የባንኩን ስራዎች ውጤታማነት በዘላቂነት ለማስቀጠል በተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወደ እንቅስቃሴ የተሰማሩ የባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች የለውጡ ግንባር ቀደም አስፈፃሚ ሆነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተገለፀ።
ባንኩ ይህንኑ ስትራቴጂካዊ ውጥን ወደ ዘለቄታዊ ውጤታማነት ለመቀየር ባስቀመጠው አሠራር መሠረት ላለፉት ሁለት ወራት ወደ ተለያዩ ዲስትሪክቶች አሰማርቶ የነበረውን የድጋፍና ክትትል ግብረ-ኃይል አፈፃፀም ሪፖርት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል ገምግሟል፡፡
ቀን 13/6/2017 ዓ/ም አዲስ አበባ
የባንኩን የሥራ ክንውኖች ትርጉም ያለው ውጤት ለማስመዝገብ በሚደረገው የለውጥ አስተዳደር ሂደት በተሰጠው ተልዕኮ ላይ የተሠማሩ አመራሮችና ሠራተኞች ግንባር ቀደም የለውጥ መኮንኖች እንደሆኑ በመገንዘብና ከተለመደው አሠራር ወጣ ያሉ አካሄዶችን በመከተል ለባንኩ ሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት እንዳለባቸው የዕለቱን የውይይት መድረከ የመሩት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ተናግረዋል፡፡
በዘላቂነት የባንኩን የዕድገትና የባለቤትነት ኃላፊነት በተግባር እየተከታተለ ያለው የመንግስት አካልም ለውጡን ይበልጥ ለማስቀጠል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ከባንኩ ጋር በነበረው የጋራ ውይይት ወቅት ውጤታማ ተግባቦት ላይ መድረስ መቻሉን ያስረዱት ፕሬዝዳንቱ ይህንኑ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የለውጡን ግስጋሴ ከወትሮ በተለየ መንገድ መምራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በተለይም በስትራቴጂካዊ ድጋፍና ክትትል ወቅት የተገኙ የመረጃ ግብአቶችን የባንኩን ቢዝነስ ስራዎች ትኩረት በሚመጥን መልኩ ተንትኖ በመጠቀም ዓመቱን በተሻለ ውጤታማነት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ፍጥነት መጨመር ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ወራት በተደረገው ድጋፍና ክትትል ወቅት የተገኙ ድሎችን ማስቀጠልና ችግሮች ላይ ፈጣን የመፍትሔ እርምጃዎችን የመውሰዱን ኃላፊነት እንደሚሰራም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡
በድጋፍና ክትትሉ የተገኙ ተሞክሮችን ለማስቀጠል እና በተለዩ ችግሮች ላይ ፈጣን ምላሾችን ለመስጠት የጋራ አቋም በመያዝ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!