ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

@sinksar


ይኼ ገጽ የአመቱ ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው።

" ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15

# ያጋሩ

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

22 Oct, 15:46


ሰኞ ማታ!
ቀን:- 11/02/2017ዓ.ም

በአ.አ ከተማ መርካቶ አካባቢ ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።

እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።

በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።

በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ምን ያህሎቻችን ነን ግን ለነገ አብዝቶ የሚያስጨንቀን?

ይኼው ነው!።

ክፉ አታምጣብን
ሰላም አውለህ ሰላም አሳድረን በሉ/እንበል/

ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ አስከፊና ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ላይ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

22 Oct, 15:29


#ኦርቶዶክስተዋሕዶ

" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው ፦

" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡

ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡

ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡

በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከታች ተያይዟል)

የዘገባው ምንጭ
@tikvahethiopia

✍️† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †✍️
               🌹🌹🌹
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

21 Oct, 12:09


🌹✞ ስንክሳር ጥቅምት ፲፪ (12)  ✞🌹

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለልበ አምላክ "ቅዱስ ዳዊት":
ለቅዱስ "ማቴዎስ ሐዋርያ" እና ለቅዱስ "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🙏+*" ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ "*+🙏

ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:-
"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ:
አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:19) ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን::

እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል:: *" አቤት አባታችን ዳዊት!!! . . . ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል "* እንላለን::
ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

ይህች ቀን ለእሥራኤል የነገሠባት ቀን ናት::
እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ" ቢለው በዚህች ቀን ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም ገብቷል::

በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ:: ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::

በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ:: የቅዱሱ ዜና ብዙ ነውና ለታሕሳስ 23 ይቆየን:: በቸር ቢያደርሰን በዚያው ቀን ከክብሩ እንካፈላለንና::

🙏+"+ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ +"+🙏

ቅዱሱ በቀዳሚ ስሙ "ሌዊ": በቀዳሚ ግብሩ ደግሞ "ቀራጩ" ይባል ነበር:: ወንጌል እንደሚል ጌታችን የጠራው ከሚቀርጥበት ቦታ ሲሆን (ማቴ. 9:9) ከ12ቱ ሐዋርያት ደምሮ (ማቴ. 10:1) ስሙን "ማቴዎስ" ብሎታል:: ትርጉሙም "ኅሩይ" (ምርጥ) እንደ ማለት ነው::

ጌታችንን በዘመነ ሥጋዌው በፍጹም ምናኔ ከማገልገሉ ባለፈ ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ: የእጁን ተአምራት ተመልክቷል:: የቃሉንም ትምሕርት ሰምቷል:: በጌታ ሕማማት ጊዜ ምንም በፍርሃት ከተበተኑት አንዱ እሱ ቢሆን አመሻሽ ላይ ወደ ማርቆስ እናት ቤት (ጽርሐ ጽዮን) ሒዶ ወንድሞቹን ሐዋርያትን ተቀላቅሏል::

የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከሙታን ተነስቶ ትንሳኤውን ሲገልጥም ቅዱስ ማቴዎስ ነበረ:: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ በጌታ ዕርገት ጊዜ ሊቀ ዽዽስናን ተሹሟል:: በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም ጸጋውንና 71 ልሳናትን ተቀብሎ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ወንጌልን ሰብኩዋል::

ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም ለማዳረስ እጣ በተጣጣሉ ጊዜ ለቅዱስ ማቴዎስ ምድረ ፍልስጥኤም ደረሰችው:: ሃገረ ስብከቱን ካዳረሰ በሁዋላም ወደ ሌሎች ሃገራት ተጉዞ ሰብኩዋል::

ለምሳሌ በገድለ ሐዋርያት ላይ በኢትዮዽያ: በፋርስና በባቢሎን አካባቢ ማስተማሩን ይገልጻል:: የሚገርመው ደሞ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ነገር ሃገራችን ውስጥ መኖሩ ነው::

ወደ አክሱምና አካባቢዋ ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም በሔድንበት ወቅት በጻድቃነ ዴጌ/ዶጌ ገዳም ውስጥ (አክሱም አካባቢ የሚገኝ የ3ሺ ስውራን ቦታ ነው) የቅዱስ ማቴዎስን በትረ መስቀል መመልከት ችለናል:: አባቶችም ቅዱስ ማቴዎስ በዘመነ ስብከቱ አክሱም አካባቢ መጥቶ እንደ ነበር ነግረውናል::

+ቅዱሱ ሐዋርያ በአይሁድ: በአሕዛብና በአረሚ መካከል እየተመላለሰ አስተምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቷል:: የጣዖት ካህናትንና ነገሥታትን ጨምሮ እልፍ አእላፍ ነፍሳትን ወደ ክርስትና መልሷል::

ስለዚህ ፈንታም እጅግ ብዙ መከራዎች
ተፈራርቀውበታል:: ጌታችንም በየጊዜው እየተገለጸ ያጽናናው ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያውን ወንጌል በምድረ ፍልስጥኤም ሲጽፍ: ዘመኑም ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት (ማለት በ43 ዓ/ም) አካባቢ ነው::

ወንጌሉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ የዘር ሐረግ ጀምሮ የጌታችንን ትምሕርቱንና ተአምራቱን በሰፊው ያትታል:: በመጨረሻም ከምሴተ ሐሙስ እስከ ትንሳኤ ድረስ አትቶ ይጠናቀቃል::

