Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

@addismaleda2


Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

09 Feb, 23:24


ሰበር ዜና

የኢትዮጵያ ሳተላይት ኔትወርክ ኢሳን ቲቪ የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ

"ፈጣሪ ይመስገን እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል!"  መሳይ መኮንን ደረጀ ሀብቴ ፋሲል የኔአለም ታማኝ በየነ ሀብታሙ አያሌው እንዲሁም የቀድሞ የኢሳት ቲቪ ሁሉ ጋዜጠኞች አዲስ የተመሰረተ ቲቪ ነው ሰብስክራይብ አድርጉ https://youtu.be/9wzqrEZkMYw?si=ZKc1WJTdCLQuz7Ro

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

07 Feb, 13:34


ኢንፈርህ ሞት !
ሞትን አንፈራውም !
ሰው ሁኑ !
----
የብፁእ አቡነ ጰጥሮስ ምክር ለነወረኛው ሥርዓት!
ለተጨማሪ መረጃ በዚህ መልቀቅ የማይቻሉትን በቴሌግራም አስቀምጠናል
https://t.me/Habtamuayalew10

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Jan, 15:47


Fano fano habtamu ለተጨማሪ መረጃ በዚህ መልቀቅ የማይቻሉትን በቴሌግራም አስቀምጠናል
https://t.me/Habtamuayalew10

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Jan, 15:41


አብይ አህመድ በፋኦ እንደተሸለመ የሚገልጽ ዜና የመንግስት ሚዲያዎችን አጨናንቋል። የሸለመው የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ዜናው ትርጉም ይኖረው ነበር። ለነገሩ እሱም ከኢትዮጵያ ህዝብ አይጠብቅም። ለፍርድ እንጂ ለሽልማት የሚያበቃ ምን ሰራና?! እንዲህ ዓይነቱ ሽልማት መነሻና መድረሻው ይታወቃል። መለስ ዜናዊም የሀገሩን ገበሬ በማዳበሪያ እዳ አሲዞ በኖሮዌይ የማዳበሪያ አምራች ኩባንያ በኩል ዓለምዓቀፍ ሽልማት እንዲያገኝ የተደረገበትን ድራማ እናስታውሳለን።

ከለጋሽ ሀገራት የቀረበን ስንዴ ሰርቆ ለኬኒያና ሶማሊያ ገበያ አስፈጭቶ የሚሸጥ የአብይ አህመድ አገዛዝ በስንዴ የተሳካ ስራ ሰርቷል ብሎ መሸለም ለምን እንዳስፈለገ ይገባናል። 30 ሚሊዮን ህዝብ በተራበባት፥ 5 ሚሊዮን ህዝብ በገዛ ሀገሩ ተሰዶ በየመጠለያው በሚኖርባት፥ የከተማ ውስጥ ረሀብ በተስፋፋባት፥ ድህነት ከምንጊዜውም በላይ በተንሰራፋባት ሀገረ ኢትዮጵያ ለዚህ ሁሉ ክስረትና መከራ የዳረገን ግለሰብ መሸለም የኦትዮጵያን ህዝብ ከመዝለፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ስለኢትዮጵያውያን ኑሮ ፋኦ ምስክርነት ሊሰጥ አይችልም።

እከክልኝ ልከክልህ አስቀያሚው የፖለቲካ ቁማር ዛሬ በልኩ ተገልጧል። አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ጨካኝ፡ አረመኔ፡ ደካማ ሆኖ የሚታወስ ገዢ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ የያየሰው ቴሌግራምን ይቀላቀሉ መረጃ ያግኙ
https://t.me/YayesewShimelis

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

28 Jan, 04:41


በታጣቂዎች መንገድ ላይ “እየተዘረፍን” እና እየተንገላታን ነው ሲሉ ተማሪዎች


በአማራ ክልል ከተለያዩ ስፍራዎች ወደ መቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ የሚገቡ ተማሪች በመንገድ ላይ በታጣቂዎች የሚደረግ ፍተሻ መኖሩንና ተማሪዎች እንዲሁም መምህራን እንዳያልፉ እየተከለከሉ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰምታለች። ለአዲስ ማለዳ ሃሳባቸውን የሰጡ ተማሪዎች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ “ተማሪዎች እና መምህራን እንዲያልፉ አይፈልጉም”።

ከጎንደር መነሻውን ያደረገ ሌላ የመቅደላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪም ደብረ ታቦር ሲደርሱ ከፊት ለፊታቸው በመኪና መንገድ እንደተዘጋባቸው ይገልጻል። “ከተሳፋሪዎቹ መካከል የሱዳን ስደተኞች ሲቀሩ ሌላውን ተሳፋሪ ስልክ፣ ገንዘብ እና ሌሎች ነገሮችንም” እንደወሰዱ ገልጾ ከዛ በኋላ ግን ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን መጓዛቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል።

