ሳተናው ሚዲያ

@satenaw_media


የዚህ ቻናል አባል ስለሆኑ እያመሰገንን ለወዳጅዎ በማጋራት ትግሉን ይቀላቀሉ

ሳተናው ሚዲያ

22 Oct, 21:02


Mulugeta Anberber (Facebook)

እምሽክ!

ሳተናው ሚዲያ

22 Oct, 18:05


Mulugeta Anberber (Facebook)

የትብብር ጥያቄ!

የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እያደረገ ባለበት ወቅት ከጨፍጫፊዎች ጋር እየተጋደሙ ያሉ በአማራ ሕዝብ ስምና እሴት እየነገዱ ያሉ ሞዴል ባይነን ሴተኛ አዳሪዎችና የሥርዓቱ የጥቅም ተጋሪዎች አርቲስቶችን ጉዳይ በተመለከተ መረጃዎችን እየጨረስሁ ነው፣ መረጃውን ይፋ ከማድረጌ በፊት ይህን ካልሰማህ የምትሉኝ የጽሁፍና የምስል ማስረጃ ካለ በውስጥ ላኩልኝ!

እስካሁን በሰበስብሁት ብዙ ሞዴል ነን ባዮችና አርቲስት ነን ባዮች ሴተኛ አዳሪዎች ተገኝተዋል። (ቀልድ የለም፣ ይፋ ይሆናል)

ያላመረረ ትውልድ አይድንም!
አንበርብር!

ሳተናው ሚዲያ

22 Oct, 16:30


Mulugeta Anberber (Facebook)

ገባ ገባ በሉ!

ሳተናው ሚዲያ

22 Oct, 08:49


Mulugeta Anberber (Facebook)

ታላቅ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ!
በ16 ከተሞች!

ሳተናው ሚዲያ

21 Oct, 22:52


Mulugeta Anberber (Facebook)

እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም ይላሉ የአገዛዙ አፈቀላጤዎች!

ራሳችሁ ያነደዳችሁትን ለማን ልታላኩ ነው።

አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ነው።

መርካቶን ለምን እንደአቃጠላችሁት ዝርዝር መረጃ ይዤ እመለሳለሁ!

ሳተናው ሚዲያ

21 Oct, 16:36


Mulugeta Anberber (Facebook)

የጥቅምት ሰማዕት - ፋኖ አርበኛ ሞላ ደስዬ

ጀንበሯ መጥለቅ እያማራት ነበር ወደ ምዕራብ አዘቅዝቃለች፤ የቦሩ ስላሴ ቅዝቃዜ አይሏል፥ ዝናብ እና ብርድ አድሮባቸው ከሀይቅ (ሂትቻ) ተነስተው ቦሩ ስላሴ የገቡት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ለ6 ሰአት ያህል ትንቅንቅ ላይ ናቸው፤ በዚህ ሂደት 3 የሚሆኑ ጓዶች ተሰውተዋል።

ዕለቱ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ/ም ምሽት ነው። ይህ ዕለት አርበኛ እና ምሁሩ ያ ለሰማይ ለምድር የከበደው በአማራነት ልቡ የመነነው ጀግናው ሰማዕት ፋኖ ሞላ ደስዬ የተሰዋበት ዕለት ነው።

በወቅቱ ጠላት ሙሉ ለሙሉ ተሁለደሬ ወረዳን ማለትም ሀይቅና ዙሪያውን መያዝ ስላልቻለ በምትኩ የአምባሰል ተራሮችን በመቆጣጠር በቦሩ ስላሴ አድርጎ ደሴን የመቆጣጠር ዕቅድ ነበረው፤ ያኔ ዝናብ እና ብርድ ለተከታታይ ቀናት ያለፈበት የምስራቅ አማራ ፋኖ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ሂቲቻ እኩለ ሌሊት ላይ ደረሰ:: እዛው በማደር በጧት 12 ሰአት ስብሰባ ተብሎ ተጠራ:: ጠላት በቦሩ ስላሴ አድርጎ ደሴን ሊቆጣጠር ነው ተብሎ ተነገረ። በእግር ጉዞ ተጀመረ:: ትንሽ መንገድ እንደተጓዝን አንድ ካሶኒ እና አይሱዚ ከፓትሮል ጋር ተላከ::

በጢጣ ሚካኤል አልፈን በደሴ ዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት አድርገን ወደ ቦሩ ስላሴ በሰልፍ ጉዞ ተጀመረ። ጠላት በዲሽቃ እና በስናይፐር ተኩስ ከፈተ:: ቦታ ቦታ ተያዘ:: ከወገን በኩል የዲሽቃውን በዲሽቃ የክላሹን በክላሽ ምላሽ ተሰጠ። ዲሽቃውን ሙሉጌታ ዲሽቃ ያስጎራው ጀመረ:: ብሬኖችን እነ ራምቦ፥ ጋሻው እና ሌሎች ጀግኖች አቅለበለቡት።

የጨበጣ ውጊያውን እነ በለጠ ሸጋው፥ ይታገሱ አራጋው እና አማን ባረኩት። ዳንኤል አለሙ ኢንፎርቲውን ጥሎ ስናይፐር ይዞ ጠላትን መጣል ጀመረ። ተኩሱ ተባባሰ፤ ምድርጤ...

View original post

ሳተናው ሚዲያ

21 Oct, 12:10


Mulugeta Anberber (Facebook)

ዘንድሮ እንደ ዳንኤል ክብረት ስሙ የበዛለት የለም።

ዛሬም አዲስ ስም ወጥቶለታል። እሱም ዳኒ ጩለሌው ተብሏል።

ከዚህ በፊት የነበሩት ስሞች፦
ዘንዘሪጡ ዳንኤል
ጋኔል ክስረት
ዳኒ ቦይ
ሂሳቡ

አሁን ደግሞ:👉 ዲኒ ጩለሌው!

ሳተናው ሚዲያ

21 Oct, 09:00


Belay Manaye (Facebook)

የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ።

ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም እና የአማራ ፋኖ በጎንደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በስልክ ቆይታ አድርገዋል። በአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) አመቻችነት በተደረገው የሚዲያ ብሪፊንግ ተግባር፣ የፋኖ አመራሮቹ ከዋሽንግተን ፖስት (Washington post)፣ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት (Reuters)፣ ዘኢኮኖሚስት (The Economist)፣ ብሉምበርግ (Bloomberg) እና ከአውሮፖ ፍሪላንስ (freelance journalist from Europe) ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል።

በዚህም የፋኖ አመራሮቹ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በተለይም የአብይ አህመድ ቡድን በንፁሃን ላይ እያደረገ ስላለው ጭፍጨፋ አጭር ገለፃ ካደረጉ በኋላ፣ በጋዜጠኞች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ እና ማብራሪያ እንደሰጡ ተገልጿል።

በዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ እና የጦር ወንጀሎች ለማጣራት የውጭ ገለልተኛ ቡድን ገብተው ለማጣራት እንዲችሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ልታደርጉ ትቀበላላችሁ ወይ? የአማራ ክልልን ከዋና ዋና ከተሞች በስተቀር 90 በመቶ ተቆጣጥራችኋል ይባላል፣ ክልሉን ሙሉውን ብትቆጣጠሩ ምን ታደርጋላችሁ? እናንተ በምትቆጣጠሯቸው ቦታዎች ለህዝቡ ምን አይነት አገልግሎት እየሰጣችሁ ነው? እና መሰል ጥያቄወች ይገኙበታል።

በተጨማሪም፣ እናንተ በተቆጣጠራችኋቸው ቦታዎች የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች፣ ለምሳሌ ዘረፋ እና እገታ...

View original post

ሳተናው ሚዲያ

20 Oct, 10:59


Belay Manaye (Facebook)

ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ እንዳላማው ክንዴን ጨምሮ ባሕር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የቆዩ ወገኖች ወደ ዳንግላ ካምፕ ተወስደዋል። በአማራ ክልል ወታደራዊ ካምፖች፣ መጋዘኖች እና ማሰልጠኛዎች ማጎሪያ ሆነዋል።

ሳተናው ሚዲያ

19 Oct, 19:22


Mulugeta Anberber (Facebook)

ለ12 ቀን ሲካሄድነበረውን ስብሰባ ሙሉ ለሙሉ ስከታተለው ነበር። እናም በተስፋ መቁረጥ ደምደውታል!

የመጨረሻ ውሏቸው፦
የስብሰባ አዳራሽ- አድዋ 00 ሙዚዬም

ውሎ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን!

ጠ/ሚ እስካሁንሰነበቱባቸውን10 ሰነዶችን ዋና ዋናሚላቸውንና አዳማ ያቀረበውን ቪዲዮ ሙሉ ሳይሆን ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ሲነሱነበሩትን ጉዳዮች ተቆርጦ እንዲቀርብ ተደርጓል። ከተቆረጡት ንግግሮች መካከል (ኤርትራን እንደጋዛ) በዚሁ ውስጥ አጠቃላይ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ አንስቷል። ከአንሳቸው ነጥቦች መካከል "አመራሩፅንፈኛ ምሽግ ናችሁ፣ እናንተ ሰርታችሁ ለውጥ አታምጡ፣ሆነ ነገር ሲነገራችሁ አንገት መነቅነቅና ከንፈር መምጠጥ ሆኗል ስራችሁ" ብሏቸዋል።

ቀጥሎም "አጠቃላይ እኛ አሁን ባለው ሁኔታ ከንጉሱ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድርስ በምስለኔ እንጅ ሶማሌ በራሱ ተወላጅ ክልሉን መርቶ አያውቅም፣ አፋር በራሱ ተወላጅ ተመርቶ አያውቅም፣ ክልሎች አሁን ያላቸውን ያክል ነፃነት ኖሯቸው አያውቁም።" እያለም ቀባጥሯል። ታሪክ ስለማያውቅ ከዚህተለዬ ሊናገር አይችልም።

#ስለDiplomacy፦ ዙሪያችን ብዙ እድገታችንንማይወዱ በክፉ አይን እየተመለከቱን ነው።ባህር በር ጥያቄ ጉዳይ ነገምማንተወው ጉዳይ ነው ብሏል። በቪዲዮ ላይ ባለፈው ናዝሪት ላይ በተካሄደው ስብሰባ ኤርትራን እንደ ጋዛ እናደርጋታለን ያለውን ቆርጠውታል።

አብይ አህመድ ከፋኖ ጋር እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምንም ያለው ነገርለም፤ ግን ንግግሮቹ ሁሉተስፋ መቁረጥ ይመስላል።

#####################

ከአብይ አህመድ ማጠቃለያ በመቀጠል ከንቲባ ተብዬዋ በአካል መጥታስራ መመሪያ ልሰጥ ነው በሚል ደስኩራለች።

በንግግሯም "እናንተምንሰራውን ስራ ጠላት ሲያራክሰው እያያችሁ ምንም...

View original post

ሳተናው ሚዲያ

19 Oct, 18:24


Mulugeta Anberber (Facebook)

📌የኢትዮ ቴሌኮምን ሼር በተመለከተ (Boycott)

1ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም የብር እና የዶላር ምንዛሬ በገበያ ትይዩ እንዲደረግ ከመወሰኑ ቀድም ብሎ የነበረው ጠቅላላ ዋጋ 80 ቢሊየን ብር ነው ነበር። ዶላር 100 ቤት ሲገባ ሁላችንም በግማሽ እንደደኸየነው ኢትዮ ቴሌኮምም ዋጋው ወደ 40 ቢሊየን ይወርዳል ማለት ነው። እሺ በጦርነት የወደመበትን ንብረት፣ አገልግሎት ባልሰጠባቸው ቦታዎች ያጣውን ገቢ ምናምን እንተወውና 20 ቢሊየን ጨምረንለት 100 ቢለየን ብር ዋጋ እንስጠው።

የቴሌኮሙ 10 ከመቶ ድርሻ 30 ቢሊየን ነው ከተባለ ጠቅላላ ዋጋው 300 ቢሊየን ነው ማለት ነው። ይህ የተጋነነ ዋጋ (Overvalued) ወይም ማውጣት ከሚችለው በላይ ነው ማለት ነው። የ10 ብር እቃ በ1ሺ ብር መግዛት ከፈለግህ መብትህ ነው።

2ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም በጣም ከፍተኛ እዳ ያለበት ተቋም ነው። ይህን ያክል እዳ ካለበት ተቋም ሼር መግዛት ካዋጣህ ምርጫው የአንተ ነው።

3ኛ. ኢትዮ ቴሌኮም ቬር ሸጦ የሰበሰበውን ብር ምንድነው የሚያደርገው? ተቋሙን ያዘመንብታል? ወይስ መንግስት የጦር መሳሪያ እንዲገዛበት ይሰጣል? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት። መልሱ ብሩ ለጦር መሳሪያ ግዢ እና ሰዎችን በማፈናቀል ስልታዊ የዲሞግራፊ ለውጥ ለማድረግ እየተሰራ ባለው የኮሊደር ልማት ይውላል የሚል ነው። ህዝብህን ለመግደል ለሚውል ተቋም ገንዘብህን ካፈሰስክ ከገዳዮች አትለይም። መብቱ ግን የአንተ ነው።

4ኛ. የቴሌኮም ዘርፉ በአደገኛ ሁኔታ እየተቀየረ ነው። ኢንተርኔት ከስፔስ ላይ መግኘት ተችሏል። ከሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰሩ ስልኮች እየተመረቱ ነው። ይህ ለውጥ አሁንም ገመድ የሚዘረጋውን ኢትዮ ቴሌኮም ያከስሩታል። በዚህ ፍጥነት ይራመዳሉ...

View original post

ሳተናው ሚዲያ

19 Oct, 07:34


Mulugeta Anberber (Facebook)

📌ድርብርብ ኃላፊነት አለብን!

ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ሕይወታችን የሰቀቀን ነበር፡፡ አማራ በመሆናችን እንዳንዶቻችን ከአማራነታችንም በተጨማሪ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች በመሆናችን ፋሽስታዊው ቡድን ዛሬ አፈነን፣ ነገ አፈነን እያልን ነበር የሰቀቀን ህይወት የምንገፋው፡፡ ያም ሆኖ ብዙዎቻችን ከመታፈን አላመለጥንም፡፡ ዛሬ ያለነው ስደት ላይ ነው፡፡ ስደት ጥሩም ባይሆን እንደ ኢትዮጵያ እታፈናለሁ ብለን ብዙ የምንሰጋበት አይደለም፡፡

ስለሆነም ድርብርብ ኃላፊነት አለብን፡፡ አንድም የሕልውና ትግል ላይ ለሚገኘውና በየእለቱ በድሮን ለሚጨፈጨፈው ሕዝባችን ድምፅ መሆን፡፡ ሁለትም በፋሽስታዊው ቡድን ታፍነው በየማጎሪያ ቤቱ ለሚገኙት ውድ ወገኖቻችን ድምፅ በመሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ያለንበትን ሁኔታ እንዲገነዘብና ጫና እንዲያደርግ መታገል፡፡ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ሊያደርግ የሚችለውና የእኛን ሁኔታ በትክክል ሊገነዘብ የሚችለው በበጎ አድራጎት መልክ ሳይሆን እኛ በታገልነው መጠን ነው፡፡

ስለሆነም በውስጣችን ሊኖሩ የሚችሉ ጥቃቅን የአካሂድ ልዩነቶችን ወደ ጎን ብለን ለሚሰቃየው ሕዝባችን ስንል የመተባበርና በአንድነት ፀንተን የመቆም ግዴታ አለብን፡፡

በውጭ ሀገራት በየዩኒቨርሲቲው በትምህርት ላይ የምትገኙ የአማራ ልጆችም በውጭ ቋንቋዎች መፃፍና ስለ አማራ ሁኔታ ማስረዳት ይጠበቅባችኋል፡፡ ቢቻል ቢቻል ያላችሁበትን ዩኒቨርሲቲ ተጠቅማችሁ የጥናት ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀትም በጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡

በተባበረ ክንድ የምናደርጋት እያንዳንዷ የየእለቱ ጥረታችን ፍሬ አላት፡፡ ከያዝ ለቀቅ ወጥተን ጸንተን ስናታገል ምን ያክል ውጤት እንደምናመጣ እያየነው ነው፡፡

እንበርታ‼️

ሳተናው ሚዲያ

18 Oct, 20:19


Mulugeta Anberber (Facebook)

X ያልቀናን፣ በፌስቡክ አውጅልን ብለዋል!

ሳተናው ሚዲያ

18 Oct, 19:09


Mulugeta Anberber (Facebook)

📌ትብብር!

ፌስቡክ እነዚህ ፎቶ በመለጠፍ፣ ደጋግሞ በመለጠፍ፣ አሁንም በተደጋጋሚ በተናጥል በመለጠፍ ይጥለቅለቁ!

ሌላ ነገር የሚለጥፉትን በማስቆም በእነዚህ ይሞላ!

እንተባበር!