ቅዱስ ማቴዎስ ከ12ቱ ሐዋርያት በአንድ ነገሩ
ይለያል:: ከ5ቱ ዓለማት አንዱን (ብሔረ ብጹዓንን)
ያስተምር ዘንድ ተመርጧል:: ዘወትር እሑድ በደመና እየተነጠቀ ኃጢአት ወደ ሌለበት ዓለም ገብቶ ብጹዓንን ያስተምር ነበር:: "ሰላም ለማቴዎስ በደመና ሰማይ ዘተነጥቀ: ኅሩያነ ይርዓይ ዘብሔረ ብጹዓን ደቂቀ::" እንዲል::

+በዚያም ዘወትር ጌታችንን ያየው ነበር:: ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ ከተመላለሰ በሁዋላ በፍጻሜው ለጊዜው ባልለየናት አንዲት ሃገር ውስጥ አረማውያን አስረው አሰቃይተውታል:: በዚህች ቀንም ገድለውታል::

ጥቅምት 12 ቀን የሚከበሩ
👉ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዳዊትልበ አምላክ (የነገሠበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
4.ቅድስት ልዕልተ ወይን
5.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
6.ጻድቃን ዼጥሮስ ወዻውሎስ

👉 ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

✍️† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †✍️
               🌹🌹🌹
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

20 Oct, 22:37


የትላንቱ ማሕሌተ ጽጌ ያሳደረብኝ ስጋት

በልጅነታችን ቤተክርስቲያ ያደግን የእድሜ እኩዮቼ ከየትኛውም የከተማችን ጥግ ተሰባስበን ባሳደገን ደብር ውስጥ ማሕሌተ ጽጌን ቆመናል። ነገር ግን በጣም ሀዘን ውስጥ የጣለኝ አንድ ልምድ ሲቀር ታዝቤ በስጋት ሌቱን አሳልፌያለሁ።

በግራ እና በቀኝ ከሊቃውንቱ ቀጥለው የሚቆሙ ታዳጊዎች የወረብ ዑደት አልቆ ዝማሬው ወድ ቸብቸቦ ሲቀየር ሊቃውንቱ ይጨርሱና ታዳጊዎች በድጋሚ በግራ እና በቀኝ እየዘመሩ ወደ ሰዓታቱ ለመገናኘት ያመራሉ። ይህ የዝማሬ አገልግሎት እስከዚህኛው ዓመት ድረስ ደምቆ የቆየ ነበር።

በትላንትናው ዕለት ግን በብዛት የታዳጊዎች ልምድ የነበረው ዝማሬ አልነበረም። ምክንያቱም ታዳጊዎች በቤተክርቲያኒቱ በብዛት አልነበሩም።

አራዳ በሚገኘው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚገኙ መንደሮች ኗሪ የነበሩ የአጥቢያው ምዕመናን በአብላጫው "ለልማት" ከመንደሩ ተነስተዋል።

በልጅነቱ ሲያገለግል ያደገ ሁላ በአዋቂነት እድሜው ቤተክርስቲያንን ርቆ ይቀር ዘንድ አይቻለውምና የእድሜ እኩዬቼ ወንዶችም ሴቶችም አሁንም ከቤተ ክርስቲያን አልቀረንም።

ይቺ ምስኪን ቤተክርስቲያናችን ቀጣይ ተተኪ ይኖራት ይሆን?
አስፈርቶኛል።

"ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው"
ሉቃስ፣ 18-16

ጥቅምት 10-2017 ዓ.ም
ጋዜጠኛ ያሬድ ሹመቴ

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

20 Oct, 22:28


✞ ስንክሳር ጥቅምት 11 ✞
🌿🌹🌿

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

✞ እንኩዋን ለአባ "ያዕቆብ ስዱድ" እና ለእናታችን "ቅድስት ዺላግያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🌹" አባ ያዕቆብ ስዱድ "🌹
"ዻዻስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው::
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው::

ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ
አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር
"ሸክም: ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው::
ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን
አይመኝም::

ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም
ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው::

አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኩዋ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት ( ዽዽስና) ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን
ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው::

እነዚህም የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443
(451) ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ
ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::

በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ
አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና
ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ ያዕቆብ ሲባሉ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ የአንጾኪያ መንበር ፓትርያርክ ነበሩ::

ቅዱሱ በገዳማዊ ሕይወት የተመሠከረላቸው:
በትምሕርት የበሰሉና ለመንጋው የሚራሩ በመሆናቸው በምዕመናን ይወደዱ ነበር:: ነገር ግን ተረፈ አርዮሳውያንና መለካውያን ከነገሥታቱ ጋር አብረው ብዙ አሰቃዩዋቸው:: በመጨረሻም ከመንበራቸው አፈናቅለው ወደ በርሃ አሳድደዋቸዋል:: ከስደት በሁዋላም አባ ያዕቆብ በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

🌿"🌹 ቅድስት ዺላግያ ገዳማዊት 🌹"🌿

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የኃጥኡን መመለስ እንጂ ሞቱን አይፈልግም:: በጠፋው በግ መገኘት ደስ ይለዋል:: በእግርህ ሒድ እንኩዋ አይለውም:: ይልቁኑ በትከሻው ተሸክሞ ከጐረቤቶቹ ጋር ደስ ይለዋል እንጂ::

ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ቅዱሳን አንዳንዶቹ ጭንቅ ከሆነ የኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ናቸው:: ግን ድንቅ በሆነ ንስሃቸው "ቅዱሳን" ከመባል ደርሰዋል:: ከእነዚህም አንዷ ቅድስት ዺላግያ ናት::

