Apostolic generation evangelize

@apogeneva1


Mark16÷15 And he said unto them, Go ye into all the world, and preach the Gospel to every creature.
ማር 16÷15 እንዲህም አላቸው።ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
for any comment
@ApoGenEvaBot @rob_apo

Apostolic generation evangelize

16 May, 09:45


#ቃለ_መጠየቅ

ከቀድሞ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአሁኑ በአለም አቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ የሆኑት ቄስ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ዛሬ ማታ በጽሁፍ ወደ አንባቢዎችና አድማጮች እናደርሳለን።

ይህ ቃለ መጠየቅ ከ10 አመት በፊት በስልጣን ቆይታቸው ውስጥ እያሉ የተጠየቀ ብሆንም ዛሬ ግን በዚህ ሰአት በስልጣን ገበታቸው ላሉት ወንድሞችና እህቶች በጣም ወሳኝ ነው።

ዛሬ ማታ በ2:00 ክፍል አንድን እናቀርባለን።
በማራናታ ተለግራም ቻናል ላይ ይጠብቁን።

JOIN AND SHARE THIS INFORMATION

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

COMMENT፦ @Taddyapostolic

Add members for group @marantawoch

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

16 Feb, 22:42


Music

Apostolic generation evangelize

13 Feb, 04:12


የማለዳ ትምህርት /263/
ቀን 05/06/16 ዓ/ም 49ኛ ሳምንት (ማክሰኞ)

ርዕስ፦ #ተፈትነህ_ተሻገር

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ። በየማለዳው ከመሶቡ የማያልቅ የእለቱ የነፍሳችን እንጄራ የሆነውን ጣፋጩ ምግብ እያዘጋጀ ያለው አምላካችን ኢየሱስ ይባረክ እያልኩኝ ለዛሬም አቅዶ ወደ ልቤ ያመጣውን ትምህርት ላካፍላችሁ። እናንተ ምናልባት የት/ት አዘጋጅው አንተ ነህ/የሆነ ሰው ነው/ ብላችሁ ሊታሰቡ ትችላላችሁ፤ እኔ ግን በራሴ የሚያዘጋጀው ት/ት የለኝም፥ እርሱ ከሰጠኝ በስተቀር..... እርሱ ባይረዳኝና ርዕሱ ባይሰጠኝ፣ የቃሉን ፍቺ ባያበራልኝ ኖሮ እኔ ይህን ሁሉ በምን አቅሜ ነው በየቀኑ የሚያቀርበው? ስለ ሁሉ ኢየሱስ ይመስገን።

የዛሬውን ትምህርት፦ "ተፈትነህ ተሻገር" በሚል አርዕስት ላካፍላችሁ። በምድር ላይ እስካለን ድረስ የተለያዩ ፈተናዎችን እናስተናግዳለን። አንዳንዱን በሽንፈት አንዳንዱን በድል እናልፋለን። ለተማሪው በተማረው ትምህርት ፈተና አለው፤ ለአርሶ አደሩም በሚያርሰው እርሻ ፈተና አለው፤ ለመንግሥት ሠራተኛም በሥራው ፈተና አለው፤ እንዲሁም ደግሞ ለጽዮን ጉዞም ፈተና አለው፤ ማሰናከያ አለው። ነገር ግን መፈተን ብቻ ዋጋ የለውም፤ ተፈትኖ መሻገር እንጅ። ተፈትኖ የወደቀው ጎበዝ አይባልም፤ ያለፈው/የተሻገረውን እንጅ። የእገሌ ልጅ ፈተና ተፈተነ ማለት ብቻ አያስደስትም ነገር ግን ከፈተና አልፏል/ ተሻገረ ስባል ነው ሙሉ ደስታ የሚሰማው። ዛሬ ግን በዚህ በትምህርቴ ርዕስ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቼ ላካፍላችሁ የወደድኩት ነገር ብኖር የሰማያዊ መንገድ ፈተና ነው።

