﷽ዚክረ መንዙማﷺ

@zekr_menzuma


የኛን #You_Tube ቻናል ለማግኝት ይሄን ይጫኑ⬇️👇
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ
@ABD_ABD2 ተጠቅመዉ ያድርሱን✍️
የመውሊድ ሀድራ ቪዲዮ በድምፅ የተቀዳ መንዙማ ያላቹ ላኩልን
{ @ABD_ABD2 }

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

19 Oct, 05:15


ይህ ከጀርመን ጎዳናዎች አንዱ ነው 🇩🇪

ሰዎች ለድሆች እና በልተው ማደር ላቃታቸው ችግረኞች ምግብ በፌስታል አምጥተው ያንጠለጥላ።

ቦታው ላይ ምንም አይነት ይህንን የሚገልጽ ማስታወቂያ የለም: ካሜራም አልተገጠመም: ምግቡን ሲያስቀምጡ እና ችግረኞችም ምግቡን ሲወስዱ አብረን ፎቶ ካልተነሳን የሚላቸው የለም: ሲመገቡ ቪዲዮ እየቀረፀ የሚያጎርሳቸው የለም

ምግቡ ፌስታሉ እና ችግረኞቹ ብቻ ነው የሚተዋወቁት።

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው!!

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

03 Oct, 16:22


ኢሬቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?

እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።

ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።

ገና፣ ፋሲካ በዓል "ቢድዓህ" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ ነው "ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

30 Sep, 03:05


በራስህ ላይ እንዲደርስ የማትፈልገዉን በሌሎች ላይ አታድርግ!!!

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

16 Sep, 12:33


«ሙሐመድ ቢራ🍺» ለምን የለም ? ማለት ጀምረዋል። ቄስ መስሎኝ በጊዮርጊስ ተጉመጥምጦ የሚቀድሰው ! እኛን ካልነካችሁ ለቅሶው አይድምቅም ማለት ነው ?

https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

16 Aug, 09:20


ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂራጂኡን የሱ ነበርን ወደሱም ተመላሽ ነን ትልቅ አጂላ ኡለማ አጥተናል

ማረፊያዎትን ከምትወዷቸው ሰይዳችን ሰለሏሁ አለይሂወሰለም፣ከሰሀቦች፣ከደጋጎችያድርግላችሁ።

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

14 Aug, 12:37


አላህ ማሊኩ ደስ የሚል መንዙማ ዚክረ መንዙማ || ZIKER MENZUMA & NESHIDA TUBE👇👇👇
https://youtube.com/shorts/w9xZn8nuxEM?feature=share
https://youtube.com/shorts/w9xZn8nuxEM?feature=share

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

15 Jul, 10:21


መልዓከ ሞት የዱንያ ቆይታውን ለማገባደድ ጥቂት ሴኮንዶች የቀረውን ፍጡር ከሌሎች ነጥሎ ለመውሰድ ባሻው መንገድ ይመጣል። በዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል የተስተዋለው ክስተት «ሟች እንዲህ ቢያደርግ ኖሮ ይህ አይፈጠርም ነበር» የሚያሰኝ ክፍተት እንደሌለው የሩቅ ምስጢራት ግርዶ ላልተገለጠልን የመሬት ነዋሪዎች መማሪያ ነው። ቀለሙ ተነስቷል ፤ ወረቀቱም ደርቋል።

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

07 Jul, 15:36


ዘይኑ ሀበሻ የሴቶች ሀድራ መንዙማ ዚክረ መንዙማ || ZIKER MENZUMA & NESHIDA TUBE👇👇👇
https://youtube.com/shorts/ytkux4wzBFM?feature=share
https://youtube.com/shorts/ytkux4wzBFM?feature=share

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

15 Jun, 17:41


عيد مبارك
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال وكل عام وانتم بألف خير وصحة وسلامة وعافية
EID MUBARAK🕋 📿

https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

07 Jun, 02:03


ነገ ዙልሂጃ 1 ይጀምራል በፆም ብናሳልፈው ተቆጥሮ ማይዘለቅ አጅር እናፍሳለን ነይተን እንፁመው

ከተቻለ ሁሉንም ቀናት ካልተቻለ የተወሰነውን ካልሆነ ሰኞና ሀሙሱን ካልሆነ የመጨረሻ 2 ቀናትን አላህ ይቀበለን

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

07 Jun, 02:01


ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ጁምዓ  አንድ ብሎ ይጀምራል! የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሰኔ 9 ዕለተ እሁድ እንደሚከበር ታውቋል! አስሩን ቀናት በመልካም ስራ እናሳልፋቸው በዱዋ አንረሳሳ

ኡድሂያ የሚያርድ ሰው ደሞ መከልከል ካለባቸው ነገር እንዲከለከል ለምሳሌ ጥፍር :ጸጉር መቁረጥን የመሳሰሉ ከዛሬ ይጀምራል    የሰማ ላልሰማ ...