=>ይህቺ ቅድስት እናት በልጅነቷ በመልኩዋ ምክንያት ስሕተት ያገኛት ናት:: አምላክ የፈጠረውን መልክና ገላ እንዴት መጠቀም እንዳለብን እየተማርን አይደለምና በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ገላችን ለዲያብሎስ ሰጥተነዋል::

ይህቺ እናትም ችግሯ ይኼው ነበር:: ስለ ገጽታዋና
ገላዋ የነበራት የተሳሳተ አመለካከት መጀመሪያ ወደ ትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ): ቀጥሎም ወደ ዝሙት ከተታት:: ለዘመናትም የሰይጣን ወጥመድ ሆና ኑራለች::

ፈጣሪ ግን ለሁላችንም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና
እሷንም ጠራት:: ምናልባትም በዘመኗ የብዙ ሰባክያንን ትምሕርት ሰምታለች:: አንዱም ግን ወደ ልቧ አልገባም::

ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት አስተማሪ በጥሩ አማርኛ ልባችን ደስ ያሰኝ ይሆናል እንጂ ሊለውጠን አይችልም::

በዘመኑም የሚታየው ትልቁ ችግር ይኼው
ይመስለኛል:: እግዚአብሔር የሾማቸው አባቶቻችን
ተቀምጠው ወጣቶች መድረኩን የሙጥኝ ብለነዋል::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ዺላግያ አንድ ቀን
የሰማችው የደጉ ዻዻስ ትምሕርት ግን ፈጽሞ ዘልቆ ተሰማት:: ተጸጸተች: አለቀሰች:: ወደ ዻዻሱ ሔዳ "ማረኝ" አለች: ንስሃ ሰጣት:: እርሷም ንብረቷን ሁሉ መጽውታ በርሃ ገባች::

አንገቷን ደፍታ በጾምና በጸሎት ሰይጣንን ድል ነሳችው:: ከሃገሯ ሶርያ ወደ ቀራንዮ ደርሳ ተመልሳ ለ30 ዓመታት ዘጋች:: ተባሕትዎዋን ስትፈጽም በጸጋ እግዚአብሔር ተአምራትን ሠርታ: ለኃጥአን መንገድ ጧፍ ሆና አብርታ
በዚህች ቀን ዐርፋለች::

=>አምላከ ቅዱሳን የሚያስተውለውን የንስሃ አእምሮን ያድለን:: ከወዳጆቹ በረከትም አያርቀን::

=> ጥቅምት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት
1.ቅዱስ አባ ያዕቆብ (ስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት)
2.ቅድስት ዺላግያ ገዳማዊት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅዱስ አርማሚ ሰማዕት

=> ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄምና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

" መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና
ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ
ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: "
(ሉቃ. 15:3-7)

✍️† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †✍️
🌹🌹🌹
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

19 Oct, 18:02


🌿 ስንክሳር ጥቅምት 10 🌿
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ሰማዕታት "ባኮስ ወሰርጊስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🌹" ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ "🌹

ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል
የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ
ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል
ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል::

እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው::
ባኮስ እና ሰርጊስ (ሰርግዮስ) ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም
ነበር::

ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ 2ቱ ቅዱሳን ሥራ
አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ
ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና::

በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው::

ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው
ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ: ይጸልያሉ: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ::

ከቆይታ በሁዋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ
መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ
ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ::

ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ
ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ::

በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቀያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች
ነንና ከዚህ በሁዋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው
አንታዘዝም" አሉት::

መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት 4 ቀን በሆነ
ጊዜ ግን 2ቱን ለያዩዋቸው::

ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት::

ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር
አስወጣችው:: በአካባባቢውም "ባባ" እና "ማማ"
የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት::

ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ6 ቀናት ካሠሩት በሁዋላ
በዚህች ቀን እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በሁዋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል:: ተአምራትም ታይተዋል::

=>አምላከ ሰማዕታት ጽንዓት: ትእግስታቸውን አሳድሮ ከበረከታቸው ይክፈለን::

ጥቅምት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት
1.ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ (ሰማዕታት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ መስተጋድል
3.አባ አውማንዮስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
7.ቅዱስ እፀ መስቀል

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇

       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

19 Oct, 16:01


ተፈጸመ !

የሊቀ ትጉኃን ባሕታዊ አባ መፍቀሬ ሰብእ ኪዳነወልድ የቀብር ስነ-ስርዓት በሐይቅ ዛሬ በቀን 09/02/2017ዓ.ም
በቅዱስ እስጢፋኖስ እና አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም ተፈጽሟል።

የሥራቸው ትጋት እና የንፁህ ልብ ትሁት በረከታቸው በሁላችን ላይ ትደር።

ቅዱስ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከቅዱሳኑ ጎን ያሳርፍልን!

