መፅሀፍ ቅዱስ

@bible_only


17 እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 10 :17

" ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:7)

@Bible_only
https://t.me/Bible_only

መፅሀፍ ቅዱስ

18 Oct, 04:13


“የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።”
— ምሳሌ 1፥33
“But whoso hearkeneth unto me shall dwell safely, and shall be quiet from fear of evil.”
— Proverbs 1፥33 (KJV)

መፅሀፍ ቅዱስ

14 Oct, 15:02


ኤፌሶን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።
⁵ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።
⁶ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።
⁷ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።
⁹ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
¹⁰ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
Ephesians 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ According as he hath chosen us in him before the foundation of the world, that we should be holy and without blame before him in love:
⁵ Having predestinated us unto the adoption of children by Jesus Christ to himself, according to the good pleasure of his will,
⁶ To the praise of the glory of his grace, wherein he hath made us accepted in the beloved.
⁷ In whom we have redemption through his blood, the forgiveness of sins, according to the riches of his grace;
⁸ Wherein he hath abounded toward us in all wisdom and prudence;
⁹ Having made known unto us the mystery of his will, according to his good pleasure which he hath purposed in himself:
¹⁰ That in the dispensation of the fulness of times he might gather together in one all things in Christ, both which are in heaven, and which are on earth; even in him:

መፅሀፍ ቅዱስ

07 Oct, 15:45


ማቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴-¹⁶ በነቢዩም በኢሳይያስ፦ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።
¹⁷ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።
¹⁸ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
¹⁹ እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
²⁰ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
Matthew 4 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ That it might be fulfilled which was spoken by Esaias the prophet, saying,
¹⁵ The land of Zabulon, and the land of Nephthalim, by the way of the sea, beyond Jordan, Galilee of the Gentiles;
¹⁶ The people which sat in darkness saw great light; and to them which sat in the region and shadow of death light is sprung up.
¹⁷ From that time Jesus began to preach, and to say, Repent: for the kingdom of heaven is at hand.
¹⁸ And Jesus, walking by the sea of Galilee, saw two brethren, Simon called Peter, and Andrew his brother, casting a net into the sea: for they were fishers.
¹⁹ And he saith unto them, Follow me, and I will make you fishers of men.
²⁰ And they straightway left their nets, and followed him.

መፅሀፍ ቅዱስ

29 Sep, 08:55


ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
³⁰ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።
Romans 8 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ And we know that all things work together for good to them that love God, to them who are the called according to his purpose.
²⁹ For whom he did foreknow, he also did predestinate to be conformed to the image of his Son, that he might be the firstborn among many brethren.
³⁰ Moreover whom he did predestinate, them he also called: and whom he called, them he also justified: and whom he justified, them he also glorified.

መፅሀፍ ቅዱስ

20 Sep, 05:39


መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።
³ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
⁵ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።
⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
Psalms 91 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ He that dwelleth in the secret place of the most High shall abide under the shadow of the Almighty.
² I will say of the LORD, He is my refuge and my fortress: my God; in him will I trust.
³ Surely he shall deliver thee from the snare of the fowler, and from the noisome pestilence.
⁴ He shall cover thee with his feathers, and under his wings shalt thou trust: his truth shall be thy shield and buckler.
⁵ Thou shalt not be afraid for the terror by night; nor for the arrow that flieth by day;
⁶ Nor for the pestilence that walketh in darkness; nor for the destruction that wasteth at noonday.
⁷ A thousand shall fall at thy side, and ten thousand at thy right hand; but it shall not come nigh thee.
⁸ Only with thine eyes shalt thou behold and see the reward of the wicked.
⁹ Because thou hast made the LORD, which is my refuge, even the most High, thy habitation;
¹⁰ There shall no evil befall thee, neither shall any plague come nigh thy dwelling.
¹¹ For he shall give his angels charge over thee, to keep thee in all thy ways.
¹² They shall bear thee up in their hands, lest thou dash thy foot against a stone.
¹³ Thou shalt tread upon the lion and adder: the young lion and the dragon shalt thou trample under feet.
¹⁴ Because he hath set his love upon me, therefore will I deliver him: I will set him on high, because he hath known my name.
¹⁵ He shall call upon me, and I will answer him: I will be with him in trouble; I will deliver him, and honour him.
¹⁶ With long life will I satisfy him, and shew him my salvation.