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

27 May, 11:51


በሴት አካል ውስጥ 2 ልብ ይገኛል

مَّا جَعَلَ ٱللَّهُ لِرَجُلٍ مِّن قَلْبَيْنِ فِى جَوْفِهِۦ

"አላህ ለአንድ (ወንድ) ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ . . ."

ለምንድነው ቁርአኑ ስለሰው ልጅ እያወራ "ሊበሸሪን (ለሰው ልጅ) 2 ልብ አላደረገለትም" ማለት ሲገባው ሴቷን ትቶ ወንዱ ብቻ በአካሉ ውስጥ 2 ልቦች እንደሌሉት የጠቀሰው?

ሴት 2 ልቦች አሏት ማለት ነው?

በእርግጥ ወንድም ሆነ ሴት አንድ ልብ ብቻ ነው ያላቸው። ነገር ግን ሴት 2 ልብ የምትይዝበት አጋጣሚ አለ። እሱም በእርግዝና ወቅት ሲሆን የእሷንና በሆዷ የሚገኘው የልጇ ልብ።

የቁርአን እንከን አልባነት ገርሞ ይገርማል 💜
በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

22 May, 07:38


የምን ቁንጅና የምን ውበት? የምን የበላይነት የምን ዝና? ሁሉም በዚህ መልክ ይጠናቀቅና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ…
﴿ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَى ﴾

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

12 May, 18:03


#ከንቱ_አለም አጭር አስተማሪ ፊልም
ZIKR MENZUMA & NESHIDA TUBE
https://youtu.be/A0muqg85jN4

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

05 May, 04:37


ያስገረመኝ
`````
አሜሪካ ላይ አንድ እጅግ ታዋቂ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። <አንተ አባት አይደለም!> የሚሰኝ ፕሮግራም ነው።
ፕሮግራሙ እንዴት መሠላቹ?
በፕሮግራሙ አንዲት ሴት ትቀርብና አብረዋት ዚና የፈፀሙ ወንዶችን የምትሞግትበት ነው። በዚህም ወንዶቹ የ DNA ምርመራ እንዲያደርጉና ከውርስ ጋር ያለውን ነገር ለመለየትና የልጇ አባት እንዲታወቅ ይደረጋል።

በጣም የደነገጥኩት ግን አንድ ፕሮግራም ላይ አንዲት ሴት ከ18 ወንዶች ጋር እንደተኛች ስትናገር ነው። የሚገርመው 18ቱም የDNA ምርመራ ቢያደርጉም አንዳቸውም አባት መሆናቸውን የሚያሳይ ውጤት አልተገኘም።
በዚህ የመጣም አባቱን ማወቅ ያልቻለው የ11 አመት ጨቅላ ህፃን በየቀኑ የሚያለቅስ ሲሆን ለከፍተኛ የጭንቀት በሽታም ተዳርጓል።
ፕሮግራሙ ወንዶችንም ያቀርባል ፤ ሚስቶቻቸው <<የልጅ አባት ነህ>> በሚል ለሚያቀርቡት ክስ በባሎች ጥያቄ መሠረት አንዳንድ ሚስቶች ለምርመራ የሚቀርቡ ሲሆን ከነሱም አንዳንዶቹ አጭበርባሪ ሆነው ይገኛሉ።
ፕሮግራሙ ከ1991 ጀምሮ የሚታወቅ ሲሆን በ19 ክብረ በአላት ላይ 3500 የሚሆን ፕሮግራም ያቀርባል። በእያንዳንዱ ፕሮግራም ላይ 3 ባለጉዳዮች ይስተናገዳሉ። (አስቡት የከሳሽ ተከሳሹን /የዛኒዎችን/ ብዛት)😭
አቅራቢ ጣቢያው NBC የሚባል ነው።

ይህ ፕሮግራም አሜሪካውያንና ምዕራባውያን ምንያህል በስነምግባራቸው ውድቀትና በዘር መጥፋት ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን በግልፅ ያሳያል።

እንግዲህ ኢስላምን የሚዋጉት እዚህ የወደቀ ደረጃ ላይ ሊያደርሱን ነው። ኢስላም ለሴት ልጅ መብት የነፈጋት ይመስል <የሴት ልጅ መብት> <የፆታ እኩልነት> እያሉ የሚያደነቁሩን ለዚህ ነው። (አላህ ያደንቁራቸውና)

እንደዚ አይነት ፕሮግራሞች በአሜሪካ የሚገኙ ሴቶች (እናቶች) የልጆቻቸውን ትክክለኛ አባት በማጣት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሚኖሩም ማሳያ ነው።

አላህ ዘርና ክብር እንዲጠበቅ ብሎ ያስቀመጠውን ድንበር በነፃነት ስም እንዲደፈር ማድረግ ድንቁርና እንጂ ሌላ አይደለም።

أُو۟لَٰٓئِكَ كَٱلْأَنْعَٰمِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْغَٰفِلُونَ

እነዚያ (ከሀዲያን) እንደ እንስሳ ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ (ከእንስሳም የባሱ ናቸው)
በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

05 May, 04:37


ያስገረመኝ
```
አሜሪካ ላይ አንድ እጅግ ታዋቂ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። <አንተ አባት አይደለም!> የሚሰኝ ፕሮግራም ነው።👇👇

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

17 Apr, 19:04


ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ።

'ትምህርት እንዴት ነው ?' ስላት ፣ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች'ና እስከአሁን አንደኛ ብቻ እየወጣች እንደሆነ ነገረቺኝ። እናቷ በፈገግታ የምናወራውን ትሰማለች። 'እና ስታድጊ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ?' ስላት ፣ ድንገት እናቷ ፊቷ ቅይርይር አለ። ልጅቷ ላይ ተኮሰታተረችባት። ግራ ገባኝ።

ልጅቷም እያፈራረቀችን በፍርሃት ውስጥ ሆና እኔ'ና እናቷን ታየን ጀመር። 'ምነው ?' አልኳት ለህፃኗ ቀስ ብዬ። 'እናቴ እኔ መሆን የምፈልገውን ነገር አትደግፈኝም...' አለቺኝ ለንቦጯን እየጣለች።

የልጅቷ አይን በእንባ ሲሞላ 'ችግር የለውም ንገሪው በቃ እኔኮ ለአንቺው ብዬ ነው...' አለች እናቷን የግዷን ፈገግ ለማለት እየሞከረች።

'እኔ ሳድግ ፓይለት ወይም ሆስተስ መሆን ነው የምፈልገው...' አለች ህፃኗ ፍንድቅድቅ እያለች። ያልጠበኩት ነገር ስለነበር እኔም ወደ እናቷ እየዞርኩ 'አሪፍ ነገር እኮ ነው የተመኘችው። እኔኮ እንደማንኛውም ህፃን የማይሆን ነገር እየጠራች አስቸግራችሁ መስሎኝ ነበር...' ስላት ፣ 'እኔም ሆንን አባቷ እኮ የምትፈልገው ብትሆን ደስታችን ነበር። ግን ደግሞ ከአሁኑ ተስፋ አድርጋ አድጋ ወደፊት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ ለመሆን በአየር መንገዱ ሂጃብሽን ካላወለቅሽ ፣ ሱሪ ወይም አጭር ቀሚስ ካለበስሽ አይሆንም ስትባል ምን ልትሆን ነው ብለን ስለምናስብ ነው ከአሁን የምንከለክላት....' አለቺኝ የንዴት ሳቅ እየሳቀች !