ነፍስ ይማር!
😢

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

19 Oct, 04:48


🌹ስንክሳር ጥቅምት 9 🌹

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

+" ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ "+

✞✞✞ ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድና ባርቶስ በደረሰች ስብከቱ እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርቷል:: 'አሐደ እምተአምራቲሁ' እንዲሉ አበው ከእነዚህ ዛሬ አንዱን እንመለከታለን::

+ቅዱስ ቶማስ ጐና ወደምትባል የሕንድ አውራጃ መግቢያ ፈሊጥ ቢያጣ ጌታ ወርዶ አበኒስ ለሚባል ነጋዴ ባሪያ አድርጐ ይሸጠዋል:: በመጀመሪያ በንጉሡ ሠርግ ቤት ውስጥ ተአምራትን አሳይቶ ሕዝቡን ከነ ሙሽሮቹና ንጉሣቸው አሳምኗል::

+ቀጥሎ ግን ጎንዶፎር ለሚባል ሌላ ንጉሥ 'ቤተ መንግስት ሥራ' ተብሎ ይላካል:: ሐዋርያውም ንጉሡን "የማንጽበትን ወርቅና ብር ስጠኝ" ብሎት ይሰጠዋል:: ንጉሡ ዘወር ሲል ግን "ወእሁብ ዘንጉሥ ለንጉሥ-የምድራዊው ንጉሥ ለሰማያዊው ንጉሥ እሰጣለሁ" እያለ ገንዘቡን ሁሉ ለነዳያን በተነው::

+ገንዘቡ ሲያልቅበት "ንጉሥ ሆይ! መሠረቱ ታንጿልና ለግድግዳው ላክልኝ" ይለዋል:: ሲልክለት ይመጸውተዋል:: አሁንም "ንጉሥ ሆይ! ለጣሪያው ላክልኝ" ይለውና ይመጸውተዋል:: መጽሐፍ እንደሚል ምጽዋት ለሐዋርያው ልማዱ ነውና::

+በመጨረሻ ግን ንጉሡ ሲመጣ ባዶ መሬት ላይ ነዳያን ገንዘቡን ሲበሉት አገኘ:: ተበሳጭቶም ቅዱስ ቶማስን ይገድለው ዘንድ አሠረው:: በዚያች ሌሊት ግን የንጉሡ ወንድም ጋዶን ሙቶ ሐዘን በሆነ ጊዜ ሐዋርያው አስነሳው::

+ጋዶንም ለቅዱሱ ሰግዶ በሰማይ ለንጉሥ ጐንዶፎር ትልቅ ቤት ታንጾ ማየቱን ተናገረ:: ንጉሡና ሠራዊቱም በፊቱ ሰግደው አመኑ:: አጥምቋቸውም ሔዷል::

+" ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልዕ "+

+በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳን ሊቀ ዲያቆናቱ ቅድሚያውን ሲይዝ ዛሬ የምናከብረው ቅዱስ ደግሞ 'ካልዕ እስጢፋኖስ' (ሁለተኛው) ይባላል:: 2ቱም 'ቀዳሜ ሰማዕት' ይባላሉ:: ዋናው በሐዋርያት ዘመን ቀድሞ እንደተሰዋ ሁሉ ሁለተኛው በዘመነ ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም ቀድሞ ተሰይፏል::

+ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ሲሆን በአንጾኪያ ቤተ መንግስት ውስጥ ከነበሩ ልዑላንና የጦር መሪዋችም አንዱ ነበር:: በዝምድና ደረጃም የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ የእህቱ ልጅ ነው:: በቤተ ፋሲለደስ ከማደጉ የተነሳም የእርሱ ልጅ እንደ ሆነ በገድሉ ተጠቅሷል::

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልዕ ማለት መልክ ከደም ግባት የተባበረለት: ጾምና ጸሎትን የሚወድ: የነዳያን አጉራሽ: ኃያል የጦር ሰውና ተወዳጅ ክርስቲያን ነው:: ያ ክፉ አውሬ በዓለም በሚገኙ ምዕመናን ሁሉ ላይ ሞትና ስቃይን ሲያውጅ በአካባቢው የነበረ ይኼው ቅዱስ ነው::

+በቦታው ከነበሩ ብዙ ሺህ ሰዎች ንጉሡን ደፍሮ የተናገረው አንድም አልነበረም:: ቅዱስ እስጢፋኖስ ግን ለክርስቶስ ቀና:: ከሕዝቡ መካከልም እየሮጠ አልፎ በንጉሡ ፊት አዋጅ የሚያነበውን ወታደር ቀማውና በአደባባይ ያችን የክህደት ደብዳቤ ቦጫጭቆ ጣላት::

+ንጉሡንም "ሰነፍ" ሲል ገሠጸው:: እጅግ የተቆጣው ንጉሡ ግን ቅዱሱን በሰይፍ ሰንዝሮ ከ2 ከፈለው:: አካሉ መሬት ላይ ሲወድቅ ራሱ ግን በዓየር ላይ ሁና ለ3 ቀናት ትንቢትን ተናገረች:: ለዚያ አስጨናቂ የመከራ ዘመንም በር ከፋቹ ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልዕ ሆነ::

ዐርፏል::

✞✞✞ ቸሩ አምላክ እንዲህ ለመንጋው የሚራሩ እረኞችን አይንሳን:: ከሐዋርያው: ከሰማዕቱና ከደጉ ፓትርያርክም ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

🌹 ጥቅምት 9 ቀን የሚከበሩ
ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልዕ (ሰማዕት)
3.ቅዱስ አትናስዮስ ብጹዕ
4.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት
5.ቅዱስ ሊዋርዮስ ሊቀ ዻዻሳት
6.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
7.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት
8.አቡነ መዝገበ ሥላሴ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
9.አፄ ዳዊት ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (ግማደ መስቀሉን ያመጡ)

✞ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: ✞✞✞ (1ዼጥ. 5:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🌹✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞🌹

        https://t.me/Sinksar
        https://t.me/Sinksar
        https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

17 Oct, 19:36


✞ ስንክሳር ጥቅምት 8 ✞
🌿🌿🌿

እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ አጋቶን ወአባ መጥራ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

" አባ አጋቶን ባሕታዊ "

ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::

ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት:
"ክምረ ክምር ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ: አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት ነው::

ታላቁ ገዳማዊ ሰው አባ አጋቶን የታላቁ መቃርዮስ ቅዱስ ልጅ ነው:: ገዳመ አስቄጥስ እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን ስታፈራ ይህ አባት ቅድሚያውን ይይዛል:: ምንም በብዛት የሚታወቀው በአርምሞው (በዝምታው) ቢሆንም ባለ ብዙ ትሩፋት አባት ነው::

የሚገርመው የቀደሙ አባቶቻችን የፈለገውን ያህል መናኝ ቢሆኑም የሰው ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም:: "ሊሠራ የማይወድ አይብላ" የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ መሠረት አድርገው ከተጋድሎ በተረፈቻቸው ሰዓት ሥራ ይሠራሉ::

አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ምናኔ ሥራ መፍታት አይደለምና ሰሌን: ዕንቅብ: ሠፌድ የመሳሰለውን ይሠፋሉ:: ታላቁ አባ አጋቶንም በአንደበቱ ድንጋይ ጐርሶ: በእግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንቅቦችን ይሠፋ ነበር::

ለነገሩስ ዛሬ ዛሬ እንኩዋን ወንዶቹ ሴቶችም ብንሆን ይህንን ሙያ እየረሳነው ነው:: ቅዱሱ ግን ይሰፋና ወደ ገበያ ይወጣል:: በጠየቁት ዋጋ ሽጦት አንዲት ቂጣ (ዻኩሲማ) ይገዛል:: የተረፈውን ገንዘብ ግን እዚያው ለነዳያን አካፍሎት ይመጣል እንጂ ወደ ገዳሙ አይመልሰውም::

ታዲያ አንድ ቀን እንደልማዱ የሠፋቸውን 5 እንቅቦች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሔድ መንገድ ላይ አንድ ነዳይ (የኔ ቢጤ) ወድቆ ያገኛል:: እንደ ደረሰም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ይለምነዋል:: አባ አጋቶን ከእንቅቦቹ ውጪ ምንም ነገር አልነበረውምና "እንቅቡን እንካ" አለው::

ነዳዩ ግን ወይ የሚበላ: ካልሆነም ገንዘብ እንደሚፈልግ ይነግረዋል:: ወዲያው ደግሞ "የምትሠጠኝ ነገር ከሌለህ ለምን ወደ ገበያ ተሸክመህ አትወስደኝም?" አለው:: የነዳዩ አካል እጅግ የቆሳሰለ በመሆኑ እንኩዋን ሊሸከሙት ሊያዩትም የሚከብድ ነበር::

ጻድቁ ግን ደስ እያለው: ያለማመንታት አንስቶ ተሸከመው:: ከረጅም መንገድ በሁዋላም ከገበያ በመድረሳቸው አውርዶ ከጐኑ አስቀመጠው:: ያ ነዳይ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ቢለምንም የሚዘከረው አጣ:: አባ አጋቶን አንዷን እንቅብ ሲሸጥ "ስጠኝ?" ይለዋል:: ጻድቁም ይሠጠዋል::

እንዲህ "ስጠኝ" እያለ የ5ቱንም እንቅቦች ዋጋ ያ ነዳይ ወሰደበት:: አባ አጋቶን ግን ምንም ቂጣ ባይገዛ: በሆነው ነገር አልተከፋምና ሊሔድ ሲነሳ ነዳዩ "ወደ ቦታየ ተሸክመህ መልሰኝ" አለው:: አባቶቻችን ትእግስታቸው ጥግ (ዳር) የለውምና ጐንበስ ብሎ በፍቅር አንስቶት አዘለውና ሔደ::

ካነሳበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ይወርድለት ዘንድ ጻድቁ ቆመ:: ነዳዩ ግን አልወርድም አለ:: መቼም እኛ ብንሆን ብለን እናስበውና . . . ምን እንደምናደርግ ይታወቃል:: ጻድቁ ግን ዝም ብሎ ቆመለት::

ትንሽ ቆይቶ ግን ስለ ለቀቀው ሊያየው ዞር ቢል መሬት ላይ የለም:: ቀና ሲል ግን ያየውን ነገር ማመን አልቻለም:: ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ:: ነዳይ መስሎ እንዲያ ሲፈትነው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበር::

ክንፎቹን ዘርግቶ: በብርሃን ተከቦ: በግርማ ታየው:: ከወደቀበትም አነሳው:: "ወዳጄ አጋቶን! ፍሬህ: ትእግስትህ: ደግነትህ ግሩም ነውና ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎት ተሰወረው:: ጻድቁም በደስታ ወደ በዓቱ ሔደ:: አባ አጋቶን ተረፈ ዘመኑን በአርምሞ ኑሮ ዐርፏል::

🌿" ቅዱስ መጥራ አረጋዊ "🌿

ቅዱሱ የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያን ሲሆን በትውልድ ግብጻዊ ነው:: ከልጅነት እስከ እውቀት: ከእውቀት እስከ ሽበት ክርስቶስን ሲያመልክ ኑሯል:: ዘመኑ ክርስቲያኖች ስለ ሃይማኖታቸው ከባዱን ዋጋ (ሕይወታቸውን) የሚከፍሉበት ነበር::

