንን ሊንክ ሁለት ጊዜ ብቻ ይንኩ👉 @biruk351

#ፀጋና_እውነት_ቤተክርስቲያን_ጅማ⛪️
#ሼር_ስለሚያደርጉ_እናመሰግናለን