የጽዮን/የሰማይ ጉዞ በፈተና፣ በመከራ፣.... በመሻገር የሚገኝ እንጅ በምቾትና በመታደል ብቻ የሚገኝ አይደለም። በእርግጥ በሰማይ ያለንን ተስፋ ስናስብ በጣም ደስታ ይሰማናል፣ ሀሌሉያ ያሰኘናል። ነገር ግን ያንን ደስታ ለመካፈል የተለያየ የሚያጋጠሙንን ፈተናዎች በትዕግስት አሸንፎ መሻገር ይጠበቅብናል።

(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 1) 6-7፤ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።

8-9፤ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።

በእምነታችን ላይ ተፈትነን ማለፍ ነገ ለሚናገኘው ድል ተስፋ ይሆንልናል። "በኢየሱስ ክርስቶስ አመንኩ ፤ በስሙ ተጠመቅሁ፣ ፈተና ለምን ይበዛብኛል?" አይባልም፤ እንደውም ኢየሱስን አምነህ፣ በስሙ ተጠመክ ማለት የሰማይ ፈተና ክፍል "ሀ" ብለህ ጀመርክ ማለት ነው። በውጭ ባለህ ሰአት የምን ፈተና ይኖራል? ሁሉም የተፈቀደ አይደል? ይህን አትብላ፣ አትጠጣ፣ አትልበስ፣ አትመኝ፣ አታደርግ የሚል ህግ የት አለና? ውስጥ ስትገባ ግን አረማመድህ፣ አነጋገርህ፣ #ሁሉም_በሰማያዊ_ካሜራ_እይታ_ውስጥ_ነው። Control የሚያደርግህ ባለቤት ተመድቦልሃል። የወርቅ ወርቅነቱ የሚጣራው በእሳት ውስጥ ነው እንጅ ከጭቃው ጋር አይደለም። የክርስቲያን ክርስትናም የሚጣራው በፈተና ነው። የሰማይ ዜጋ ለመሆን እንደተዘጋጀህ የሚጣራው በዛው ነው።

አንዳንዶች ክርስቲያን ፈተና ስበዛባቸው ከስፍራቸው የሚለቀቁ አሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ባህርይ ማወቅ ግድ ይላል። የእግዚአብሔርን ጸባይ አውቆ ማገልገልና መኖር ግድ ነው። መከራን ሳያቀምስ ምቾትን አያስቀድምም፤ ሊያነሳህ ስል ጥሎህ ያያል። በዛው ውስጥ ትዕግስትህን ይመዝናል።

(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 5) 7፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ፥ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።
8፤ እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።

ሊያከብርህ ስል መከራህን ያበዛል፤ ሰው ሁሉ እንድላገጥህ ያደርጋል፤ ከተፈተንክ በኋላ ያላገጠህ ሁሉ እያዬ ከፍ ከፍ ያደርጋሃል። ፈተና ስበዛብህ እንደው ደስ ይበልህ፤ አመስግነው፤ ከፊትህ ክብር ጠብቆሃልና።
Asphalt ላይ ቆሜህ ብቻ ተመስገን አትበል፤ በጭቃ ውስጥ ሆነህም አመስግን። እግዚአብሔር የሚመዘነው ተመችቶህና ተደላድሎህ ያመሰገንኸውን ሳይሆን በመከራ፣ በችግር፣ በበሽታ፣ በማጣት፣በስቃይ...... ውስጥ ሆነህ ያመሰገንከውን ነው።


(መጽሐፈ ኢዮብ ምዕ. 11) 16፤ መከራህንም ትረሳለህ፤ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።
17፤ ከቅትር ይልቅ ሕይወትህ ይበራል፤ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።

18፤ ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ።

19፤ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል።

መከራ የለም አይመጣብህም አልተባለም፤ አለ ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ትረሳለህ ነው የተባለው እንጅ። ምንም ይሁን ምንም ዋና አላማችን ሰማይ መግባት እስከሆነ ድረስ ፈትኖ ሰማይ ያስገባን። ፈተና መፈተን ብቻ ሳይሆን ተሻግሮ መርሳትም አለ። ነገር ተፈትነህ ብቻ አትውደቅ። በመንፈሳዊ ህይወት ላይ ከባዱ ነገር ተፈትኖ መውደቅ ነውና። እስራኤል 600,000 በላይ የሆኑ ሰዎች ከግብፅ በወጡበት ቀን አልወደቁም፣ ነገር ግን በመንገድ ላይ እየተፈተኑ አንድ በአንድ ወደቁ እንጅ።

