ለሙስሊሟ እህቴ

@lemuslimuaehte


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
بسم الله الرحمن الرحيم
በቻናላችን
ዲናዊ እውቀቶች
ስለሒጃብ ማብሪራያዎች
ስለ ትዳር ምክሮች



እናንተን ያዝናናል ያስተምራል የምንላቸው
በአላህ ፍቃድ ለናንተ እናደርሳለን።

ከናንተ ሚጠበቀው join ማረግ ነው።
@lemuslimuaehte

for any comment 👇
@fitayebot

ለሙስሊሟ እህቴ

17 Oct, 03:10


በእነዚህ ከባባድ የፈተና ማዕበሎች ውስጥ የሰው ልጅ ልብ በቁርዓን እንጂ ፅናት/መረጋጋት የለውም።

የአለማቱ ጌታ እንዲህ ብሏል:–

ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ
" እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ"
---------
#صباح_السرور
@Munajahh

ለሙስሊሟ እህቴ

14 Oct, 18:18


ሞትክ ማለት እዛው በስብሰህ ቀረህ ማለት አይደለም!ይሄ የካፊር አስተሳሰብ ነው! ሞትክ ማለት ከስራህ ጋር ተገኘህ ማለት ነው!!
እዚህ ዱንያ ላይ የሰራሃው ስራ ነው አኼራ ላይ ያንተን ማንነት የሚወስነው❗️❗️
 
ምን ላይ ነህ!? ማን ላይ ነሽ!? ራሳችንን እንፈትሽ! ሙስሊም ስለሆን ብቻ ጀነት የለም ወይም ስማችን የሙስሊም ስለሆነ ብቻ ጀነት አንደምገባ የምናስብ አለን እውነታው ግን እንደዛ አይደለም! ጀነት ማንም ሩጦ ሂዶ የሚገባበት የዱንያ ቤት አይደለም። እንዘጋጅ እንሽቀዳደም! ከወንጀል እንራቅ ወደ አላህ እንመለስ!

ለሙስሊሟ እህቴ

14 Oct, 07:38


🔖 ውድ ስለሆንሽ......!

ወንድ ልጅ አንቺን መጨበጥ እርም ተደረገበት‥
ውድ ስለሆንሽ ወንድ ልጅ በክብር ቤተሰብሽ ጋር መጥቶ እስካልጠየቀ ድረስ ዝምብሎ
#ካንቺ መለፍለፍ እርም ተደረገበት
~አሏህ የሰጠሽን ክብርና ቦታ
የትም… አትጣይው ጠንቃቃ ሁኝ ።

ለሙስሊሟ እህቴ

14 Oct, 03:45


ብዙ የትዳር ጥያቄዎች መጥተውልኝ
እንቢ አልኩ ማለትሽ ትዳር አይሆንሽም።
~
ይልቁኑ አላህን የሚፈራ፣በዲኑ ጠንካራ
የሆነ ሰው ከመጣ ምንም ሳታመነቺ ትዳሩን
ተቀበይ ዝም ብለሽ እድሜ እየቆጠርሽ አትኑሪ።

አላህ ለእህቶቻችን መልካም ትዳር ይወፍቅልን!

ሰባሐል ኸይር

ለሙስሊሟ እህቴ

13 Oct, 11:10


ትዕግስት ብዙ ችግሮች ይገፋሉ!

ችግሮች ውስጥ ደግሞ ብዙ ትምህርቶች ይወሰዳሉ። ብዙ ቀናቶች አሉ የማያልፉ የሚወስሉ ወላሂ ግን ይታለፋሉ። አልሃምዱሊላህ

ለሙስሊሟ እህቴ

12 Oct, 19:31


☀️ወንድሜ
ፎቶዋን መሰብሰብ ትተህ
መህሯን ሰብሰብ አድርግ

ለሙስሊሟ እህቴ

07 Oct, 07:07


~ደስ የሚለው ነገር…ጠዋት ላይ የምትወጣው ፀሐይ ብቻ አይደለችም፡፡ለመኖር ተስፋ እንዲኖረን የሚገፋፉ መልካም ሰዎች፣ማማረር እንደማይገባንና በሕይወት ለመቆየት ብዙ ምክንያት እንዳለን የሚመመክሩ ደጋግ ባሮችም አብረዋት ይወጣሉ፡፡ አላህን የሚያስታውሱን ዉብ ፊቶችም ይወጣሉ፡፡

ነግቶ እስክናያቸው የምንጓጓላቸው፣ የምንወዳቸው፣ የምንናፍቃቸው ሰዎችም ይወጣሉ፡፡ አላህ ያቆይልን።

እናንተን በማየቴ ደስ ብሎኛል በሉ፡፡
ተደሰቱ!።ሰዎችም ከአንደበታችሁ በሚወጣው ቃል ይደሠቱ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

ለሙስሊሟ እህቴ

07 Oct, 06:13


«ዛሬን በደንብ ኑር !»

አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን የሚመነጩት ልንሰራ ያሰብነው ነገር ከባድ ወይም ብዙ ስለሆነ አይደለም የጀመርነውን ቀላል ነገር ስላልጨረስን ነው። ትላንት አልፏል አንጨብጠውም ነገንም  ገና አላየነውም ማስተካከል የምንችለው ዛሬን ነው ያውም አሁንን።

ለሙስሊሟ እህቴ

06 Oct, 20:22


ከአንድ ሰአት በፊት በአዲስ አበባ በአንዳንድ ቦታዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶዋል።
የወንጀላችን ብዛት ምልክት ነዉ ሁላቹም በያለንበት ዱአ እናድርግ ተዉበት እናድርግ!!

لله
ከፈለገ በአንድ ሴኮንድ ያጠፋናል ወላሂ ምን ይሳነዋል ጥፋታችንን አይቶ አይቶ ዝም ብሎ ብሎ አንዴ ሲይዘን ግን አያያዙ የከፋ ነዉ!!

ኢላሂ ሀያልነትህን አሳይተህናል እኛ ደካሞች ነን ይቅር በለን🤲

ለሙስሊሟ እህቴ

04 Oct, 19:00


....የገዳ ስርዓት⁉️

እኛ ሙስሊሞች ነን ገዳው አይጠራንም፡
ይህ አይነት ስርዓት አያካትተንም፡
የአምልኮ ተግባር ከአሏህ ውጭ አይሆንም፡

ያኮረፈ ያኩርፍ ርር ይበል ድብን፡
የጌታችን ቁጣ በላዕ እንዳይወርድብን፡
ከገዳ አስተሳሰብ ከመገለል አለብን፡

የኦሮሞ ጀግኖች ኢስላም ያነፃቸው፡
ከሰማያት በላይ አንድ ነው ጌታቸው፡
አሏህን መገዛት ይህ ነው አላማቸው፡
በዚህም ረገድ ውብ ታሪክ አላቸው፡

ጥቁር ቀይና ነጭ ከለር አናመልክም፡
የፀዳ እምነት አለን ዛፍ አንታከክም፡
አሏህ የፀዳ ነው የለም ጥቁር ጌታ፡
የዚህ ተረት አማኝ ያስቡ ቀጥታ፡

ብርሀን ጨለማ ሁሉን የፈጠረው፡
ለሰውም ለጅንም ጥበብ ያስተማረው፡
ሰወችን ከሌሎች መርጦ ያከበረው፡

ብቸኛው ፈጣሪ አሏህ ነው ጌታችን፡
ጉድለት የለበትም ውቡ እስልምናችን፡
ዋቃ እሚባል ኮተት የለም በዐዕምሯችን፡

ምንም ስያሜ ስጥ ዋቃም በል ጉረቻ፡
ጀበናም በል ስኒ ድስትም በል ሙሀቻ፡
ጥቁር ነጭና ቀይ አቅማዳም ሽልቻ፡
እኛን ሙስሊሞች ነን የለንም ኢሬቻ፡

ግፍ እየተሰራ በዚህ ሁሉ መዓት፡
የአጋንንት አምልኮ የሸይጦን ግብዓት፡
እንደዚህ ነው ለካ የገዳ ስርዓት⁉️

የኦሮሞ ሙስሊሞች ከዚህ ዘግናኝና የሽርክ ተግባር ተጠንቀቁ‼️

ይህ እጅግ ዘግና ለአዕምሮ የሚከብድ ለመናገር የሚቀፍ ከኢስላም የሚያሶጣ አስተሳሰብ ነው።

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

ለሙስሊሟ እህቴ

04 Oct, 12:10


• ድብቅ መልካም ስራዎች በጣም በምታቃጥል ፀሐይ ውስጥ ቀዝቃዛ ጥላ ነውና‥ በአንተ እና በአላህ መካከል ብቻ የሚታወቁ መልካም ስራዎች እንዲኖርህ ጥረት አድርግ።

ለሙስሊሟ እህቴ

04 Oct, 04:52


#ምላስ
የሰው ምላስ በአጉሊ መነጽር ሲታይ ይህን ይመስላል ወጣ ብለው ሚታዩት ነገሮች(taste bud) ጣእም ሚለዩልን ህዋሶች ናቸው👅
የሰው ምላስ ጣፋጭ፣ጎምዛዛ ፣ ጨዋማ እና መራራ ምግቦችን የመለየት ኃላፊነት ያላቸው ከ2,000 እስከ 8,000 የሚደርሱ የጣዕም መለያ taste bud ይዟል።
እያንዳንዱ ሰው ከሌላው የሚለይ #ልዩ የምላስ #አሻራ አለው
የምላስ የላይኛው ክፍል ልዩ የሆነው ክፍል ሲሆን
ሁለት ሰዎች አንድ አይነት የምላስ ቅርፅ ፈፅሞ አይኖራቸውም። #ሱብሃን_አላህ
وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?›

ለሙስሊሟ እህቴ

03 Oct, 14:14


መርየም ቢንት ዒምራን………

አንዳንዴ ለምሬት ቶሎ ከመገስገስ፡
የመጣን መቀበል ዋጋ አለው መታገስ፡

.....አወ ትዕግስት ማለት...

الصّبرُ شجرةٌ جذورها مرة وثمارها شهية.

-ትግስት ሥሩ የመረረ ፍሬው የሚጣፍጥ ዛፍ ነው።

قال الله عن مريم عليها السلام

فَأَجَاءَهَا الْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ النَّخْلَةِ قَالَتْ يَا لَيْتَنِي مِتُّ قَبْلَ هَٰذَا وَكُنتُ نَسْيًا مَّنسِيًّا

ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡


ድንቋ ሴት ይህን ስትመኝ...!!

ማህፀኗ ውስጥ ያረገዘችው ነብይ መሆኑን አታውቅም ነበር።


መቼ ጠበቀችው ያንን ጀግና ነብይ፡
አንቀልባ ላይ ሆኖ እንደሚተነብይ፡


....ጀግናዬ ...አንዳንዴ…………

   ባልደረሱብኝ ባልነኩኝ ብለህ የምትጠላቸው ከባባድ ክስተቶች ምን አልባትም ተኣምር የሆነ ስኬት ያረገዙ ፈተናዎች ሊሆኑ ይችላሉና ታገስ ነው የምልህ እሽ
⁉️

ለሙስሊሟ እህቴ

02 Oct, 04:12


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"الْمُؤْمِنُ مَنْ أَمِنَهُ النَّاسُ عَلَى أَمْوَالِهِمْ وَأَنْفُسِهِمْ، وَالْمُهَاجِرُ مَنْ هَجَرَ الْخَطَايَا وَالذُّنُوبَ"
"ሙእሚን ማለት ሰዎች በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ላይ የሚያምኑት ነው። ሙሃጂር ማለት ሃጢአትና ወንጀሎችን የተወ ነው።"
[ኢብኑ ማጀህ፡ 3934] አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

ለሙስሊሟ እህቴ

01 Oct, 16:04


አስደሳች ~ ዜና  ለሴቶች በሙሉ!
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

🔺እነሆ  አድስ  የኪታብ  ቂርአት  ሊጀመር ነዉ!

📚ኪታብ፦ ሪሳላቱ አል_ሒጃብ!

✍️ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን رحمه الله

🎙በወንድም አብዱረዛቅ ኢብኑ ሙራድ

ዘወትር  ቅዳሜ  10:30ጀምሮ


ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ
44 ማዞሪያ አ-ተህሲን መድረሳ ነው የሚቀራው ማንኛውም በአካባቢው የምትገኙ ሙስሊም እህቶች በዚህ ሰአት  መታችሁ የዲናችሁን ጉዳይ መማር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ለሙስሊሟ እህቴ

30 Sep, 18:35


ከሶላት በኋላ አየተል ኩርሲ መቅራት ቱርፋት

ለሙስሊሟ እህቴ

30 Sep, 06:12


💬ትኩረት !

ትኩረትህ አንድ ነገር ላይ ብቻ ሲሆን ያንን ነገር ሊያሳድጉት የሚችሉ ብዙ ሀሳቦችን ማፍለቅ ትችላለህ  ጥሩ ቦታ ላይ ስታተኩር  ታድጋለህ መጥፎው ላይ ስታተኩርም ራስህን ይበልጥ ትጥለዋለህ  !

«ስለዚህ ለውጥ ስትፈልግ ትኩረት የምታደርግበትን ቦታ አስተካክል !»

ለሙስሊሟ እህቴ

29 Sep, 05:31


~ብዙ ግዜ ስለ'ዛ አባት አስባለሁ…ሱብሒ ወጥቶ ሲደክም ዉሎ አምሽቶ ስለሚገባው አባት፤ ልጆቼን እንዴት ላሳድግ ብሎ በሀሳብ እየተብሰለሰለ ያለ እንቅልፍ ስለሚያድረው አባት፣ በባስ እየሄደ በታክሲ ልጁን ስለሚልከው አባት፣ ጫማ ሳይቀይር ልጁን ስለሚያስዘንጠው አባት፣ ባገኘ ጊዜ በሰባት እጆቹ አስቤዛ ሰብስቦ ስለሚገባው አባት፣ ባጣ ጊዜ ሐዘን ፊቱን ስለሚያጠቁረው አባት፣ በዱንያ ፈተናዎች ላለመዋጥ ስለሚታገለው አባት፣ ሀሳብ ጭንቀቱ ሁሉ ስለ ልጆቹ የወደፊት ዕጣፈንታ ስለሆነው አባት፣ በዕዉን በህልሙ ልጆቼን! የሚል ቃል ከአፉ ስለማይጠፋው አባት፡፡

ድሮ ያኔ አባትነት ሲባል ቀላል ነገር ይመስለኝ ነበር፤ እሱ ልጆቼን! ሲል አፉ ስለለመደበት ብቻ ይመስለኝ ነበር፡፡ ልጁ ሲወድቅ እኔን ድፍት ያድርገኝ ሲል ልቡ የሚሰነጠቅ፣ አንጀቱ የሚተረተር አይመስለኝም ነበር፡፡

አባት .... ሾፌር ሲሆን ልጁ ይደቀንበታል፣ ስልክ ሲደወል ልጄ ምን ሆና ይሆን? የሚል ሀሳብ ቀድሞ ጭንቅላቱ ላይ ይመጣበታል፤ መንገደኛ ሲሆን መንገዱ በረዘመ ቁጥር የልጆቹ ናፍቆት ይጠናበታል፡፡

አባትህ እንዴት እንዳሳደገህ ብታውቅ ኖሮ ባንተ ላይ ያለው ሐቅ እንጂ በሱ ላይ ያለህ ሐቅ ትዝ አይልህም ነበር፡፡

ጌታዬ ሆይ ባለፈው ዕድሜያችን ከወላጆቻችን አንፃር ያጎደልነዉን ሁሉ ይቅር በለን፤ በተቀረው ዕድሜያችን የምንኻድማቸው አድርገን፡፡ 
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

ለሙስሊሟ እህቴ

28 Sep, 10:34


ታሪኳን ስትነግረን እንዲህ ትላለች:-✈️
ኡስታዛችን ነበርና ወደ ስምንት ጁዝዕ እሱ ዘንድ ካስደመጥን በሇላ በድንገት ሙሉ በሙሉ ሴቶችን ማሳፈዝ እንዳቆመ የመድረሳው ሀላፊዎች ያሳውቁናል።
በዚህን ጊዜ እኔ እና ጓደኞቼን ሴት ኡስታዛ ጋር ያዘዋውሩናል። እሷም የቀደመው ኡስታዛችን እናቱ ናት!!

ሁላችንም ጭራሽ እስከምንረሳው ድረስም የኡስታዛችን ዜና ይቋረጣል ። ከአስር ወራት በሇላም እኔ እና ጓደኞቼ ቁርዓን ሙሉ በሙሉ ሀፍዘን ድል ያለ የሂፍዝ ምርቃት ድግስ ተደረገልን። በድግሱም ዕለት ኡስታዛዬ ከጓደኞቼ አርቃ ይዛ ወሰደችን እና «አንቺን ከቤተሰቦችሽ ሊያጭሽ የሚፈልግ ወጣት አለ» አለቸኝ ስለ ወጣቱ አንዳንድ ነገር ነገረችኝ እና ከሱ ጋር ይወያዩበት ዘንድ የአባቴን ስልክ ቁጥር ሰጠዋቸው እንደተባለውም አወሩ እና ከሁለት ቀን በሇላ ቤታችን መጡ

ከዛማ የመጡት ...ሴቷ ኡስታዛዬ ባለቤቷ እና ልጃቸው [ከአስር ወራት በፊት የነበረው ኡስታዛችን!!! ] ሆኑ እላቹሃለው

🟤ድንጋጤዬማ ዛሬ ድረስ ትዝ ይለኛል...

.....ብቻ ቤታችን መቶ ኒቃቢስትም ስለሆንኩ ሸሪዓዊ እይታ ከተያየን በሇላ እንዲህ አለኝ «ባንቺ እንደተፈተንኩ ባወቅኩ ግዜ ከሸይጣን በሮች መካከል አንዱ ሊከፈት እንደሆነ ተሰማኝ ...
እናማ በአሏህ እርዳታ ሴቶችን ማሳፈዝ ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ..... ይህም ሸይጣን አነስተኛ መንገድም ቢሆን ወደኔ እንዳያገኝ ነበር.... በዚህን ግዜ አንቺን ኒካህ ለማሰር ዝግጁ እንዳልሆንኩም ስለማውቅ ከአንቺ ጋር ሊያገናኘኝ የሚችልን መንገድ በሙሉ ገታው...ልቤንም ዲኔንም አንቺንም ጭምር እንዳላበላሽ ስል...ነገር ግን በተውኩሽ ግዜ በምድር ላይ እጅግ ከማምናት ፍጡር ....እናቴ ጋር ነበር የተውኩሽ
ጎበዝ ተማሪ ናት ወደ ፊት ላይም ታታሪ የዲን አስተማሪ መሆን ትፈልጋለች ብዬ አደራ አልኳት...» አሏህም የመልካም ሰሪዎችን ስራ ከንቱ የሚያደርግ አልነበረም።
ራሳቸውን አስጠበቁ ጥብቆችንም ገጠማቸው ..."መልካሞችስ ለመልካሞቹ የተገቡ አይደል"

«...ለአስተማሪነት የቀረበ...
ኮፒ🌸

3,326

subscribers

1,011

photos

196

videos