በወቅቱ ብርቱ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ቢበዙም ብርቱ መንፈሳዊያን ተዋጊ ክርስቲያኖች ነበሩና ውጊያው ተመጣጣኝ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ሁሉም በዛለበት ዘመን ላይ ተገኝተናል::

ቅዱስ መጥራ ካረጀ በሁዋላ ነገሥታቱ "ክርስቶስን ካዱ" እያሉ መጡ:: ቅዱሱ ወሬውን ሲሰማ እጅግ ተገረመ:: ምክንያቱም መድኃኔ ዓለምን መካድ ፈጽሞ የሚታሰብ ነገር አይደለምና:: ቅዱሱ አረጋዊ ስለ 2 ነገር ሰማዕትነትን ፈለገ::

አንደኛ በክርስቶስ ስም መሞት የክብር ክብርን ያስገኛልና ከዚሁ ለመሳተፍ ነው:: ሁለተኛው ግን ለወጣቶች አብነት (ምሳሌ) ለመሆን ነበር:: መልካም መሪ ባለበት ዘንድ ብዙ ፍሬዎች አይጠፉምና:: ቅዱስ መጥራ እንዳሰበው ወደ መኮንኑ ሒዶ በአሕዛብ ፊት ክርስቶስን ሰበከ:: ስለዚህ ፈንታም ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን ከተከታዮቹ ጋር ገድለውታል::

አምላከ ቅዱሳን ትእግስታቸውን ያሳድርብን:: ከአባቶቻችንም በረከትን ይክፈለን::

ጥቅምት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አጋቶን ባሕታዊ
2.ቅዱስ መጥራ አረጋዊ (ሰማዕት)
3.ቅድስት ሶስናና ልጆቿ (ሰማዕታት)
4.አባ ሖር
5.ቅድስት በላግያ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

"ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ::
እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መስዋዕት ትሁን::
አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር:: የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ:: ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው::
ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሠጥ::
ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር::
ጻድቅ በምሕረት ይገሥጸኝ: ይዝለፈኝም::
" (መዝ. 140:2)

✍️† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †✍️
🌹🌹🌹
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