እንኳን እኛ ደካማ ሰወችና ኢየሱስ እራሱ በሰይጣን ተፈትኖ አልፏል። እርሱ አምላክ ስለሆነ አሸነፈ፤ እኛ ግን ሰዎች ነን በምን እናልፋለን? አቅም የለንም ሊንል እንችላለን። ግን ፈተና ስመጣ በአንድ በኩል ደግሞ ከፈተና ጋር መውጫ የሚያዘጋጅልን አምላክ ሁል ጊዜ ከጎናችን አለ።

" ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።" (1ኛ ቆሮ10:13)

አትዘነጉ ፈተናም አለ፤ መውጫም አለ። እንደ ግያዝ የፈተና ከፍታና ብርታት ብቻ አትመልከቱ። ከፈተናችን የሚበልጥ ኢየሱስ ከጎናችን አለ፤ አይዞ ልጆቼ ከጎናችሁ ነኝ እያለ።
ሰይጣን ያኔ ለኢየሱስ ያዘጋጀው ፈተና ዛሬ ለእኛም እያዘጋጀ ይገኛል። ከፈተናዎቹ ጥቅቱ፦
📌 ረሃብን ያሳያል 📌 ክብርን ያሳያል
📌 ትዕብትን /እውቅናን/ ያሳያል
እነዚህን ፈተናዎች ማለፍ ከቻልን በእውነትም እግዚአብሔር ያዘጋጀልን ስፍራ እንደርሳለን።

እነዚህን ጥቅሶች በጥሞና እንድታነቡ አሳስባችኋለሁ፦
ማቴ 4፥1...... ዘዳግ 8፥3
ማቴ 4፥8......ዘዳ 6፥13
ዛሬም የፈተናው መውጫ እንድያዘጋጅልን እንጸልይ

መልካም ቀን!!!

Apostolic generation evangelize

09 Feb, 04:06


የማለዳ ትምህርት /259/
ቀን 01/06/16 ዓ/ም 48ኛ ሳምንት (አርብ)

ርዕስ፦ አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም
ክፍል አንድ (1)

በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተወደዳችሁ ውድ የአንድ አምላክ ልጆች እና የማራናታ ተለግራም ቻናል ቤተሰብ እንድሁም የማለዳ ትምህርት ተከታዮች ደህና አደራችሁ? በምሕረቱ ተሸክሞን ከቀን ወደ ቀን እያሻገረን ለዛሬ ያበቃን አምላካችን ለዘላለም ይባረክ እያልኩኝ ለዛሬ ወደተዘጋጀው የማለዳ ትምህርታችን አልፋለሁ። የዛሬው የማለዳ ትምህርታችን ከላይ በርዕሱ ላይ እንዳያችሁት " አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም" በሚል ርዕስ ነው።

እንግድህ ይህ ትምህርት ክፍል በጣም ሰፊ ሀሳብ የሚያካትት ብሆንም እኔ ግን በትንሹ ጸጋየ በተረዳሁት መጠን አጠር ያለ ሀሳብ አካፍላችኋለሁ፣ እኔ ትንሽ ሀሳብ ስሰጣችሁ እናንተ ታሰፋላችሁ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ስንመለከት በየዘመናቸው የተጠሩና የተመረጡ ሰወች በቁጥሪቸው መግለጽ ባልችልም በጣም ብዙ ሰወች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። አንዳንዶቹ የተመረጡትን ዓላማ አውቀው ዓላማቸውን የፈጸሙ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ግን በሩጫቸው ላይ ደክመው በመንገድ ወድቀው የቀሩ ናቸው። በመንገድ ላይ የቀሩት ተመርጠው ዕድላቸውን በአግባቡ ያልተጠቀሙ ናቸው። ብሆንም ግን እግዚአብሔር በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያስነሳል። "መርጬ ያነሳው ሰው ጠፍቷልና ከእንግዲህ አላነሳም" አይልም። ምክንያቱም በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ለሕዝቡ ይራራልና።

ተመርጦ እድሉን አለመጠቀምና በመንገድ ላይ መቅረት የተመረጠ ሰው ድርሻ ስሆን እግዚአብሔር ግን በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያነሳል።

ለዚህም በምሳሌነት የኤልያስን ዘመን ስንመለከት፥ ኤልያስ ብቻዬ ቀረሁ፣ የእኔ እድል ይጥፋ፣ ግደለኝ እያለ እየለቀሰ ባለበት ሰአት እግዚአብሔር ግን አትፍራ፣ ገና አንተ ያላወከው ትውልድ አለኝ፣ ብቻህ አይደለህም፣ ይልቅ ሂድና ኢዩን ቀባው ብሎ ስያጽናናው እናያለን።


(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 11)
----------
2፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን?
3፤ ጌታ ሆይ፥ ነቢያትህን ገደሉ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ነፍሴንም ይሹአታል።
4፤ ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።
5፤ እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ።

እንደዚሁም በአሁኑ ዘመናችንም በጸጋ የተመረጡ ቅሬታወች አሉ። ነገር ግን ከባዱ ነገር የተመረጡ ትውልድ መሆናቸውን መዘንጋትና አልባሌ ቦታዎች ጊዜያቸውን ማሳለፍ ነው እንጅ። ማለትም የተመረጡ መሆናቸውን አለማስተዋል እድላቸውን ያጠፋል እንጅ።

አሁን በዚህ ዘመን በየቦታው የሚንሰማው ነገር ስሰለቸንና ሀሰተኞች ነብያት እንደበዙ ስንሰማ፦ ውይ በዚህ ዘመን ኤልያስ ብኖር!!! እንላለን። ነገር ግን ኤልያስ የተዘጋጀውና የተመረጠው ለዚያች ዘመን ነው እንጅ ለዚህ ዘመን አይደለም። ለዚህ ዘመን የተመረጥነው አንተ/ቺ እና እኔ ነኝ። ኤልያስ በዘመኑ ዕድሉን ተጠቅሞ ተዓምራትን ሠርቶ ለኤልሳ አሳለፈ፤ ኤልሳዕም ዕድሉን ተጠቅሞ አለፈ...... አእያለ እያለ ዛሬ ተራው ለእኛ ደረሰ። አንተና እኔ ግን ያኔ እነርሱ የሠሩትን እንተርካለን እንጅ ዛሬ ምን ሠራን?

በ2ኛ ጴጥ 2፥7 ስንመለከት በሎጥ ዘመንም ትውልድ ረከሱ፤ ሎጥ ግን ብቻው ቀርቶ ነፍሱን ያስጨነቅ ነበር። ለዚህ ዘመንም በረከሱት ትውልድ መካከል አንድ የተመረጠ ትውልድ ነፍሳቸውን እያስጨነቁ ያሉ አሉ። ከእነዚህ ከተመረጡትና አላማቸውን ካወቁት ጋር እንድንሰለፍ ኢየሱስ ይርዳን።

ነገር ግን አንድ የሚያሳዝነው ነገር በየዘመኑም እግዚአብሔርን የማያውቅ ትውልድ ይነሳል። ስለዚህ እኛ እራሳችንን ስንፈትሽ በየትኛው ትውልድ ውስጥ ተመድበናል ብለን መጠየቅ ያስፈልገናል። በመሳፍንት ዘመን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው የሠራውን ተዓምራት ያላወቀ ትውልድ ስነሳ እግዚአብሔር ግን ቸር አምላክ ስለሆነ ሌላ መሳፍንት በመካከላቸው ያስነሳቸዋል። የተነሱ መሳፍንቶችም አንዳንዶቹ ዕድላቸውን ተጠቅመው እንደ ሀሳቡ አገልግለው አሳልፈዋሉ፣ አንዳንዶቹ ግን አልተጠቀሙም።