ከዚህ በፊት በብዙ ሙስሊም እህቶቻችን ይሄ ቅሬታ ሲነሳ ብሰማም እንደዚህ ግን ተረብሼ አላውቅም። ቁጭ ብዬ የአንዲት ጎበዝ ተማሪ ሙስሊም ህፃን መብቷ ሲነፈግ ፣ ምኞቷን ገና ከአሁኑ ስትነጠቅ ማየት ያናዳል። ያሳዝናል። ልብ ያደማል።

ሴኩላር ነው በሚባል ሀገር ላይ ሙስሊም እህቶቻችንን በአለባበሳቸው ብቻ መቀጠር የማይችሉበት አየር መንገድ የሚያህል ትልቅ ተቋም መኖሩ ያሳፍራል። አውሮፕላን ውስጥ ለማስተናገድ በየቱ አስገዳጅ ምክንያት ነው ፀጉር መልቀቅ ግዴታ ሆኖ ሂጃብ ማድረግ ሊያስከለክል የቻለው ? ሱሪና አጭር ቀሚስ ተፈቅዶ ረዥምም ቀሚስ የተከለከለው ተሳፋሪው ላይ ምን እንዳይጎልበት ነው ?

አየር መንገዱ እንደ ገላ ሻጭ በሆስተሶቹ ሰውነት'ና ፀጉር መራቆት ምንድን ነው የተለየ የሚያገኘው ጥቅም ?

የሙስሊሙም ጭምር የህዝብ ተቋም የሆነው አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ ለመስራት እህቶቻችን መማር እንጂ ሰውነታቸውን አጋልጠው ማሳየት ግዴታ ሊሆንባቸው አይገባም !

በአሁን ሰዓት ሙስሊሙ ህብረተሰብም ሆነ እስላማዊ ተቋማቶች ከምንም በላይ ጊዜ ሳንሰጥ ልንታገለው የሚገባ አድሎዊ ተቋም ይሄንኑ አየር መንገድ ይመስለኛል። ይሄ ተቋም በማይረባ ቢሮክራሲው ትላንት የብዙ እህቶቻችንን ተስፋ መቀማቱ ሳያንሰው ዛሬም የልጆቻችንን ህልም ጭምር እየነጠቀ ነው።

ይሄን የተቋሙ አግላይ የሆነ አካሄድ በጊዜ በቃ ልንለው ይገባል። እኛ ታግለን መብታችንን ባለማስከበራችን ልጆቻችን ስርአት ባለው ሃይማኖታዊ አለባበሳቸው ሊያፍሩ'ና ሊሸማቀቁ አይገባም !

ሂጃብ ፣ እንዲሁም ያላጠረ'ና ያልተወጠረ ቀሚስ ያደረገች ሙስሊም ሴት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ የመሆን መብት አላት ! ትሆናለችም !

ሃሳቡ ካስማማችሁ ሼር አድርጉት ለሚመለከታቸው አካሎች እንዲዳረስ !

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

17 Apr, 19:03


ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ።👇👇👇

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

09 Apr, 16:06


...عييييد المبارك

💐...እንኳን ለ1445ኛው የኢደል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰህ/ሽ..! 🌼🌺🎉🎉🌙

👳....عيد المبارك*
علينا وعليكم تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

https://t.me/ZEKR_MENZUMA

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

09 Apr, 07:24


ሼህ አህመድ ዳለቲ
ክፍል አንድ

ሼህ አህመድ ዳለቲ በ 1894 በ ኮኪር ገደባኖ ልዩ ሰሙ መጎ አካባቢ በተለምዶ ሸንቆ በሚባል መንደር ተወለዱ ወላጆቻወ ያወጡላቸወ የ መጠሪያ ሰም ገለቱ አዱሼ ነበር ።

ሼሁ ( ገለቱ አዱሼ ) አሰራአንድ አመትሲሞላቸው አገምጃይ ወደ ሚገኝወ አጎታቸው ሸህ አወል ሁሴን ዘንድ በመሄድ የሀይማኖት ትምህረት አሊፍ - ባ ብለው ጀመሩ ፣ ሼሁ (ገለቱ አዱሼ) ከጎታቸዉ ጋር አንድ አመት ገደማ እንደቆዩ የመጠሪያ ሰማቻው ከ ገለቱ ወደ የአለማችን ተወዳጁ ስም እና የ ሚሊዮኖች ሙሰሊም መጠሪያ በሆነው በ አህመድ በመለወጥ አህመድ አዱሼ በሚል ሰም እንደተቀየረ ታሪካቸው የናገራል ። አጎታቸው ጋር ሲቀሩ እና ሲማሩ ከቆዩ ቡኃላ ከ ሁለተ አመት ቆይታ ቡኃላ ወደ አዲሰ አበባ ዙሪያ ወደምትገኘው የ እስልምና ማእከል ዳለቲ በ መሄድ ለጥቂት ግዜ ትመህር ተከታትለዋል ።