ተማሪዎች በተለይም ከመካነ ሰላም እና መርጡ ለማርያም አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የመጡ ጥቂት ሲሆኑ፤ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ከመንገድ እንዲመለሱ መደረጋቸውን አዲስ ማለዳ ማወቅ ችላለች።

አዲስ ማለዳ “ታጣቂዎቹ እነማን ናቸው? ምን ዓይነት ናቸው?” በሚል ለተማሪዎች ላቀረበችው ጥያቄ “ማንነታቸውን በእርግጠኝነት መናገር ይከብዳል፤ ነገር ግን ሬንጀር ዩኒፎርም የለበሱም፤ ሲቪሎች እንዲሁም ልብስ ያልበሱ ጭምር አሉ” መኖራቸውን ተማሪዎቹ ያነሳሉ።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ “ተማሪዎች ወደ ተቋማት እንዳይገቡ ብለን ነበር፤ አንድ ዩኒቨርሲቲዎቹ ላይ ችግር ቢፈጠር የምትጎዱት እናንተ ናቹ፤ ለዚህ ነው የምንመልሳቹ” ሲሉ ለተማሪዎች መናግራቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሲመጡ ለደህንነታቸው ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው ተማሪዎቹ እንደሆኑ በይፋ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ጥር 15 ቀን 2016 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በካምፓሱ ያለው ሁኔታ አስጊ በመሆኑም ተማሪዎችን በጊዜያዊ ምደባ ወደ ፖሊ ካምፓስ እንዲዘዋወሩ የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያዝ ወረቀት መለጠፉን አዲስ ማለዳ ከተማሪዎች ብትሰማም ወረቀቱን ዩኒቨርሲቲው አልያም ሌላ አካል ይለጥፈው ማወቅ አልተቻለም።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ለመቀበል ሶስት ቀናት ሲቀረው የአዲስ እና የሬሜዲያል ተማሪዎችን መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ሲገልጽ ለምን እንድተራዘመ የሰጠው ማብራሪያ የለም። በተያያዘ ከቀናት በፊት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ችግር ቢከሰት ሃላፊነቱን አልወስድም ማለቱም አይዘነጋም።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች ከመርጡ ለማርያም ተነስተው ወደ መካነ ሰላም ለመጓዝ ዓባይ ወንዝ ላይ ከባድ ፍተሻ በታጣቂዎች እንደሚከናወን ገልጸው ከመርጡ ለማሪያም ወደ መቅደላ ለመሄድ ሾፌሮችም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

“የተማሪነት መታወቂያ እና የትምህርት ማስረጃ የያዘ ሰው ማለፍ ቀርቶ፣ የሚወርድበት የዱላ መዓት አይጣል ነው” የሚለው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለመጀመሪያ ዓመት ምዝገባ የሚያስፈልገውን የትምህርት ማስረጃ ይዞ በመጓዝ ላይ ነበር። መንገድ ላይ መኪናውን ያስቆሙት ታጣቂዎች ግን ቦርሳውን በመፈተሽ ማስረጃዎቹ በሙሉ ከፊቱ ለፊቱ ቀደው እንደጣሉበት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲ ከደረሰ በኋላ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ መታወቂያ እና ምዝገባ ማካሄድ አትችልም ተብሎ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ መቆየት አትችልም ተብሏል። ይሄው ወጣት፤ ባለው አስቸጋሪ የኢንተርኔት መቆራረጥ ማስረጃውን ከቤተሰብ እንዲላክለት ማድረጉን ጨምሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ታጣቂዎቹ ሾፌሮችን ገንዘብ እንደሚቀበሏቸው የተገለጸ ሲሆን የተወሰኑ መምህራን የሥራ መታወቂያቸውን ደብቀው በነዋሪነት መታወቂያ ማለፍ ችለዋል ተብሏል። ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያቀኑ ተማሪዎች በታጣቂዎች የመታገት፣ የዘረፋ እና ወደመጡበት እንዲመለሱ እየተደረጉ መሆኑን ተማሪዎች ያነሳሉ።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አለመቻላቸው አይዘነጋም።

ሆኖም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአስሩ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ታህሳስ 18 ቀን 2016 አደረጉ በተባለው ምክክር ተቋማቱ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝንን ለማነጋገር ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

በውሳኔያቸው ግን “በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር ይችላሉ” የተባለ ሲሆን ከጥር 1 ቀን 2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጾ ነበር።

ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዎች ለመስራት አስቸጋሪ ስለመሆኑ ለአዲስ ማለዳ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሚኒስቴሩን ውሳኔ የአማራ ክልል ተማሪዎች ማህበር በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር ባለበት እንደቀጠለ መሆኑ እየታወቀ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ይጀምሩ ማለቱ ትክክል አይደለም በማለት ተቃውሞ ነበር።