(መጽሐፈ መሳፍንት ምዕ. 2)
----------
10፤ ትውልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባቶቻቸው ተከማቹ፤ ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርን ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ።

11፤ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ።
12፤ ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ።
13፤ እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ።

ዛሬም እኔና አንተ/ቺ የተመረጥን ትውልድ መሆናችንን ብናውቅ ኖሮ ለዚህ ትውልድ መፍትሔ ሊንሆን እንችላለን፣ እድላችንን እንጠቀም። እግዚአብሔር ለዚህ ትውልድ መፍትሔ አድርጎ እንድያስታጥቀን ጸልየን እንውጣ፣ ነገም በዚህ ርዕስ እንቀጥላለን።
መልካም ቀን!!
ነገም በዚህ ርዕስ ይቀጥላል............

በዚህ ማለዳ ትምህርት ላይ መስተካከል አለበት የምትሉት ሀሳብ ጥቆማ አስተያያት ካለ ከታች ባለ ቦት ላይ ማድረስ ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇
@Taddyapostolic
@Uwillnverwalkalone

አይ ኤሄ ይቅርብኝ የሚትሉት ከሆናችሁ እንደአማራጭ ያቀረብንላቸው የማራናታ Group አለ በእሱ ላይ commentachun ማድረስ ትችላላችሁ👇👇👇👇👇👇
@Marantawoch

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

🌻የማለዳ ትምህርት በየማለዳ🌻
🌸የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ🌸

🌼መልካም ቀን!!!🌼
@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

Apostolic generation evangelize

23 Jan, 03:55


የማለዳ ትምህርት /243/
ቀን 14/05/16 ዓ/ም 46ኛ ሳምንት (ማክሰኞ)

አርዕስት፦ "በማለዳ መገስገሳችን ከንቱ እንዳይሆን..... "

በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም የማለዳ ትምህርት ተከታዮች እንደምን አደራችሁ? እግዚአብሔር በምህረቱና በቸርነቱ ጠብቆን ከቀን ወደ ቀን እያሻገረን ለዚህ ቀንም አድርሶናል። ስለ ጥበቃውና ስለ ምህረቱ ለዘላለም ይባረክ እያልኩኝ ለዛሬ የተዘጋጀውን ወደ ጣፋጩ የማለዳ ትምህርታችን ስያልፍ ከላይ እንደተጠቀሰው "በማለዳ መገስገሳችን ከንቱ እንዳይሆን....." በሚል ርዕስ ሀረግ ተነስተን የተወሰነ ነገር እንማራለን ብዬ እገምታለሁ።

በእርግጥ በዚህ በማለዳ ተነስተን ወደተለያዩ ነገሮች እንገሰገሳለን፤ አንዱ ወደ ሥራ ቦታ፣ ሌላው ወደ ት/ቤት ሌላው ወደ ቤተ ክርስቲያን.... ወዘተ ይሄዳል። ነገር ግን ይህ ሁሉ መገስገሳችን በእግዚአብሔር ጥበቃና ፈቃድ ውስጥ ካልሆነ ከንቱ እንደሚሆን የእግዚአብሔር ቃል በግልፅ ይነግረናል።

የእግዚአብሔርን ቃል አንብበን እንመለስ፦

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 127)
----------
1፤ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2፤ #በማለዳ_መገሥገሣችሁም_ከንቱ_ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።"

ውድ አንባቢዎችና የእግዚአብሔርን ቃል ሰምታችሁ የሚትተግብሩ ወንድሞችና እህቶች ከዚህ ቃል ክፍል ምን ተረዳችሁ? እኔም የተረዳሁት ያህል ላካፍላችሁ

ዛሬ በአለማችን ላይ በብዙ ሚሊዬኖች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራዊት የተለያዩ ቦታዎችና ከተማዎች ይጠብቃሉ። በዛውም ልክ የብዙ ሰዎች ደም በየቦታው እየፈሰሰ ይውላል። ታድያ የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች ባሉበት አከባቢም ደም ለምን ይፈሳል? ሠራዊቶች አይጠብቁም ወይ? ልንል እንችላለን። ነገሩ እንዲህ አይደለም። ዋና ጠባቂ እግዚአብሔር ካልጠበቀ ሠራዊት በከንቱ ይተጋሉ። ስለዚህ የእኛ ሠላም ዛሬ ምንም ላይመስለን ይችላል። ነገር ግን የሠላም ዋጋ ሠላም በሌለበት አከባቢ ብበዛ አንድ ሣምንት ያሳለፈ ሰው ያውቃል።

በሌላው በኩል ደግሞ ቅድም ከላይ እንደተጠቀስኩት በማለዳ ተነስተን የተለያዬ ቦታ የተለያዬ ጉዳይ ሊንሄድ እንችላለን። ጉዳያችን ግን እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ካላሳካ በከንቱ መልፋታችን አይቀርም። ስለዚህ በሚንወጣበት፣ በሚንገባበት፣ በሚንሄድበት መንኔ ሁሉ ላይ እግዚአብሔርን ካላስቀደምን መገስገሳችን ከንቱ ነው ማለት ነው።

በነገራችን ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ይቅደም

በየትኛውም ቀን በየማታው የነገ ዕቅድ /plan/ እንይዛለን። የያዝነው plan የሚሳካው እግዚአብሔር አብሮን ካቀደ ብቻ ነው። ስለዚህ በየዕቅዳችን "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" ማለት እንልመድ እንጅ በሥጋ ሰውኛ ብቻ ነገ፣ ነገ፣ነገ፣..... ካልን ውጤቱ ዜሮ ይሆናል። ውጤታችን ፍሬያማ እንድሆን ከፈለግን ግን "የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ..... "እንበል።


(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 4)
----------
13፤ አሁንም። ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።

14፤ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።

15፤ በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።
16፤ አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።
17፤ እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።

እንደውም በጌታ ፈቃድ ሳንል የሚናቅደው እቅድ #በትዕቢታችሁ_ትመካላችሁ ይለናል። እኔ ትዕቢት አላቅም ብንልም እርሱን ባለማስቀድማችን ብቻ ትዕቢተኞች ተባልን ማለት ነው። ስለዚህ በማለዳ መገስገሳችን ከንቱ እንዳይሆን ምን እናደርግ ካላችሁኝ በጸሎታችሁ ሁሉ ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አስቀድሙ እላለሁ። አሁን በዚህ ማለዳ በሚንሄድበት መንገድ ሁሉ አንተ ቅደምልኝ ብለን ጸልየን እንውጣ እያልኩኝ በዚህ የዛሬ ማለዳ ትምህርተን አበቃለሁ። ነገም በሌላ አርዕስት እስከሚንገናኝ መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ።

መልካም ቀን

🙏 በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🙏

🌻 የማለዳ ትምህርት በየማለዳ 🌻
🌼 የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ 🌼

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

የመወያያ ግሩፕ @marantawoch
inbox comment @Taddyapostolic

Apostolic generation evangelize

21 Dec, 14:43


#Callforconference

የሆንሴ ምልኒዬም ኮንፈራንስ promotion

DATE 12-14/04/016
የሆንሴ ምልኒዬም ኮንፈረንስ ለመካሄድ ጥቅት ሰአታት ብቻ ነው የቀረው። ደግሞም ዝግጅቱ እንደተጠናቄቀ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላከታል። በተጨማሪም እኛም በስፍራው ተገኝተን ኮንፈራንስን ለመካፈል ላልቻሉት በተለግራማችን ቻናል በኩል ለበረከቱ ተካፋዮች እንድናደርጋችሁ ወድደናልና እናንተም ከወዲሁ እየተዘጋጃችሁ ጠብቁን።

በእኛ በኩል ያለው ዝግጅት አጠናቅቀናል። ስለዚህ እናንተም ለወንድሞችና እህቶች ሼር በማድረግ ላልሰሙት አሰሙአቸውና በግሩፓችን ላይ add አድርጉ።

ሼር ሼር ሼር

ግሩፓችን @marantawoch በዚህ ላይ add እያደረጋችሁ ጠብቁን
የነገ ሰው ይበለን!!!

