📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

@allah_is_the_great


የአላህን እዝነት ማግኘት ለምንፈልግ ሁሉ፦
وإذا قرئ القرآن فاستمعوا له وأنصتوا لعلكم
تزكمون
ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ ጸጥም በሉ ይታዘንላችኋልና።(ሡራ አል-አዕራፍ 204)

ቁርኣንን ልብ ሰጥተን በማድመጥ ብቻ የአላህንራሕመት እንላበሳለን አላህ ራሕመቱን ያጎናፅፈን።

🔽 ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት 🔽

@Astaytemaschaabot

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

22 Oct, 11:52


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

21 Oct, 16:44


የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
ችግር ደርሶበት ችግሩን ሰዎች እንዲቀርፉለት በማሰብ ብሶቱን ለሰው ያሰማ፤ችግሩ አይቀረፍለትም።
በጌታው በመመካት ችግሩን አላህ ላይ ያሳረፈ፤ በፍጥነት አላህ የተብቃቃ ሀብት ይሰጠዋል። ወይ ቅርብ ሀብታም ዘመድ በመሞቱ ይወርሳል። አሊያም በፍጥነት ባለፀጋ ያደርገዋል።”ሰሒህ አቢዳውድ (1645)

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

16 Oct, 02:12


ሀቅ ፈላጊ የሆነ ሰው ስህተቱ ሲነገረው አይቆጣም፣ አይሳደብም እንደውም አመስግኖ ይቀበላል


📌قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
🔘ሸኽ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና ይህን ብለዋል።

【الذي يريد الحق يفرح بالنصيحة ويفرح بالتنبيه على الخطأ】
♻️ሀቅን የሚፈልግ የሆነ ሰው፦
🔹ሲመክሩትና
🔹ከስህተትህ ተመለስ ተብሎ ሲነገረው ይደሰታል።
شرح كتاب العبودية (252)

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Oct, 10:36


የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ነው እንደ መንግስት ተሿሚ በተገኘበት ቦታ ለተሰብሳቢው ህዝብ ስብከት የሚያከናውነው። እዚች ሃገር ላይ ሴኩላሪዝም የሙስሊሞችን መብት ለማፈን ሲፈላግ ብቻ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

08 Oct, 04:57


Mishary Rashid al Afasy ( 30 juz )

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Oct, 19:27


◾️የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

➡️ አላህን የሚፈራ፣ ባለው ነገር ላይ የሚብቃቃና እራሱን የሚደብቅ (ዝቅ የሚያደርግ) ሰው አላህ ይወደዋል።

📚(ሙስሊም ዘግቦታል።)

◾️ሸህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

➡️ ነጃ መውጣት (መዳን) የምትፈልግ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ አደራ፦
①) የአላህን ኪታብ "ቁርአን" አጥብቀህ ያዝ
②) ቅናቻውን "የመልእክተኛው መንገድ" ተከተል
③) ቢድአ "በዲን ላይ ጭማሬ" ተጠንቀቅ።

📚 شرح المنظومة الحائية (ص٥٦)

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

04 Oct, 18:18


....የገዳ ስርዓት⁉️

እኛ ሙስሊሞች ነን ገዳው አይጠራንም፡
ይህ አይነት ስርዓት አያካትተንም፡
የአምልኮ ተግባር ከአሏህ ውጭ አይሆንም፡

ያኮረፈ ያኩርፍ ርር ይበል ድብን፡
የጌታችን ቁጣ በላዕ እንዳይወርድብን፡
ከገዳ አስተሳሰብ ከመገለል አለብን፡

የኦሮሞ ጀግኖች ኢስላም ያነፃቸው፡
ከሰማያት በላይ አንድ ነው ጌታቸው፡
አሏህን መገዛት ይህ ነው አላማቸው፡
በዚህም ረገድ ውብ ታሪክ አላቸው፡

ጥቁር ቀይና ነጭ ከለር አናመልክም፡
የፀዳ እምነት አለን ዛፍ አንታከክም፡
አሏህ የፀዳ ነው የለም ጥቁር ጌታ፡
የዚህ ተረት አማኝ ያስቡ ቀጥታ፡

