Bilal Nur

@bilalnur1


#ETHIOPIA

Bilal Nur

21 Oct, 19:03


ሰበር መረጃ ‼️

መርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ እስካሁን አልቆመም።

እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ " በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ተጠንቀቁ 🙏
@bilalnur1

Bilal Nur

21 Oct, 10:18


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

⬇️

የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤




@bilalnur1

Bilal Nur

20 Oct, 08:15


Tiktok creative award  ጥቆማ ተጀምሯል ሰላሳ second አይፈጅም
https://www.tiktokcreativeawards.com
👆 በዚ ከገባችሁ በሁአላ
@bilalnurr     👈ይሄንን link best informative content የሚለው ላይ
ወይም ከላይ በ photo አስቀምጫለው


ከ አንድ በላይ ሰው መጠቆም ይቻላል

Bilal Nur

20 Oct, 08:14


አዲስ አበባ የተፈፀመ

ትናንት ሜክሲኮ ጋር አንዲት እናት ልጇን ይዛ እየለመነች እያለ ደንብ አስከባሪዎች መጥተው ሂጂ ከዚህ ሲሏት እናትም ይሄው ውሰዱት ብላ ልጇን ጥላ መጥፋቷን ሰምተናል።ያሳዝናል ።

ኧረ በልክ አርጉት (Wasu mohhamed)

@bilalnur1

Bilal Nur

18 Oct, 19:50


Tiktok creative award  ጥቆማ ተጀምሯል

https://www.tiktokcreativeawards.com
👆 በዚ ከገባችሁ በሁአላ

@bilalnurr     👈ይሄንን link best informative content የሚለው ላይ


ከ አንድ በላይ ሰው መጠቆም ይቻላል

Bilal Nur

18 Oct, 18:24


Tiktok creative award ጥቆማ ተጀምሯል ዝግጁ

https://www.tiktokcreativeawards.com
👆 በዚ ከገባችሁ በሁአላ
@bilalnurr 👈ይሄንን link best informative content የሚለው ላይ



ከ አንድ በላይ ሰው መጠቆም ይቻላል

Bilal Nur

18 Oct, 17:40


በእምቢታ የፀናችው ወ/ሮ ኩሹ በሽማግሌዎቹ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባት በገመድ ከግንድ ጋር ታስራ በልጆቿ እና በህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ ተደረገ።

ስትገረፍ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ህዝቡ ቁጣውን መግለፅ ጀመረ።

ይህን ውሳኔ አስተላልፏል የተባሉት ሽማግሌዎች ጃርሶ ቦሩ፣ ገልገሎ ጃተኒ፣ ዲዳ ዋሌ፣ ዲዳ ጃተኒ፣ አለካ ጃርሶ፣ ባርጪ ኢያ፣ ዲባ ጎሊቻ የተባሉ ሲሆኑ እነዚህ ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች 5 ቀን ታስረው በዋስትና መለቀቃቸውን ሰምተናል።@bilalnur1

Bilal Nur

18 Oct, 17:33


ሰሞኑን በሀገራችን የተፈፀመ አሳፋሪ ድርጊት‼️
📌"ባለቤትሽ ጋር ለምን አልመለስም አልሽ በማለት ልጆቿና ህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ የተወሰነባት የልጆች እናት"

ጉዳዩ እንዲህ ነው። ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ ምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ቃቀሎ ቀበሌ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ኩሹ ከአቶ ገልገሎ ዋሪዮ ጋር ትዳር ከመሰረቱ 12 አመታት አስቆጥሯል ሶስት ልጆም ወልዷል።
ወ/ሮ ኩሹ ሶስተኛ ልጃቸውን ነፍስጡር ሆነው ባለቤታቸው የሀገር መከላከያ ተቀላቅለው ለግዳጅ 4 አመት ሌላ ቦታ ቆይቷል።
አራት አመታትን ሶስት ልጆችን ብቻቸውን ያሳደጉት ወ/ሮ ኩሹ ከአራት አመታት በኋላ ባለቤታቸው ከመከላከያ ተሸኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ጉዳዩን ያስረዱት የቤተሰብ አባል አቶ ገለግሎ ሲመለሱ የተለያዩ ሱሶችን ስለለመዱ ትዳሩ እንደቀድሞ ሰላማዊ ሊሆን አልቻለም ጭቅጭቅ እና ግጭት ተከሰተ ይላሉ።

ወ/ሮ ኩሹ ትዳራቸው እንዳይፈርስ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ብታስመክርም ባለቤቷ ሊስተካከል ስላልቻለ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ ትሄዳለች።

ይህን ጊዜ ባል ሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ያስጠይቃል፣ ወ/ሮ ኩሹ የእኔ ጉዳት አልታየም በፍፁም አልመስም በማለት የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ውድቅ ታደርጋለች።

ሽማግሌዎቹም የምንልሽን ስሜ ቶሎ ወደ ቤትሽ ተመለሺ ካልሆነ ቅጣት እንጥልብሻለን በማለት ሲያጠነቅቋት እንደቆዩ ተበዳይ ትናገራለች።

@bilalnur1

Bilal Nur

15 Oct, 14:29


ከኮንታ ዞን አስተዳደር የተላለፈ መልዕክት

ስለ አካባቢያችን በተሳሳተና ተገቢነት በሌለ አኳሃን በተለያዩ ሚዲያ አውታሮች የሚደረጉ አሉታዊ ድርጊቶች እንዲቆሙና እንዲታረሙ ከኮንታ ዞን አስተዳደር የተላለፈ መልዕክት

የኮንታ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ሲሆን ዞኑ ከአዲስ አበባ በጅማ በኩል 450 ኪ.ሜ ርቀት ሲኖረው በሰሜን በኩል ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ በምስራቅ ከዳዉሮ ዞን፣ በምዕራብ ከከፋ ዞን እና በደቡብ በኩል ደግሞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ጋር ይዋሰናል፡፡

ኮንታ ከሀገራችን ከሁሉም አካባቢዎች በተለያየ አጋጣሚ የመጡ ብሄር ብሄረሰቦች ያለአንዳች ልዩነት ለዘመናት በሰላምና በፍቅር ተከባብረው በጋራ የሚኖሩባትና ሰርተው ያተረፉባት፣ ኖረው ወልደው የከበሩባት የብዙኃን እናት ናት፡፡

የኮንታ ማህበረሰብ እንግዳ ተቀባይ የሆነ ቸር፣ደግና የዋህ ህዝብ መሆኑን እግር ጥሏቸው ለአንድ ቀን እንኳን ደርሰው የተመለሱ አካላት የሚመሰክሩት እውነታ ነው፡፡

ህዝቡ ሰላም ወዳድ የሆነ፣ከራሱ በላይ ለሌላው ሰላምና ደህንነት አብዝቶ የሚጨነቅ፣ ገራገር የመልካም እሴት ተምሳሌት የሆነ ህዝብ ነው፡፡

አካባቢያችን ኮንታ እንደ ሌሎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ሁሉ የበርካታ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶች የሚገኙበትና በሀገር መሪ አንደበት ጭምር "ኮንታ በምድር ላይ ከስዕል ውጭ ገነት የሚታይበት ምድር"መሆኑ ተመስክሮ ከአካባቢው ተፈጥሮ ጋር የሚሄዱ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እየተገነባ ያለ አካባቢ ናት፡፡
ከማህበረሰባችን መልካም እሴትና ከአካባቢያችን ተፈጥሮ ሀብት ክምችት መነሻ የሀገር መሪዎች የትኩረት ማዕከል በመሆን የገበታ ለሀገር አካል የሆነው የኮይሻ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት፣ የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ የሚገኝበት፣ የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክና በውስጡ የአፍሪካ ግዙፉ ዝሆን መገኛ፣ ከህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ከፍተኛ የሆነና ሲጠናቀቅ 1,860 ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል የኮይሻ ኃ/ኤ/ፓ/ ግድብ ያለበት አረንጓዴና ለምነት ከአመት አመት የማይለየው ውብ አካባቢ ነው፡፡
ኮንታ ስካይ ላይት የመሳሰሉ ትላልቅ የሆቴል ድርጅቶች የሚገኙበትና የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ዓመቱን ሙሉ የሚመላለሱበት የቱሪስት መዳረሻ የሆነ ከባቢ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንድ የአካባቢያችን አርሶ አደር በቃላት አገላለጽ ጉድለት መነሻ የተላለፈው መልዕክት በተሳሳተ መንገድ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥቶ ብዙዎች ሲቀባበሉ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይህ ግለሰብ በጫካ ውስጥ ያገኛቸውን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን መንገድ እንዳይጠፋባቸውና ዝሆንና ሌሎች የዱር እንስሳትን ማግኘት የሚችሉበትን ትክክለኛ አቅጣጫ ቃላት እያጠረው በየዋህነት "በዚህ ከሄዳችሁ ኮንታ ትገባላችሁ" ያለውን ንግግር ከአውድ ውጪ በመውሰድ ተገቢነት በሌለውና በተሳሳተ መንገድ በማሰራጨት የአካባቢያችንና የህዝባችን መልካም ስም እንዲጎድፍና አካባቢው በመጥፎ እንዲቀረጽ ምክንያት እየሆነ መሆኑን ታዝበናል፡፡

የዚህ ግለሰብ የዋህነት የተሞላው ንግግርና አገላለጽ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ባህልና አስተሳሰብ በመልካምነትና በአውንታ ተወስዶ መገለጽ ሲገባው ስለአካባቢው በቂ መረጃ በሌላቸው አካላት ዘንድ ጥርጣሬን ፈጥሯል፡፡

አሁንም በተሳሳተ ትርክት የመጥፎ ነገር ምሳሌ ሆኖ በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ሲገለጽ ይስተዋላል፡፡

ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው በመላው ዓለም ተደራሽነት ያላቸው እንደነ ኢ.ቢ.ኤስ(ebs) የመሳሰሉ ትላልቅ ሚዲያዎችና አንዳንድ ማስታወቂያ የሚሰሩ ድርጅቶች ጭምር ይህን የግለሰቡን አገላለጽ የሚዲያ ፕሮግራማቸውና የማስታወቂያቸው ማጣፈጫ አድርገው ሲጠቀሙ ማየት እጅግ ያሳዝናል፡፡
ኢ.ቢ.ኤስ ብዙ ሚሊዮን ተመልካች ያለውና ስሜ ጥር ሚዲያ ሆኖ ሲያበቃ እንዲህ አይነት የአንድን አካባቢና ህዝብ ስም የሚያጎድፍ ድርጊት መፈፀሙ ያሳዘነው የኮንታን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለተመልካቹም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር የሌለው መሆኑን ያሳያል፡፡

የትኛውም ሚዲያ ለሚዲያ ፍጆታ የሚጠቀማቸውንና ለህዝብ የሚያስተላልፈውን የድምጽም ሆነ የምስል መረጃ በይዘትም ሆነ በአገላለጽ ከማህበረሰቡ ባህል፣ታሪክ፣ቋንቋ፣ ሞራል፣ ስብዕናና እሴት ያላፈነገጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለበት በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ያስገድዳል፡፡

በመሆኑም በዚህም ሆነ በሌሎች መመዘኛዎች ለህዝብና ለሚዲያ በማይመጥን፤ የአንድን አካባቢ ስም በሚያጠለሽና ተገቢነት በሌለው አኳሃን በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን በቀን 03/2/2017 ዓ/ም እሁድን በኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራም በጋዘጠኞች "በዚህ አትህዱ፤ በዚህ ከሄዳችሁ ኮንታ ትገባላችሁ" የሚል አሳፋር ድምጽ ተደጋግሞ ሲተላለፍ ተደምጧል፡፡

የትኛውም ጋዜጠኛም ሆነ የሚዲያ ባለሙያ ለአድማጭ ተመልካቹ ማድረስ ያለበትን ቃላትም ሆነ መልዕክት ጠንቅቆ ማወቅና መረዳት ግዴታ ሆኖ ሲያበቃ እንዲህ አይነት አንድን ህዝብ በሚያንቋሽሽና ለሌላውም የተሳሳተ መረጃና መልዕክት በሚያስተላልፍ አኳሃን የሚዲያ ፕሮግራም መስራት ህገ ወጥነት መሆኑን አበክረን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ስለዚህ የኢ.ቢ.ኤስ. ቴሌቪዥን ጣቢያ የተሳሳተ መልዕክት በማስተላለፍ የአካባቢውን ስም ከማጉደፍም ባለፈ ስለአካባቢያችን በቂ መረጃ በሌላቸው አካላት ዘንድ ብዥታ የፈጠረ በመሆኑ በራሱ ሚዲያ መልሶ የማረምና ህዝባችንንም በግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ ጉዳዩ በህግ አግባብ እንዲታይ ለማድረግ የምንገደድ መሆኑን እየገለጽን ሌሎችም ተቋማትና ግለሰቦች ባለማወቅም ሆነ በቀልድ አልያም ለገንዘብ ማግኛ ተብሎ ስለአንድ አካባቢ የተሳሳተ መልዕክት ማስተላለፍ ከሞራልም ሆነ ከህግ አንፃር ተገቢ ባለመሆኑ እንዲቆም አጥብቀን እንገልፃለን፡፡

Bilal Nur

09 Oct, 18:43


#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ
ዲቪ ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።

ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://dvprogram.state.gov/

2,489

subscribers

28

photos

3

videos