አስተያየትና ጥቆማ ካላችሁ @Taddyapostolic ላይ ገብታችሁ ጻፉ

@MARANATHAWOCH

Apostolic generation evangelize

14 Dec, 16:29


#የምስራች

ዛሬ ማታ " የትኛውን pdf ፈልገው አጥቷሉ" የሚል ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

ከዚህ በታች ያሉ pdfoch በእጃችን ስለሚገኝ የፈለጉትን pdf ስሙን በ @MARANTAWOCH GROUP በመላክ መሳተፍ ይችላሉ።

በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ላኩልን። ነገር ግን pdfun የሚንለከው
በ @MARANATHAWOCH ተለግራም በኩል ስለሆነ JOIN አድርጋችሁ ጠብቁን።

ለሌሎችም #SHARE ማድረግን አትርሱ ፤ የፈለጋችሁትንም PDF ጽፋችሁ
በ @MARANTAWOCH GROUP ላይ ላኩልን።

የpdf ስሞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

1, ቃሉ ይናገር፦ በቢሾፕ ተክለማርያም የተጻፈ
2, Eschatology_ finale destiny፦ በቢሾፕ ጌታሁን ላምቤቦ
3, የአንድ አምላክ ልጆች ይለይ፦ በወ/ም ታደሰ ከWCU
4, የመዳን እውቀትን ተቀበል፦ በወ/ም ታደሰ ከWCU
5, ወደ መዳን የሚያደርስ እውነት፦ scanned by camera
6, ህይወት የሚገኝበት መንገድ፦ scanned by camera
7, የስላሴ አመጣጥ፦ በወ/ም ናቲ ከአረካ
8, ጥምቀት በእርግጥ ያድናል
9, የልደት በዓልን ስለ ማክበር መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
10, እግዚአብሔር አንድ ነው።
11, የሥላሴ አማኞች ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች
12, የ666 ምልክቶች
13, የኢትዮጵያ ሐዋርያት ቤተክርስትያን አባላት መመሪያ
14, የማለዳ ትምህርት ከ1-60
15, እውነት እና ምህረት
16, አስተማሪ ትረካዎች
17, መንፈሳዊ ግጥም
18, መንፈሳዊ ወጣት
19, ዘጠኙ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች
20, ኢየሱስን ማን ይሉታል
21, የማለዳ ትምህርት ከ61-120
22, ONLY JESUS ( APK)
23, #የሥላሴ_አጠያየቅ_ምስጥር
24, #የዶክትርን_ትምህርት_እግዚአብሔር_አንድ_ነው
25, #አማላጅ_ማንነው?
26, የማለዳ_ትምህርት_121_200
27, 38 አመት ከአጋንንት ጋር የቆዬ ሰውዬ ታርክ
28, እምነት በእግዚአብሔር ቃል

.
.
.
ከእነዚህ ከ1-28 ካሉት ውስጥ የፈለጉትን በመወያያ ግሩፓችን ላይ አስቀምጡልን

#join & #share

👉 @MARANATHAWOCH
👉 @MARANATHAWOCH

የመወያያ ግሩፓችን @marantawoch ላይ እናወራ

የግል ጉዳይ ካሌ በ @Taddyapostolic ያድርሱልኝ
እስከ 2:30 ድረስ የፈለጉትን ያስቀምጡ

Apostolic generation evangelize

09 Dec, 11:19


Duraan dursa nagaan Waaqayyoo isiniif haa ta'u obboleewwan keenya jechaa, faarfannaa damee lallaba Wallagaa, Gurmuu faarfattoota Yidiidiyaa mat-dureen isaa #NA_TIKSITEETTA jedhu application aposto'ic song jedhu irraa ni argatu, #Code faarsa kanaa immoo karaa kanaanis argachuu dandeessu.

Lakkofsa bilbila
0916201276
0908559506
bilbila or SMS nu dubisaa.

Eebbifamaa!