ከደለቲም በ መቀጠል በ ኢትዪጵያ ሙሰሊም ታሪክ በ እሰልምና ትምህርት ማእከልነት በሰፋት ወደ ሚታወቀው ወሎ እና አካባቢው በማቅናት ለከፍተኛ ትመህርት እራሳቸውን አዘጋጁ ፣ ወሎ ወሰጥ ልዩ ሰሙ ዳወዶ በተበለ አካባቢ መቀመጫቸውን በማደረግ የተለያዪ ኪታቦችን እና የዲን ትመህርቶችን ከ እውቁ ሼህ ዑመር ከተባሉ አሊም እና ከሌሎች አሊሞች ዘንድ እየተዘዋወሩ ከ አሰራ አምስት አመት በላይ ቆየታ ከደረጉ ቡኃላ ፣ በ ኡሰታዘቸው ሼህ ዑመር ምክር እና ትእዛዝ አማካኝነት መርቀው እና ዱአድርገውላቻው ወደ ትወልድ ሰፈራቻወ ሄደው ዲንን እንዲያሰፈፉ እና እንዲያተምሩ ተላኩ ።

ሼህ አህመድ የ ሀይማኖት ትመህርት ማሰተማር የጀመሩት ከ ጠላት ወረራ በፊት ሁለት አመት ቀደሞ በሎ በ ዳለቲ ነው ፣ ዳለቲ በ አለም ገና እነ በሰበታ መሀል ተገነጥሎ በሚወጣ መንገድ በ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኝ በሸዋ የሙሰሊሞች መአከልነት ሆኖ ያገለግል ነበር ። ሼህ አህመድ ለ ሰባት አመት በዳለቲ በማሰተማር ከቆዩ ቡኃላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ማሰተማራቸውን የገፈበታል ሲሆን ፣ የራሳቸውን መርከዝ ወይም መሰድረሳ በመመሰረት ከ ገደባኖ፣ወለኔ ፣ሰለጤ ፣ ከ ኦሮሞ አካባቢ እና ከወሎ ጭምር ሼህ አህመድ ጋር ደረሶች ኢልምን ፈለጋ የመጡ ነበር ፣ ይህ ተቋሟቸው ከእሳቸው ህልፈት ቡኃላ እንኳን የ ሼህ መድረስ እየተባለ ኡማውን አገልግሏል ።

ሼሁ ሰምሰያሜቸው በተለይም በዳለቲ ቆይታቻው በዳለቲ በሚኖሩ የትገሬወረጂ በሚባሉ የ ኦሮሞበሄረሰቦች ከፍተኛ እወቅና እና ወዴታ ሰለነበራቸው በአዲስ አበባ ቆየታቸው ሰዎች የስም ሰያሜቸውን ሼህ አህመድ ዳለቲ ዩሏቸው ነበር ሆኖም ግን በተለይም የህ መጠሪያ በጣም የሚያከብሯቸው የ ሚወዷቸው የ ሰጋዘምዶች እና የተወለዱበት አካባቢ ተወለጆችን ቅሬታ ሰላሰነሳ ሰም ሰያሜቸው
" ሼህ አህመድ ዳለቲ " ወደ " የአም ሼህ " ወደሚል መጠሪያ በ ወዳጆቻው መገለገል ጀመረ ትርጓሜውም የሁሉም ሼህ እንደመለት ነው ።

ሼህ አህመድ አዱሼ እንደ ሀይማኖት መምህር ሆነው 40 አመት ያገለገሉ ሲሆን ፣ በህይወት ዘመናቸው 42 ግዜ ሀጅ ያደረጉ ሲሆን አበዘኛውን ማለት የቻላል እንደ አሁኑ አለጋ በአልጋ በልሆነበት ዘመን በ መርከበ ጉዞ ነበር ። ቁርአን ወደ አማርኛ ሲትሮገምበ ሀይለስላሴ ዘመን ፣ እሳቸው የተስራውን ስራ ረቂቅን አይተው እርማት እና እንዲያሻሽሉት ከተመረጡ አምስት ሀገር አቀፍ ታላላቅ ዑለማዋች ውስጥ አንዱ ናቻው ።

ይቀጥላል

በዚህ ቻናል⬇️👇
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA