🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

@rasn_fllega


~አንተን እንደ ገባህ እንጂ ሰዎች እንደተረዱህ አትኑር፤
.
.
.
ምክኒያቱም ከአንተ እና #ከአላህ በላይ ስላንተ የሚያውቅ ሰው የለምና!!

ሀሳብ መስጫ ግሩፕ👉 @rasn_discuss
owner👉 @Fuad_Abdulhamid
በቲክቶክ👉 tiktok.com/@fuad_heart

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

21 Oct, 06:23


👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/QURAN_KG

የየትኛውን ቃሪእ ቲላዋ ይፈልጋሉ?

ከ 200 በላይ ቃሪዎችን የሚያገኙበት ልዩ ቻናል
ጋበዝኳችሁ፡፡

Join & share us
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

21 Oct, 04:10


ቀልቤ ከዝነት ደጅህ
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ገጣሚና አቅራቢ፡
ፉአድ አብዱልሐሚድ



Join & share us
ይጫኑ👉 @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

19 Oct, 19:10


እኔ፦ የኔ ብርቅዬ እናት❤️
ኡሚ፦ ወዬ የኔ አንበሳ

እኔ፦ አንቺ ለኔ ከሆንሽልኝ ነገር አንፃር ግን ምን አድርጌልሻለው እላለው?
ኡሚ፦ አይኖቼ አንተን ሰላም ሆነህ ብቻ ማየታቸው ለኔ ይበቃኛል።

እኔ፦ እናትዬ! እኔኮ የጠየኩሽ... "እኔ ምን ሰጠሁሽ ነው?"
ኡሚ፦ አንተ እራስህ እኮ የኔ ልዩ ስጦታዬ ነህ ጀግናዬ!!!
....በል አሁን ቁርስህን በደንብ ብላና ወደ ስራ ሂድ....💕💕💕💕

       የእናት ነገር......
🤍°°°°°°°°°°°°°°°°🤍

አላህ ረጅም ሀያት ያኑርሽ።🤲

Join & share us
ይጫኑ👉 @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

15 Oct, 20:08


ሱረቱል አንዐም
ቃሪእ....🇪🇹

❤️❤️❤️🌹❤️❤️❤️
Join & share us
ይጫኑ👉 @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

12 Oct, 19:45


በጣም የሚፋቀሩ ትኩስ ጎጆ የመሰረቱ ጥንዶች ነበሩና....
ለተወሰኑ ቀናት ቤተሰብ ዚያራ ቤተሰቦቿጋ ሄዳ ቆይታበት .... ቤቱ ቢወረው... ጥቂት ስንኞችን ቋጥሮ ሰደደላታ....
👇👇👇👇👇

ህመሜ ነሽ አንቺ ...
          አንቺው ነሽ ፈዋሹም፤
በናፍቆት ስሰቃይ..
               እኮ ማንን ልሹም?፤
ሁሉም ህመም ሲሆን...
                    ትልቁ ትንሹም፤
አለሁልህ ካላልሽ...
                ንጋቶች አይመሹም።


ፉአድ
ያልተዘወጃቹ ሸባቦች....
አላህ ይዘውጃቹ አቦ...
አሚን በሉ🤲🥰

❤️❤️❤️🌹❤️❤️❤️
Join & share us
ይጫኑ👉 @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

08 Oct, 17:43


#ወዳጆቼ … 😍
ለሌሎች በማሰብና በመጨነቅ ውስጥ
ከባድ ህመም አለው አይደል!?

#መፍትሔው ምን ይሆን....?


ዱንያ ላይ እንግልታችሁ ሲበዛ ጀነትን አስቡ፣
በበሽታ ወድቃችሁ ስትከርሙ ጀነትን አስቡ፣
መከራ ሲደራረብባችሁ ጀነትን አስቡ፣
ስትበደሉ ጀነትን አስቡ፣
ሐዘን ሲወርሣችሁ ጀነትን አስቡ፣ 
ስትንገላቱ ጀነትን አስቡ፣
ሸክማችሁ ሲበዛ ጀነትን አስቡ፣
ያሰባችሁት ሲዘገይ ጀነትን አስቡ፣
በዱንያ ድካሞች ላይ ሁሉ ጀነትን አስቡ፣
ሁሌም አሻግራችሁ ጀነትን እዩ፡፡

ጀነትን ስታስቡ ችግራችሁ ይከስማል፣
ህመማችሁ ይቀልላል፣
መከራችሁ ይወገዳል፣
ድካማችሁ ይጠፋል፣
ሸክማችሁ ገለባ ይሆናል፣
ሐዘናችሁ ይረሳል፣
ጉዳታችሁ ያንሳል፡፡

ጀነትን አስቡና ኢንሻአላህ ነገ እናርፋለን በሉና ታገሱ፤
ኢንሻአላህ ነገ እንካሳለን በሉና አላህ የወደደላችሁን ዉደዱ፣
ኢንሻአላህ ነገ እንደሠታለን በሉና በሐዘናችሁ ተጽናኑ፡፡

ጀነትን ስናስብ ጀነት ዉስጥ አብዝተን የምንናፍቃቸው ረሱላችን አሉ፤
ምርጦቹ የአላህ ነቢያት አሉ፣
የምንወዳቸው ሶሐቦች አሉ፣
ደጋግ የአላህ ባሮች አሉ፣
ዱንያ ላይ ልናገኛቸው ተመኝተን ሳናገኛቸው ወደ አኺራ የቀደሙን ተናፋቂዎች ሁሉ አሉ፡፡

ጀነት ዉስጥ ዐይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ በልብ ላይ ዉልብ ብሎ የማያውቅ ፀጋ የተባለ ሁሉ አለ፡፡
ጀነት ዉስጥ ዱንያ ላይ ስንወደው የነበረ ነገር ሁሉ አለ፣
ዕረፍትና መዝናናት አለ፡፡
ለዚህ ሁሉ ስንል ጀነትን እናስባለን፡፡
ጀነትን ስናስብም የዛሬ መከራችንን ሁሉ እንረሳለን፡፡
ጀነት የብርታት መርፌያችን ናት፡፡
ጀነት ጉልበታችን ናት፡፡  

ወዳጆቼ!
የዱንያን ላይ ችግሮች አትፍሩ፣
በመከራ እንግልቶቿም አትሸበሩ፡፡
ሁሉም በጎ ፍሬ አላቸዉና አትደናገጡ፡፡

ወዳጆቼ … ጀነት .. ዱንያ ላይ ያሳለፍነዉን መከራና ችግር ሁሉ ወዲያው እዚያ እንደገባን በቅጽበት የምንረሳበት ሁሉ ሞልቶ የተትረፈረፈበት የድሎት አገር ነው፡፡

በርግጥ ብዙ ነገሮች ጉዳታችን ሁሉ አጠቃለው የመካስ ጉልበት የላቸዉም፡፡ ጀነት ግን ከመጠን በላይ የምንካስበት አገር ነው፡፡

የሙእሚን ዕረፍቱ ጀነት ነው፡፡
አላህ ሆይ ጀነትህን ስጠን፡፡
ለብርቱ ባሮችህ ያዘጋጀኸውን ምርጥ ስጦታ ሸልመን፡፡

ከሶባሐል ኸይር መጽሐፍ የተወሰደ


Join & share us
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

06 Oct, 18:49


🫰እኔ ምላቹ...

ሰው ግን... እንዴት ስለራሱ ብቻ
እያሰበ መኖር ይችላል?


እስቲ እንዴት?
ንገሩኝ

"እኔም አማረኝ💔!"


Join & share
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

03 Oct, 18:46


በማፍቀር ውስጥ ደስታ...
ለሰሚው ቢከብድም፤

ከእልፍ ሀዘን መሀል...
ሀሴትን አልክድም።



"አላህ በሀላሉ ያስደሳን አቦ!"
ፉአድ አ/ሐሚድ


Join & share
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

01 Oct, 08:38


"ቆይ አባት መጣሁ"

"አባቴ!"

"አቤት ልጄ?"

"እየሱስ ያድናል"

"ምነው ልጄ ሰላምታ አይቀድምም?"

"እሺ ይቅርታ! ደህና ዋሉ አባት?"

"አልሀምዱሊላህ የኔ ልጅ:: አንቺስ ታዳ?"

"ደህና ነኝ ጌታ ይመስገን"

"እዚህ አደባባዩ ላይ ቆመሽ እየሱስ ጌታ ነው ስትይ ሰማሁ ልበል?"

"አዎ አባባ እየሱስ ጌታ ነው::ጌታን ይቀበሉ"

"ለመሆኑ ልጄ እንዲህ ሰው በተሰበሰበበት እንድትሰብኪ ማን ፍቃድ ሰጠሽ?"

"አልገባኝም"

"መፅሀፋቹ አደባባይ ላይ እንድታወሩ ይፈቅድልሻል ልጄ?"

"እንዴታ! ወንጌልን ለዓለም ሁሉ እንድንሰብክ ጌታ አዞናል::ወንድ ሴት እያሉ መለያየት የእስልምና ብቻ ነው፣ በዛ ላይ ሴቶች በእስልምና ነው የተበደሉት ::"

"ተይ ልጄ የማታውቂውን አታውሪ: እስቲ 1ኛ ቆሮንጦስ 14:34 ክፈቺና አንብቢ"

"ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ: ህግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና:: ለሴት #በማህበር መካከል #መናገር_ነውር_ነውና ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ" (ፊቷ እየቀላ ነው ) ማንበቧን አቋረጠች

"ምነው ልጄ ዝም አልሽ?"

"በፍፁም ይሄን አንቀፅ ከዚህ በፊት አንብቤው አላውቅም"

"አውቃለው ልጄ፣1ኛ ወደ ጢሞቲዎስ 2:12 ብታነቢ ደሞ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም ይላል"

"በእየሱስ ስም"

"አሁን ውይይታችንን እንቀጥል ወይስ...?"

"ቆይ አባት መጣሁ" (በዛው እብስ አለች!!!)
.
"እነዚያ ተውራትን የተሸከሙ ምሳሌያቸው ማር እንደተሸከመች አህያ እንጂ ሌላን አይደሉም።
©elaftube

Join & share us
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

29 Sep, 04:08


"Giving charity extinguishes the wrath of God."

"ሰደቃ መስጠት የአላህን ቁጣ ታጠፋለች።"

Prophet Muhammad ﷺ
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ

Join & share us
@rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

27 Sep, 06:47


የኔ ነብይ🥰
ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም

Join & share us
👉 @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

22 Sep, 19:28


የኔዋ ማማዬ ኧረ ቃልም አጣው፤
ስጠራሽ ወይ በይኝ ካልሆነ ተቀጣው።

ማማ ማማ ስል ነው የፈታሁ አንደበት፤
ስምሽ ይክበርልኝ ስቀኝ ልኑርበት።

ብርታቴ ሁኚና ዳገቱን ልጋፋ፤
ሀያትሽ ረዝሞልኝ አሰኚኝ አንጋፋ።

ፉአድ አብዱልሐሚድ

🌹 Join & share 🌹
      @rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

09 Sep, 20:07


ሶብር🌹

👉ትግስት የዚህ አለም ሀብት የመጭው አለም ስኬት ናት። አላህ ለታጋሾች ትልቅ ስጦታን ሰጣቸዋ በገነትም አበሰራቸው።

وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡

'👉'ትግስት ከኢባዳዎች አንዱና ምንዳውም የላቀ ነው። አላህ ትእግስትን ከሶላት ጋር አብሮ በማቆራኘት ጠቅሶታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡


Join us
T.me/rasn_fllega

🌙 ራስን ፍለጋ(islamic)

05 Sep, 18:01


Join us
T.me/rasn_fllega

1,202

subscribers

614

photos

139

videos