1. የመጾር መስቀል በቅዳሴ እና በማዕጠንት ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን የሚይዘው ነው።
2. የእጅ መስቀል ካህናት ምእመናንን የሚባርኩበት በእጅ የሚያዝ የመስቀል ዓይነት ነው።
3. የአንገት መስቀል ምእመናን በክርስቶስ ያላቸውን እምነት ለማመልከት ከማዕተባቸው ጋር በአንገታቸው የሚያደርጉት ነው።
4. እርፈ መስቀል በማንኪያ ቅርጽ ተሠርቶ በእጀታው ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት ነው። ሠራዒው ዲያቆን በቅዳሴ ጊዜ የአምላካችንን ክቡር ደሙን ስምእመናን የሚያቀብልበት ነው። እንዲሁም ጌታችን በዕለተ ዓርብ የተወጋበት ጦር ምሳሌ ነው።
Abel Mekbib | Official Channel