ከምንም ነገር በላይ የተማሪዎቹን ደህንነት መጠበቅ የሚቀድም በመሆኑ ማህበሩ እንደ ተቋም ከሚኒስቴሩና ከትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር ውሳኔውን ለማስቀልበስ የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቋል።

Via:አዲስ ማለዳ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

27 Jan, 17:31


የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ፣ በግማሽ በጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ካቀደው አጠቃላይ የገቢ መጠን ውስጥ የሰበሰበው ግማሹን ብቻ እንደኾነ አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ 72 ቢሊዮን ብር መኾኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በግማሽ ዓመቱ የሰበሰበው ገቢ ግን 17 ቢሊዮን ብር ገደማንቾ ብቻ እንደኾነ ገልጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተሻለ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም ያስመዘገቡት፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች እንዲኹም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ናቸው ተብሏል።

ቢሮው ዝቅተኛ ገቢ የሰበሰበው፣ በዋናነት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ መኾኑን ጠቅሷል።

@Liyu_Mereja9
@Liyu_Mereja9

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Jan, 15:40


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!

እኛ እዚህ ከተራ መከተር አልቻልም:: በረዶው ዘንድሮ ጠንክሯል::
ለተጨማሪ መረጃ ትክክለኛውን የመሳይ መኮንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ድምፅ ለህዝብ
https://t.me/mesaymekonnen2

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

18 Jan, 14:17


ተመስገን ✈️🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ  ከቀኑ 8:00 መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ

ጎማው አልዘረጋም ብሎ

በፓይለቱ ድንቅ ችሎታ ና በፈጣሪ አማካኝነት ሁሉም ተሳፋሪዎች ያለምንም ጎዳት ና ችግር ከፕሌኑ ውስጥ መውጣት ችለዋል::

ተመስገን 🙏❤️

ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ይመልከቱ
https://t.me/YayesewShimelis

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Jan, 17:21


አስፍሸ እንወድሀለን
https://youtu.be/86SsVgYvbj0?si=8O3_tUSl9phs7UBk

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

16 Jan, 17:21


ነፍስህ በሰላም ትረፍ አስፍሽ ወንድሜ ሁሌም አስታውስሀለው ቃልክን አከብራለው ልጄን አደራ እንዳልከኝ አደራየን እወጣለው ወንድሜ አስፍሽ ሁሌም አስታውስሀለው የኔ መካሪየ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Jan, 17:36


አስፍሸ እንወድሀለን
https://youtu.be/86SsVgYvbj0?si=8O3_tUSl9phs7UBk

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Jan, 15:52


የኢቢኤስ ቤት በሀዘን ተውጧል

የአንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባልደረቦች በስቱዲዮ ተገኝተው ሐዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
ነፍስ ይማር!
ለተጨማሪ መረጃ ትክክለኛውን የመሳይ መኮንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ድምፅ ለህዝብ
https://t.me/mesaymekonnen2

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

14 Jan, 07:31


የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት አስደንጋጭ ዜና ነው። ነፍስ ይማር። በመልካም ስራዎችህ ሁሌም እናስታውስሃለን።
ለተጨማሪ መረጃ ትክክለኛውን የመሳይ መኮንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ ድምፅ ለህዝብ
https://t.me/mesaymekonnen2

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

12 Jan, 09:25


https://youtu.be/XVsQ_OWGqK4?si=5zkqXWLjrn2FV5yD

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

11 Jan, 16:52


Fake news alert 🛑🛑🛑
አቡነ ጴጥሮስ ለሃዋርያዊ ተልዕኮ ወደ አሜሪካ ተጏዙ

የቅዱስ ሲኖዶስ ፀኃፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው  ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ ወደ ሃገረ አሜሪካ ተጉዘዋል
አቡነ ጴጥሮስ ወደ አሜሪካ የተጏዙት በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ መሆኑም ታውቋል የአቡኑ የጉዞ ምክኒያትም በቅርቡ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በሃገረ ስብከታቸው ለማክብር እንደሆነም ታውቋል ::
በማህበራዊ ሚዲያ ከሃገር እንደሸሹ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ እውነትነት የሌለው መሆኑን የአቡኑ የቅርብ ሰዎች ለየኔታ ሚዲያ ገልፅዋል ::
አቡኑ የሃዋሪያዊ ተልዕኳቸውን እንደፈፀሙ ከ ሳምንት በኃላ ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል

ከሃሰተኛ መረጃ ራስዎን ይጠብቁ
ሼር በማድረግ ሌላውንም ይጠብቁ
ለተጨማሪ መረጃ ለመገኘት እንዲሁም ትንታኔዎችን በስዩም ተሾመ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል ታማኝ መረጃ ያግኙ https://t.me/SeyoumTeshome1