መፅሀፍ ቅዱስ

11 Sep, 04:18


1ኛ ጴጥሮስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።
³ የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
1 Peter 4 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ Forasmuch then as Christ hath suffered for us in the flesh, arm yourselves likewise with the same mind: for he that hath suffered in the flesh hath ceased from sin;
² That he no longer should live the rest of his time in the flesh to the lusts of men, but to the will of God.
³ For the time past of our life may suffice us to have wrought the will of the Gentiles, when we walked in lasciviousness, lusts, excess of wine, revellings, banquetings, and abominable idolatries:

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
በአዲሱ አመት ዘመናችን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የምንኖርበት አመት ይሁንልን።
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

መፅሀፍ ቅዱስ

28 Aug, 05:31


“ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።”
— ሮሜ 13፥11
“And that, knowing the time, that now it is high time to awake out of sleep: for now is our salvation nearer than when we believed.”
— Romans 13፥11 (KJV)

መፅሀፍ ቅዱስ

25 Aug, 12:23


ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።
³⁹ ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።
⁴⁰ ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።
⁴¹ ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥
⁴² የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።
Luke 10 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ Now it came to pass, as they went, that he entered into a certain village: and a certain woman named Martha received him into her house.
³⁹ And she had a sister called Mary, which also sat at Jesus' feet, and heard his word.
⁴⁰ But Martha was cumbered about much serving, and came to him, and said, Lord, dost thou not care that my sister hath left me to serve alone? bid her therefore that she help me.
⁴¹ And Jesus answered and said unto her, Martha, Martha, thou art careful and troubled about many things:
⁴² But one thing is needful: and Mary hath chosen that good part, which shall not be taken away from her.

መፅሀፍ ቅዱስ

21 Aug, 16:16


ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
²⁷ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
²⁸ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
²⁹ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
³⁰ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
³¹ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
³² እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
Ephesians 4 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ Be ye angry, and sin not: let not the sun go down upon your wrath:
²⁷ Neither give place to the devil.
²⁸ Let him that stole steal no more: but rather let him labour, working with his hands the thing which is good, that he may have to give to him that needeth.
²⁹ Let no corrupt communication proceed out of your mouth, but that which is good to the use of edifying, that it may minister grace unto the hearers.
³⁰ And grieve not the holy Spirit of God, whereby ye are sealed unto the day of redemption.
³¹ Let all bitterness, and wrath, and anger, and clamour, and evil speaking, be put away from you, with all malice:
³² And be ye kind one to another, tenderhearted, forgiving one another, even as God for Christ's sake hath forgiven you.

መፅሀፍ ቅዱስ

14 Aug, 16:46


ዮሐንስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።
² ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
³ እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤
⁴ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።
⁵ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
⁶ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።
⁷ በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።
⁸ ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
⁹ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።
John 15 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ I am the true vine, and my Father is the husbandman.
² Every branch in me that beareth not fruit he taketh away: and every branch that beareth fruit, he purgeth it, that it may bring forth more fruit.
³ Now ye are clean through the word which I have spoken unto you.
⁴ Abide in me, and I in you. As the branch cannot bear fruit of itself, except it abide in the vine; no more can ye, except ye abide in me.
⁵ I am the vine, ye are the branches: He that abideth in me, and I in him, the same bringeth forth much fruit: for without me ye can do nothing.
⁶ If a man abide not in me, he is cast forth as a branch, and is withered; and men gather them, and cast them into the fire, and they are burned.
⁷ If ye abide in me, and my words abide in you, ye shall ask what ye will, and it shall be done unto you.
⁸ Herein is my Father glorified, that ye bear much fruit; so shall ye be my disciples.
⁹ As the Father hath loved me, so have I loved you: continue ye in my love.

መፅሀፍ ቅዱስ

13 Aug, 03:35


ያዕቆብ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።
¹² ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።
¹³ ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር።
¹⁴ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
¹⁵ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።
¹⁶ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
James 5 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ Behold, we count them happy which endure. Ye have heard of the patience of Job, and have seen the end of the Lord; that the Lord is very pitiful, and of tender mercy.
¹² But above all things, my brethren, swear not, neither by heaven, neither by the earth, neither by any other oath: but let your yea be yea; and your nay, nay; lest ye fall into condemnation.
¹³ Is any among you afflicted? let him pray. Is any merry? let him sing psalms.
¹⁴ Is any sick among you? let him call for the elders of the church; and let them pray over him, anointing him with oil in the name of the Lord:
¹⁵ And the prayer of faith shall save the sick, and the Lord shall raise him up; and if he have committed sins, they shall be forgiven him.
¹⁶ Confess your faults one to another, and pray one for another, that ye may be healed. The effectual fervent prayer of a righteous man availeth much.

መፅሀፍ ቅዱስ

08 Aug, 16:16


ያዕቆብ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤
⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
⁹ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
¹⁰ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።
James 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ Submit yourselves therefore to God. Resist the devil, and he will flee from you.
⁸ Draw nigh to God, and he will draw nigh to you. Cleanse your hands, ye sinners; and purify your hearts, ye double minded.
⁹ Be afflicted, and mourn, and weep: let your laughter be turned to mourning, and your joy to heaviness.
¹⁰ Humble yourselves in the sight of the Lord, and he shall lift you up.

መፅሀፍ ቅዱስ

04 Aug, 16:36


ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
John 14 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ Let not your heart be troubled: ye believe in God, believe also in me.
² In my Father's house are many mansions: if it were not so, I would have told you. I go to prepare a place for you.
³ And if I go and prepare a place for you, I will come again, and receive you unto myself; that where I am, there ye may be also.

መፅሀፍ ቅዱስ

28 Jul, 12:46


ኢሳይያስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤
²⁰ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
Isaiah 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ If ye be willing and obedient, ye shall eat the good of the land:
²⁰ But if ye refuse and rebel, ye shall be devoured with the sword: for the mouth of the LORD hath spoken it.

መፅሀፍ ቅዱስ

27 Jul, 07:33


(አማርኛ 1954)“መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።”
— ዘዳግም 33፥27

(KJV)“The eternal God is thy refuge, and underneath are the everlasting arms: and he shall thrust out the enemy from before thee; and shall say, Destroy them.”
— Deuteronomy 33፥27 (KJV)

መፅሀፍ ቅዱስ

26 Jul, 03:44


(አማርኛ 1954)“የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።”
— ኢያሱ 1፥8

(KJV)“This book of the law shall not depart out of thy mouth; but thou shalt meditate therein day and night, that thou mayest observe to do according to all that is written therein: for then thou shalt make thy way prosperous, and then thou shalt have good success.”
— Joshua 1፥8 (KJV)

መፅሀፍ ቅዱስ

25 Jul, 04:16


(አማርኛ 1954)“ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥14

(KJV)“If ye be reproached for the name of Christ, happy are ye; for the spirit of glory and of God resteth upon you: on their part he is evil spoken of, but on your part he is glorified.”
— 1 Peter 4፥14 (KJV)

መፅሀፍ ቅዱስ

23 Jul, 05:39


“ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥11
“If any man speak, let him speak as the oracles of God; if any man minister, let him do it as of the ability which God giveth: that God in all things may be glorified through Jesus Christ, to whom be praise and dominion for ever and ever. Amen.”
— 1 Peter 4፥11

መፅሀፍ ቅዱስ

20 Jul, 17:20


“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”
— ዮሐንስ 15፥13
“Greater love hath no man than this, that a man lay down his life for his friends.”
— John 15፥13

መፅሀፍ ቅዱስ

19 Jul, 03:57


(አማርኛ 1954)መዝሙር 126
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።
⁶ በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።

(KJV)Psalms 126 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ They that sow in tears shall reap in joy.
⁶ He that goeth forth and weepeth, bearing precious seed, shall doubtless come again with rejoicing, bringing his sheaves with him.