17 Oct, 10:04


🌸ፍትሐ_ነገሥት ክፍል ፳፰

🌻አንቀጽ ፴፱ - በእንተ ተአምኖ -
ራሱን የቻለ አካለ መጠን ያደረሰ ሰው በእውነት በደሉን ቢናገር ኃጢአት ስለሠራ ንስሓ ይገባዋል፡፡
                        🌻አንቀጽ ፵
        በእንተ ዘይትረከብ እምዘተኀጥአ
አንድ ሰው የጠፋ ገንዘብን ቢያገኝ ካገኘበት ቦታ እስከ ሰባት ቀን ያስመርምር፡፡ በየገበያው በየአደባባዩ ያስመርምር፡፡ ባለገንዘብ ነኝ ያለ ሰው ከመጣ የጠፋውን ገንዘብ ተለይቶ የሚታወቅበት መልኩን ይናገር፡፡
                      🌻አንቀጽ ፵፩
                 በእንተ ዘይኤዝዝ በንዋዩ
ይህ አንቀጽ መዋቲ ለወራሲ ወይም ለሌላ ሰው ስለሚያዝዘው ንብረት ይናገራል፡፡ መዋቲ ከተወው ገንዘብ አስቀድሞ የመግነዝ ዋጋ፣ መቃብር ለሚቆፍሩ ሰዎች ዋጋ ማወጣጣት ይገባል፡፡ የአብድ የዝንጉዕ ትእዛዙ አይጸናም፡፡ አዛዚ የሚያዝበትን ገንዘብ እንጂ የማያዝበትን ገንዘብ ቢያዝ ትእዛዙ አይጸናም፡፡ ንብረቱን ሁለት እጅ ለልጆቹ ሲሶውን ለሰብአ ቤተ ክርስቲያን ርቦውን ለዘፈቀደ ብሎ ያዝዝ፡፡ ክርስቲያን ሰው ድኅነተ ነፍስ በሌለበት ገንዘቡን መበተን አይገባውም አለ ለዘዋሪ ለአዝማሪ ለመሸታ ለጋለሞታ መበተን አይገባውም፡፡
                     🌻አንቀጽ ፵፪
                        በእንተ ርስት
ለራሱ መታሰቢያ ሊሆነው ከሞተው ሰው ገንዘብ ለነዳያን ስጡ፡፡ ዕለተ ሞቱ ለደረሰበት ሰው በፍርድ ቀን ዋጋ ሊሆነው ከገንዘቡ ለነዳያን ማዘዝ ይገባዋል፡፡ አበዳሪ ወይም ሌላ ባለዕዳ ከሟቹ ዘጠኝ ቀን አስቀድሞ መጠየቅ አይገባውም፡፡ የመዋቲ ሚስት ከባሏ ወራሾች ጋራ እኩሌታውን ገንዘብ ትካፈል፡፡ ልጆቿ ቢሆኑ ግን ከልጆቿ እንደ አንዱ ሆና ትካፈል፡፡ ልጆችም ተካክለው ይካፈሉ፡፡ በእናት በኩል ካለ ዘመድ በአባት በኩል ያለ ዘመድ አስቀድሞ ይውረስ፡፡ ቅርብ ዘመዶች ይውረሱ፡፡ ከዚያ ሩቅ ዘመዶች ሊወርሱ ይገባል፡፡ ከዘመዶቹ ውጭ የሆነ የታዘዘለት ሰው ካለም ይውረስ፡፡ አባት እናት የልጃቸውን ገንዘብ ከወንድሙ ከእኅቱ በልጠው ቀድመው መውረስ ይገባቸዋል፡፡ ከአባት አስቀድሞ አያት ከልጅ አስቀድሞ የልጅ ልጅ ከወንድም አስቀድሞ አጎት መውረስ አይገባቸውም፡፡ ባል የሚስቱን ገንዘብ መውረስ ይገባዋል፡፡ አወራረስ ከላይ ወደታች ማለትም ከአባት ወደ ልጅ ከልጅ ወደ የልጅ ልጅ ይወርዳል፡፡ ወደታች ልጅ የልጅ ልጅ ቢታጣ ግን ወደላይ ይወጣል፡፡ መውረስ የሚገባው ከሕግ ሚስት የተወለደ ነው፡፡ መውረስ ለቅርብ ዘመድ ሊሆን ይገባል፡፡ ለመዋቲ እናት አባት ባይኖሩ ወንድ አያቱ ሴት አያቱ ከወንድሞቹ ከእኅቶቹ ጋራ ይውረሱ፡፡ ከወንድም ልጆች ወንድም ይቀርባል፡፡ በጎንና በጎን ካሉ ከአጎት ከአክስት ወደላይ ያሉ አያቶች ይቀድማሉ፡፡ ወራሽ የሌለው ሰው ገንዘቡ ለመንግሥት ይሁን፡፡ በገንዘቡ ያዝበት ዘንድ የወደደውንም ያደርግበት ዘንድ ለወደደውም ያወርስ ዘንድ የኤጲስ ቆጶሱና የቤተክርስቲያኑ ገንዘብ ተለይቶ የታወቀ ይሁን፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ከተሾመ በኋላ ያገኘው ገንዘብ ከሞተ በኋላ ለቤተ ክርስቲያን ይሁን፡፡ ምንም ቢያዝለት ኢአማኒ አማኒውን አይውረሰው፡፡ አውራሹን የገደለ አይውረስ፡፡
                     🌻አንቀጽ ፵፫
                       በእንተ ፈታሒ
በሀገር ተሰብስቦ ሲኖሩ ጸብ አይቀርም፡፡ ተጣልቶም ዕርቅ አይቀርም፡፡ ይህም ያለዳኛ አይፈጸመም፡፡ ዳኛ ግብሩ ጠባዩ ያማረ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ሀገር ሁሉ ሹም ሹሙ፡፡ ዳኛ በፍርድ ጊዜ የማያዳላ፣ መማለጃ የማይቀበል ሊሆን ይገባዋል፡፡ ዳኛ አካለ መጠን ያደረሰ ከሠላሳ በላይ ዓመት የሆነው ወንድ ይሁን፡፡ ዳኛ የተማረ ይሾም እንጂ ያልተማረ አይሾም፡፡ ዳኛ ኦርቶዶክሳዊ ምእመን ሊሆን ይገባል፡፡ ዳኛ ከነውር ከነቀፋ የራቀ፣ ብልህ አዋቂ፣ በቁጣ ጊዜ የሚታገሥ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ዳኛ ጆሮው የማያከራክረው ዓይኑ የሚያስተውል፣ አንደበቱ የበረታ፣ የሕዝቡን ቋንቋ የሚያውቅ፣ መጽሐፍ አዋቂ ይሁን፡፡ ምስክሮችን መመርመር ይገባል፡፡ ከሐሰት ንጹሓን የሆኑ፣ የታመኑ፣ ደጋግ እንደሆኑ መመርመር ይገባል፡፡ በሐሰት ከፈረዳችሁት ፍርድ የተነሣ ለቅጣት የተዘጋጃችሁ እንዳትሆኑ ረበናትን ከመምሰል ተጠበቁ፡፡ ዳኞች ፍርዳችሁ እውነት ቢሆን በዚህ ዓለምም በወዲያኛው ዓለምም በእውነት ዋጋችሁን ከእግዚአብሔር ታገኛላችሁ፡፡ ዳኛ ተቆጥቶ ሳለ፣ ፈርቶ ሳለ፣ አዝኖ ሳለ፣ ደስ ብሎት ሳለ፣ ተርቦ ሳለ፣ ተጠምቶ ሳለ፣ ታሞ ሳለ፣ አንቀላፍቶት ሳለ፣ ሰንፎ ደክሞ ሳለ፣ ሰክሮ ሳለ፣ ሰልችቶት ሳለ አይፍረድ፡፡ ዳኛ ሳይፈርድባችሁ ባላጋራ ሳያወርድባችሁ አትማሉ፡፡ መሓላ በጸብ በክርክር ጊዜ በግድ ያለውድ ይሻል፡፡ በፈራሽ በተርታ ነገር ስመ እግዚአብሔርን ጠርተህ አትማል፡፡ ከካህናት ወገን በሐሰት ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ የማለ ሰው ሦስት ዓመት ይለይ፡፡ በምትፈርዱበት አደባባይ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንዳለ ዕወቁ፡፡ ፍርድ ለመፍረድ ከቤተ እግዚአብሔር ገብቶ መቀመጥ አይገባም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ፀብ ክርክር ጩኸት ሊደረግበት አይገባም፡፡ ዳኞች በዕለተ እሑድ መፍረድ መቅጣት አይገባቸውም፡፡ በዕለተ እሑድ የተጣሉትን ብታስታርቁ ብፁዓን ገባርያነ ሰላም ከተባሉት ትቆጠራላችሁ፡፡ የአንዱን ቃል ሰምታችሁ ባላጋራ ሳይመጣ አትፍረዱ፡፡ ከሁሉ ጋር ለመስማማት ቸኩል፡፡ እግዚአብሔር የይቅርታ የርኅራኄ ባለቤት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ወደአሕዛብ ዳኛ መሔድ አይገባውም፡፡ ይፈርዱለት ይፈርዱበት ዘንድ ወደ ሸሁ ወደ ቃልቻው መሔድ አይገባውም፡፡ በካህናቱ የሚፈረደውን ፍርድ ወደመኳንንት አይውሰዱት፡፡ የሚመሰክሩ ሰዎች እውቀት ያነሳቸው አይሁኑ፡፡ ኢአማኒ በአማኒ መመስከር አይገባውም፡፡ ኻያ ዓመት ያልሆነው ሕፃንም አይመስክር፡፡ በሐፃኒ በመጋቢ እጅ ያለ ሰውም አይመስክር፡፡ አውቆ አበድ አይመስክር፡፡ ዲ*ዳ አይመስክር፡፡ የዕለት ራት የጣት ቀለበት የሌለው ድኻ አይመስክር፡፡ ሎሌ ለጌታው ጭፍራ ለአለቃው አይመስክር፡፡ ሰካራም አይመስክር፡፡ ሰው ለራሱ ሊመሰክር አይገባም፡፡ በራሱ ላይ መመስከር ግን ይችላል፡፡ ዘመድ ለዘመዱ መመስከር አይገባውም፡፡ ሰው በጠላቶቹ መመስከር አይገባውም፡፡ አበዳሪ በተበዳሪ መመስከር አይገባውም፡፡ በኤጲስ ቆጶስ ላይ የመ*ና*ቃ*ንን ምስክርነት መቀበል አይገባም፡፡ የአንዱን ኤጲስ ቆጶስ ምስክርነት በአንዱ ኤጲስ ቆጶስ አይቀበሉት፡፡ በወንድሞቻቸው ቀንተው ክፉ ነገሩን ወደው በሐሰት የሚመሰክሩ ብዙ ናቸውና ሰውን ሁሉ በምስክርነት አይመኑት፡፡ ነገራቸው እውነት ቢሆን ነው እንጂ እውነት ካልሆነ ምስክሮችን ብዙ ናቸው ብለው ሊያምኗቸው አይገባም፡፡
 
© በመ/ር በትረ ማርያም አበባው
         ክፍል-፳፱- ይቀጥላል. . .
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
               🌹🌹🌹
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar

ስንክሳር እና ወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳዮች

17 Oct, 09:57


የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን የጸደቀውን ሕግ በጽኑ አውግዘውታል። እርምጃው የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂና ሜሎኒ ድጋፍም አለበት ተብሏል።
ራሳቸውን እንደ ክርስትያን እናት የሚቆጥሩት ጠቅላይ ሚንስትሯ፣ ልጆች መወለድ ያለባቸው ከወንድ አባት እና ሴት እናት ብቻ ነው ብለው ያምናሉ።
ሜሎኒ ቀደም ሲል ስለማሕጸን ኪራይ አላስፈላጊነት ሲናገሩ ተሰምተው ነበር።
በምርጫ ቅስቃሳቸው ወቅትም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የማይደግፍ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር።
በ2023 የእርሳቸው መንግሥት ከተመሳሳይ ጾታ የተገኙ ልጆችን እንዳይመዘገብ ለሚላን ከተማ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትር ሜሎኒ የማሕጸን ኪራይ የፈጣሪን ጸጋ እና ብቸኛ ስልጣን በገንዘብ መግዛት እንደሚቻል ለማሰየት የሚሞክር ማጭበርበር ነው ብለው ያምናሉ።
ጠቅላይ ሚንስትሯ ብቻ ሳይሆኑ ምክትላቸው ማቴዮ ሳልቪኒም የማሕጸን ኪራይን በጽኑ አውግዘውታል። “ሴቶችን እንደ ኤቲኤም ማሽን የሚቆጥር ድርጊት ነው” ብለውታል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ እንደሚሉት የማህጸን ኪራይ ከሚፈጽሙት 90 በመቶ የሚሆኑት የተቃራኒ ጾታ ጥንዶች ናቸው።
የማሕጸን ኪራይን በተመለከተ የተለያዩ አገራት የተለያየ ሕግ አላቸው። ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጣሊያን እና ጀርመን የማሕጸን ኪራይን በሕግ የከለከሉ የአውሮፓ አገራት ናቸው።
በዩናይትድ ኪንግደም የማሕጸን ኪራይ ቢፈቀድም ጽንሱን ለምትሸከመው ሴት የተጋነነ ክፍያ መፈጸም ክልክል ነው። በአየርላንድ፣ ሆላንድ፣ ቤልጂየም እና ቼክ ሪፐብሊክ ፍርድ ቤት ስለማሕጸን ኪራይ ውሳኔ አይሰጥም።
ግሪክ ደግሞ የውጭ አገር ሰዎች የማሕጸን ኪራይ ቢፈጽሙ በሕጋዊነት ትቀበላቸዋለች። ነገር ግን ማሕጸን የምታከራየዋ ሴት ትዳር የሌላት መሆኗ መረጋገጥ አለበት።
አሜሪካ እና ካናዳ ለተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች የማሕጸን ኪራይን የሚፈቅዱ ሲሆን ጥንዶቹ ከውልደት ጀምሮ የወላጅነት መብትም ያገኛሉ።

BBC