ብርሀን ጨለማ ሁሉን የፈጠረው፡
ለሰውም ለጅንም ጥበብ ያስተማረው፡
ሰወችን ከሌሎች መርጦ ያከበረው፡

ብቸኛው ፈጣሪ አሏህ ነው ጌታችን፡
ጉድለት የለበትም ውቡ እስልምናችን፡
ዋቃ እሚባል ኮተት የለም በዐዕምሯችን፡

ግፍ እየተሰራ በዚህ ሁሉ መዓት፡
የአጋንንት አምልኮ የሸይጦን ግብዓት፡
እንደዚህ ነው ለካ የገዳ ስርዓት⁉️

የኦሮሞ ሙስሊሞች ከዚህ ዘግናኝና የሽርክ ተግባር ተጠንቀቁ‼️

ይህ እጅግ ዘግና ለአዕምሮ የሚከብድ ለመናገር የሚቀፍ ከኢስላም የሚያሶጣ አስተሳሰብ ነው።

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

04 Oct, 08:35


የጁምአ ቀን
~~~~~~~~

ነብዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል ፡ አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም
1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣ 4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ። የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:9_10)

የጁመአ ቀን ሱናወች ~~~~~~~~~~~~~‌
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

‌ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ال

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Sep, 10:18


▪️አዲስ ቆንጆ ምክር


የአላህ ስሞችና መገለጫዎች
የአላህን እውቀት በተመለከተ
የሲህርና የድግምት ሁክም
🔰ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተወስቶበታል

🎙الشيخ سلمان العبادي حفظه الله
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Sep, 20:04


🔹 تلاوة أول سورة الحشر
🔹 القارئ: #عبدالرحمن_الماجد
•••━══❁✿❁══━•••

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Sep, 03:24


◼️የጅሙአ ቀን ሰለዋትን እናብዛ


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
↪️ አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመልእክተኛው ላይ ሶለዋት አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📚(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56)

اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد


http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 23:01


▪️ለወላጆች መልካም ማድረግ‼️
                  
አላህ እንድህ ብሏል:-
♦️ وَٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًۭٔا ۖ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًۭا(النساء ٣٦)
➡️አላህንም ተገዙ። በእርሱም ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች መልካምን ስሩ።(አል ኒሳዕ)

♦️وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍۢ وَفِصَٰلُهُۥ فِى عَامَيْنِ أَنِ ٱشْكُرْ لِى وَلِوَٰلِدَيْكَ إِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ(لقمان ١٤)

➡️ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው። ጡት መጣያውም በሁለት አመት ውስጥ ነው። ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው። መመለሻው ወደኔ ነው። (ሉቅማን 14)

➡️ኢብኑ መስኡድ (ረዲየሏሁ አንሁ)እንዳሉት ለነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ከስራዎች አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ ምንድን ነው? ብዬ ጠየኳቸው ፣

♦️እሳቸውም ሰላትን በወቅቱ መስገድ ከዚያስ ቀጥሎ?ስላቸው ለወላጆች መልካም መዋል አሉ። ከዚያስ ቀጥሎ ስላቸው በአላህ መንገድ ላይ ትግል ማድረግ አሉኝ ።

📚(ቡኻሪ ሙስሊም ዘግቦታል።)

http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 21:27


እንዲህ ነው ነብዩን ﷺ መውደድi
~
ወደው አይደለም በ734 ሂጅሪያ የሞቱት ታጁዱን ዑመር ኢብኑ ዐሊይ አልፋኪሃኒ እንዲህ ያሉት፡-
“ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም በሱናም መሰረት አላውቅለትም። በዲን ላይ ተምሳሌት የሆኑትና የቀደምቶችን ትውፊቶች አጥብቀው የያዙ ከሆኑት የሙስሊሙ ህዝብ ምሁራኖች ከአንዳቸውም ተግባሩ አልተወሰደም። ይልቁንም ቦዘኔዎች የፈጠሩት ቢድዐ ነው። ሆዳ ሞች ያተረፉበት የሆነ የነፍስ ዝንባሌ ነው። ...
ይህ እንግዲህ ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ረቢዐል አወል ወር የሞቱበትም ከመሆኑ ጋር ነው። መደሰቱ በሱ ውስጥ ከማዘን ቅድሚያ የሚሰጠው አልነበረም።” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 04:39


📖ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-
«እውነትን የሚፈልግ በምክር ደስ ይሰኛል፣ ስሕተቱን ሲነገረው ደስ ይለዋል «እንጂ አይከፋም»።"

(ሸርሑ ኪታቢ አል – ዑቡዲያህ (252)

=
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

14 Sep, 16:06


መውሊድ የሙስሊሞች ኢድ አይደለም።

መውሊድ በዲን ላይ የተጨመረ መጤ በአል ነው።

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13620

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 19:39


የ ቲክቶክ ትውልድ

🎙ሸይኽ ኤልያስ አሕመድ

ሁዳ መልቲሚዲያ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 19:18


📻 መውሊድ መቼ ተጀመረ?
🎙ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁ'ላህ

http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 14:57


۞إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُم۞
۞ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ ۞(ቁርአን 49:13)

ያ አላህ! አንተን ከሚፈሩ ባሮችህ አድርገን።💚


http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt