የመጨረሻው የፎርሞች ባህሪ የማይከፈሉ መሆናቸው ነው። በመጨረሻ ፕሌቶ እንዲህ ይላል፦ ፍጹም እውነተኛ ነገር ፎርሞች ብቻ ናቸው። በሌላ አገላለጽ ስለ ፎርሞች ስናወራ እያወራን ያለው ስለ መንፈሳዊው፣ ስለ ረቂቁ አለም ነው።
ፕሌቶ የፎርሞች አለም ብቻ ለምን እውነተኛው አለም እንደሆነ እንዲህ ያስረዳል፦ ለምሳሌ አንድ ትልቅ፣ ክብ፣ ቆንጆ የዝግባ ጠረጴዛ አለ። አንድ ቁስ ክብ ነው የምንለው በክብነት ሲሳተፍ ነው። ስለዚህ አንድን የዝግባ ጠረጴዛ ትልቅ፣ ክብ፣ ቆንጆ የምንለው ትልቅነት፣ ክብነትና ቁንጅና ሲኖሩ ብቻ ነው። ዝግባ የሚባል ፎርም ባይኖር ጠረጴዛው ከነጭራሹ አይኖርም ነበር። ስለዚህ ፍጹም እውነታ የፎርሞች አለም ብቻ ነው—የማይለዋወጥ፣ የማይከፋፈል እና ዘለአለማዊ።
አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ ፈላስፋዎች፣ አሳቢዎች፣ የሂሳብ ሊቆች በሃሳባዊው አለም መመሰጣቸው የራሳቸው ጉዳይ ነው። እኔ በሃሳባዊው አለም አልወሰድም። የኔ ፍላጎት እውነተኛው አለም ነው። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች እውነተኛ አለም የሚሉት አሁን የሚያዩትን፣ የሚሰሙትን፣ የሚዳስሱትን አለም ነው። ፕሌቶ ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፦ "እውነተኛው" አለም እውነተኛው አለም አይደለም። ስለዚህ የፎርሞች ጽንሰሃሳብ ለጥቂት ፈላስፋዎች ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም። ሁላችንንም ይመለከተናል። ምክንያቱም እውነት ብለን ተቀብለነው የምንኖረው አለም እውነት አይደለም።
ፕሌቶ ይሄንን ሃሳብ ሲያጠናክር የትኛውም ውብ የምንለው ቁስ ፍጹም ውብ አይደለም። ሁሌም ውበት ከሚባለው ፎርም አንጻር ያነሰ ውበት ነው ያለው። እውነተኛ ውበት ያለው በፎርሞች አለም ብቻ ነው።
ፕሌቶ እንዲህ ይላል፦ በዚህ አለም ላይ ሁለት ነገሮች አሉ—የመጀመሪያው የተለዋዋጭ፣ ስሜት ሰጪ ነገሮች አለም ሲሆን ይህም የዋሻው አለም ነው። በዚህ አለም ያሉ ነገሮች እንከን የሞላቸው ናቸው። ስህተት፣ ኢሉዥን፣ ድንቁርና የዚህ አለም ተምሳሌቶች ናቸው። በሌላ በኩል የፎርሞች አለም አለ—ፍጹም፣ ዘለአለማዊ፣ የማይለዋወጥ። የእውነተኛ ተፈጥሮና እውቀት አለም ይሄ ነው። እንግዲህ ይህ የፕሌቶ ጽንሰሃሳብ የትኛውንም የእውቀት ዘርፍ ለመረዳት የምንጠቀምበት ነው።
በመጨረሻ ፕሌቶ እንዲህ ይላል፦ ሶስት ፎርሞች ከሌሎች ፎርሞች የላቀ ደረጃ አላቸው—እነሱም ጥሩነት፣ ውበትና እውነት ናቸው። ለምሳሌ ክብነት ውብ ነው ልትሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን ውበት ክብ ነው ልትሉ አትችሉም። ስለዚህ ውበት ከክብነት የላቀ ደረጃ አለው።
የፕሌቶን የፎርሞችን አለም ለመለማመድ ብቸኛው አማራጭ ሜዲቴሽን ነው። በነገራችን ላይ የፕሌቶ ፎርሞች የፕሌቶ ብቻ አይደሉም፤ የሁላችንም እውነታ ናቸው። ፕሌቶን ልዩ የሚያደርገው ይህንን ግዙፍ እውነት ቀድሞ በመረዳቱ ነው። ፕሌቶን ታላቅ ፈላስፋ የሚያሰኘው የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ እውነት የሆነ መሰረታዊ ነገርን መግለጹ እና ሃሳቡን ለመግለጽ እና ለሁላችንም ለማስረዳት የተጠቀመው የዋሻው ተምሳሌት ታላቅ እውነት በቀላል ዘዴ የሚነግር ኃያል ታሪክ በመሆኑ ነው። እንዲህ ናቸው አሳቢዎቻችን ቀድመው መጥተው ቀናውን መንገድ የሚጠርጉልን፣ የእውቀትን ወጋጋን የሚያሳዩን፣ ነቅተው የሚያነቁን ናቸው።
ሶስተኛው የምእራቡ አለም ተወዳጅ ፈላስፋዬ ፍሬድሪክ ኒቼ ነው። የሱን ታላቅ ፈላስፋነት ጉዳይ ለሌላ ቀን ብናሳድረውስ?!
ምስል፦ Allegory of the cave/የዋሻው ምሳሌ
© Te Di