የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

@geezg


እግዚአብሔር በረዳን መጠን በሚጋባን መልኩ በቴሌግራም የግእዝ ትምህርት ሁሉንም የሚመጥ አቀራረብ እነሆ!!!
ለየትኛውም አስተያየትና ጥያቄ
@Dn_Aderu ላይ ማድረስ ይቻላል

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

20 Jan, 06:56


ባሕርኒ ርእየት ወጎየት
ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ
አድባር አንፈርዐፁ ከመ ሐራጊት።
ትርጉም፦ባሕር አየች ሸሸችም
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ
ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ኮረብቶችም እንደ ጡቦቶች ዘለሉ። መዝ 113፥3
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።አሜን(፫)

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

11 Sep, 13:47


ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
👇
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ጠልን ይጠግባል።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 11

ወይረውዩ አድባረ በድው ወይትሐሠዩ አውግር ወይቀንቱ
👇
የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 12

ወይለብሱ አብሐኰ አባግዕ ወቆላትኒ ይመልኡ ስርናየ ይጸርኁ እንዘ ይሴብሑ
👇
ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 13
እንቋዕ አብጽሐክሙ:


እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልካም አዲስ ዓመት!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

16 Apr, 01:31


ምንተ ትኀሥሣሁ ለሕያው ምስለ ምውታን? ተንስአ ኢሀሎ ዝየ ።ሉቃ ፳፬:፭

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ?  ተነስቷል እንጅ በዚህ የለም።  ሉቃ ፳፬:፭  እንኳን አደረሰዎት መልካም በዓል!!!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

07 Jan, 02:31


እንኳን አደረሳችሁ!!!!!!!!

===============================
ወይቤሎሙ መልአክ ኢትፍርሁ እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሓ ዘይከውን ለኵሎ ሕዝብ ።
እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘዉእቱ ክርስቶስ  እግዚእ ብሩክ  በሀገር ዳዊት። ሉቃ ፪÷፲

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
መልአኩም እንዲህ አላቸው እነሆ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች
እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
ሉቃ ፪÷፲
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም በጤና አደረሳችሁ።  * መልካም በዓል
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

11 Sep, 00:55


ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
👇
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ጠልን ይጠግባል።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 11

ወይረውዩ አድባረ በድው ወይትሐሠዩ አውግር ወይቀንቱ
👇
የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 12

ወይለብሱ አብሐኰ አባግዕ ወቆላትኒ ይመልኡ ስርናየ ይጸርኁ እንዘ ይሴብሑ
👇
ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ።
መዝሙረ ዳዊት 64 : 13
እንቋዕ አብጽሐክሙ:


እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ መልካም አዲስ ዓመት!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

07 Jan, 04:09


እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ሠናይ በዓል ለኩልነ።

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

29 Aug, 18:49


ቀን 23/12/2013ዓም
ሰዓት 9:00 pm
ለተክለ ሃይማኖት ዋዜማ

ዋዜማ ቅኔ
ሰርቁ ንብረተከ ስሩቃነ ፃድቅ ፃድቅ ለሐብተ ማርያም ካልዑ
እስመ እግረ መስኮተ ቤትከ ሰቢሮሙ ቦዑ
ቀኖና ወፆም ዘበቅጽረ ቤትከ ጸንዑ
ወተእኅዙ ካዕበ እንዘ ይወጽዑ
ቅጽረ ቤቱ ለፃድቅ ገርድዑ

አማርኛ
የሃብተ ማርያም ሁለተኛ አቡነ ተክለሃይማኖት የገብረ መንፈስ ቅዱስ ሌቦች ፆምና ቀኖና ንብረትህን ሰረቁ
በቤትህ ቅጽር የጸኑ ፆምና ቀኖና ሌቦች ሰብረው ገብተዋል እና
የዳኛ ተክለ ሃይማኖትቤትየቤቱን ቅጥር ሲወጡ ተያዙ
ሙያ
ሰርቁ=>ማሰርያ ይስባል እንጅ አይሳብም
ንብረት=>የሰቁ ተሳቢ
ከ=>ዝርዝር
ስሩቃን=> የቅኔ ባለቤ
ፃድቅ=> የስሩቃን ዘርፍ
ፃድቅ =>አሰሚ የወጣበት
ለ=>ዘርፍ ደፊ ዘርፍ ደፊነቱ ደፊናቱ ካልኡ ላለው
ሐብተ ማርያም=> ይቅኔ ባለቤት
ካልዑ=> የፃድቅ ቅጽል
እስመ=>ያለው አገባብ ፍቹ ና ሙያው አስረጅ
እግር መስኮት ምሳሌ መስኮት ሰም እግር ወርቅ ተመስሎ የስቢሮሙ ተሳቢ

ከ =>ዝርዝር
ሰቢሮሙ => ቦዝ
ቦዑ=>ብሎ እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል
ወ=> ያለው አገባ ፍቹ ና ሙያው አጨፋሪ
ቀኖና ወፆም=> በወ ተጫፍረውየአስረጅ ባለቤቶች

ዘ => ያለው አገባብ ፍቹ የ ሚያው ቅጽል ቅጽልነቱ ቀኖ ወፆምል ላለው
በ=> ያለው አገባብ ፍቹ በቁም ቀሪ ሙያው ማድረግያ
ቅጽር => በየውደቀበት ማድረጊያ
ቤት=>የቅጽር ዘርፍ
ከ=> ዝርዝር
ጸንዑ=>ብሎ እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
ወ=> ያለው አገባብ ፍቹ 'ም' ሙያው ደጋሚ
ተእኅዙ=> ማሰርያ ይስባል እንጅ አይሳብም
ካዕበ => ዳግመኛ ሙያው አንቀጽ አጎላማሽ አጎላማሽነቱ ተእኅዙ ላለው
እንዘ => ያለው አገባብ ፍቹ ሲ ሙያው ማንጸርያ
ይወጽዑ=>ብሎ እንዳያስር እንዘ ይጠብቀዋል
ቅጽር=>ተሳቢ
ቤት => የቅጽር ዘርፍ
ለ=> ለዘርፍ አያያዥ አያያዥነቱ ቤተ ፃድቅ የሚይሰኝ
ፃድቅ ገርድዑ=> ምሳሌ ገርድኡ ሰም ፃድቅ ወርቅ ተመስሎ የአያያዝ ባለቤት

እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ አመታዊ የእረፍት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!!!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

21 Aug, 09:08


🎄🎄🎄ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍስሐ ምጡቀ🎄🎄🎄

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅ እና እሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ሰላም እላሁ!!

ትፍስሐተሰ ተፈሳሐኩ በፍልሰትኪ ይእዜ። ገፀ ዚአኪ እሬኢ ማእዜ።

እንቋዕ አብጽሐነ አብጽሐክሙ ለዕርገተ እመ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም!!!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

19 Aug, 04:54


ቅኔ ዘአበው በእንተ ምስጢረ ደብረ ታቦር

🌿🌿🌿 ጉባኤ ቃና 🌿🌿🌿

ሙሴ ኢትኅድግ መቃብረከ ክሱተ፣
እስመ እንተ ጴጥሮስ ቤት ኢይከውነከ ቤተ።

🎄🎄🎄ትርጉም🎄🎄🎄
🔵ሙሴ የተከፈተ መቃብርህን አትተው፣
🔴የጴጥሮስ ቤት ቤት አይሆንህምና።

🔔🔔🔔ምስጢር🔔🔔🔔

"የሰው ቤት ቤት ላይሆን ቤትህን አትልቀቅ" እንዲሉ
ሙሴ ከሞተ በኋላ በአካለ ነፍስ ወደ ደብረ ታቦር መምጣቱንና ተመልሶ መሄዱን ጴጥሮስም "ለሙሴና ለጴጥሮስ አንዳንድ ቤት እንስራ" ካለ በኋላ ቢቱ አለመሰራቱን ባለ ቅኔው አመስጥሯል።



🌿🌿🌿 ዘአምላኪየ ቅኔ 🌿🌿🌿

ውስተ ደብረ ምስጢር ታቦር እመ ትሬኢ ደመና፣
ኢይመስለከ ሙሴ ዘይወርድ መና፣
ደመና ታቦር ፍሉጥ አኮኑ እምደመና ደብርከ ሲና።

🎄🎄🎄ትርጉም🎄🎄🎄

በምስጢር ተራራ ታቦር ደመናን ብታይ ሙሴ! መና የሚወርድ አይምሰልህ። ሲና ከተባለ ተራራህ ደመና የታቦር ደመና የተለየ ነውና።

🔔🔔🔔ምስጢር🔔🔔🔔

ቀድሞ በደብረ ሲና የታየው ደመና ለእነ ሙሴ የሰማይ መናን የሚያዘንብላቸው ሲሆን በደብረ ታቦር በኤልያስና በሙሴ በሐዋርያትም ፊት የታየው ደመና
"ይህ ልጄ ነው እርሱን ስሙት" የሜል የወልድን ነገር የሚያሰማ በመሆኑ!! ባለ ቅኔው ሙሴን ደመና ባየ ቁጥር መና ይወርድልኛል ብሎ የሚጓጓ አስመስለው ተቀኝተዋል።

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

05 Aug, 16:20


🌿በይነ ትሕትና ወንህጽ አባግዕ 'እለ አረጋዊ' ቀዳሚ
🌿እፎኑመ ዮሴፍ ባዕለ ጸጋ ይሰሚ

አማርኛ
የአረጋዊ በጎች ትህትና ና ንጽህና ሰለ ነዚህ ዮሴፍ እንዴት ባለ ጸጋ ይባል?

የቅኔ ሙያ

=>በይነ- አገባብ ፍቹ- ስለ - ሙያው ማንጸርያ
=>ትሕትና ንጽህ በወ ተጫፍረው አባግዕ - ምሳሌ - ትሕትና- ንጽህ ወርቆች- አባግዕ ሰሞች -ተመስለው- በይነ የወደቀበት ማንጸርያ (የማንጸርያ ባለቤቶች)

=>ወ - አገባብ ፍችው ና ሙያው አጫፋሪ
=>እለ -አገባብ- ፍችው - የ -ሙያው- አዠያዥ


=>አረጋ- የአዠያዥ ባለቤት
=>ቀዳሚ- ቅጽል -ቅጽልነቱ ለአረጋዊ

=>እፎኑመ - እንዴት ሙያው አንቀጽ አጎላማሽ- አንቀጽ አጎላማሽነቱ ይሰሚ ላለው
=>መ- ትራስ

=>ዮሴፍ- የቅኔ ባለቤት
=>ባዕል ጸጋ -የይሰሚ ተሳቢ
=>ይሰሚ - የቅኔ ማሰርያ

🌿መድኀኔአለም ገስጽ ኮሮና ዘተመነነ እምግብሩ
🌿እስመ ውስተ ምድር ሰባአ ንዋያቲከ ይዘሩ

አማርኛ

መድኀኔአለም ሆይ ከስራው የተና የሚያስጠላ የሆነ ኮረናን ገስጽ
በምድር ውስጥ (ወደ ምድር) ሰው ገንዘብህን ይበትናል እና

የ ቅኔ ሙያ

=>መድኀኔአለም -የቅኔ ባለቤት
=>ገስጽ - የ ቅኔ ማሰሪያ
=>ኮሮና- የይገስጽ ተሳቢ
=> ዘ -ያለው አገባብ ፍቹ የ ሙያው ቅጽል -ቅጽልነቱ ኮረና ላለው
=>ተመነነ- ብሎ እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
=>እም- አገባብ ፍቹ ከ ሙያው መነሻ
=>ግብር- የመነሻ ባለቤት

=>እስመ -አገባብ ፍቹ ና ሙያው አስረጅ- አስረጅነቱ ገስጽ ላለው
=>ውስተ- ያለው አገባብ ፍቹ ውስጥ(ወደ)

=>ምድር - ውስተ የወደቀበት
=>ሰብእ ንዋያት ምሳሌ - ሰብእ ወርቆች- ንዋያት ሰሞች- ተመስለው የይዘሩ ተሰተሳቢ
=>ይዘሩ- እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

29 Jun, 05:00


🎄🎄🎄ጉባኤ ቃና🎄🎄🎄

🌿🌿🌿ሰገራተ ዓለም ላዕካን ተፈስሑ መልዕልተ ቡራኬ አውዶሙ፣🌿🌿🌿

🌿🌿🌿አኮኑ ሞዕዎ ለዝንቱ ድንቃዌ ልዮን ጸሮሙ።🌿🌿🌿

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

09 May, 09:49


ጉባኤ ቃና
ሐና ትትፌሳህ በዘተጸውዐ ስማ፣
ድራረ ምሴት ትሕድስተ እስመ ረከበት በጻማ።

ትርጉም
ሐና ስሟ ስለ ተጠራ ትደሰታለች፣
የማታ እንጀራ(እደሳ) በድካም አግኝታለችና።

ምስጢር
የማታ እንጀራ(ብዙ ሀብት) ያገኛች እናት ስሟ በተጥራ ቁጥር ትደሰታለች።
እንዲሁም የእናት ምሳሌ የሆነችው ሐና በስተ እርጅናዋ ማርያምን ወልዳ ታደሰች እየተባለ ሲተረክላት ስመጥር ዝነኛ ሆነች።በማለት ተቅኝተዋል

ድንግል ሆይ ባንች መወለድ የእናትሽ የሐና እድሜ እንደታደሰ ሁሉ የኛም የጎሰቆለው ማንነታችን ይታደስ ዘንድ ምልጃሽ፣ ረድኤት፣ በረከትሽ አይለን አሜን!!!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

02 May, 01:53


አመ ሳልስት ዕለት ተንስአ እሙታን

በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ

ቅዳሴ ዲ

እንቋዕ አብጽሐነ አብጽሐክሙ ለብረሃነ ትንሳኤሁ በሰላም አሜን!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

30 Apr, 11:22


ተሰቅለ በእንቲአነ

ስለ እኛ ተሰቀል

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

25 Apr, 08:26


ጉባኤ ቃና
ውሰደው
ኦ አንትሙ አርድእተ ብዙህ ኩርጓኔ፤
ኢይከውን እንበለ ሆሳዕና አማኑኤል ቅኔ።
ይህ ለቅኔ ተማሪዎች ብቻ ነው

ዘአምላክያ

ህፃናት ኩሎሙ ዘበቤተ ሳዶቅ ሀና፣
ይትዋነዩ እንዘ የሀብዙ እንተ ቆጽል መና፣
ወአዕባን አብቀዉ አፉሆሙ ውስተ ቤቶሙ ሆሳዕና።

በሀናና በሳዶቅ ቤት ያደጉ ሁሉም ህፃናት የቅጣል እንጀራ እየጋገሩ ይጫወታሉ ። አልቃሾች አእባን ግን በቤታቸው ሆሳዕና ውስጥ አፋቸውን ከፈቱ

ሰም

መቼም ልጅ ሆኖ በየሰፈሩ የቅጠል እንጀራ እየጋገር ያልተጫወተ አንዱ ሲጫወት አንዱ አፉን ከፍቶ ያላለቀሰ የለም በሰሙ ይሄንን ሲያስታውስ

ወርቁ

ሰዎች ማመስገን ባቃታቸው ጊዜ ህፃናት እና የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተቅ ክርስቶስ እንዳመሰገኑ ያመለክታል

እንቋዕ አብጽሐነ ወአብጽሐክሙ ለበዓለ ሆሳዕና በጤና ወበ ሰላም አሜን!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

19 Apr, 15:41


ለቅኔ ተማሪዎች
ሙያው በዚህ መልኩ ይሆናል
!


ኢሰከበ= ያለው ማሰርያ ይስባል እንጂ አይሳብም
ሚመ= አንቀጽ አጎላማሽ አንቀጽ አጎላማሽነቱ ለ ኢሰከበ
ኒቆዲሞስ= የቅኔ ባለቤት
= ያለው አገባብ ፍቹ የ ሙያው ቅጽል ቅጽልነቱ ኖቆዲሞስ ላለው
= ያለው አገባብ ፍቹ በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ
ፍቅር= በ የወደቀበት ማድረጊያ
ወንጌል= የፍቅር ዘርፍ
ይፃሙ = ብሎ እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
ፍቅርቱ ወንግል= ምሳሌ
ፍቅርት= ሰም
ወንጌል = ወርቅ
ተመስላ=የአስረጅ ባለቤት
ኩለሄ=አንቀጽ አጎላማሽ አጎላማሽነቱ ትመጽዕ ላለው
እስመ =ያለው አገባብ ፍቹ ና ሙያው እስረጅ
ትመጽዕ = ብሎ እንዳያስር እስመ ይጠብቀዋል
= ያለው አገባብ ፍቹ ብቁም ቀሪ ሙያው ማድረግያ
ህልም= በ የወደቀበት ማድረግያ
ሰናይ ምሴት! መልካም ምሽት!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

19 Apr, 05:59


ኢሰከበ ሚመ ኒቆዲሞስ ዘበፍቅረ ወንጌል ይፃሙ፣

ፍቅርቱ ወንጌል ኩለሄ እስመ ትመጽዕ በህልሙ።


ትርጉም

የወንጌል ፍቅር በወንጌል ፍቅር የደከመ ኒቆዲሞስ ምንም አልተኛ፣

ፍቅረኛው ወንጌል ሁልጊዜ በህልሙ ትመጣለች እና።

ምስጢር

ሰም
አንድ ያፈቀረ ሰው ጓደኛው ሌሊት በህልሙ እየመጣች ምንም አይነት እንቅልፍ ሳይዞር እንዳደረ የሚያጠይቅ ሲሆን

ወርቅ

ወንጌልን ያፈቀረው ኒቆዲሞስ እንቅልፍን ወደ ጎን በመተው ሌሊት ሌሊት ከጌታ ዘንድ በመሄድ ለመማር ብዙ እንደ ደከመ
ያመልክታል

የቅኔውን ሙያ የሚፈልጉ ካሉ እመለሳለሁ።


የቃላት ትርጉም

ሰከበ =ተኛ
ኢሰከበ= አልተኛም
ሚመ =ምንም
ፃመወ =ደከመ

ኩለሄ =ሁልጊዜ
እስመ= እና
መጽዐ =መጣ
ትመጽዕ =ትመጣለች

መልካም ቀን ይሁንልን

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

13 Apr, 06:22


ሰላም ውድ የግእዝ ትምህርት ቤተሰቦች
እንደ ምን አላችሁ? ለብዙ ቀናት ተለያይተን ነበር እግዚአብሔር መልሶ ስላገናኘን ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን!

ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ትምህርታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
የናንተ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው
እንደ ምትከታተሉ አሳዩን

ማንኛውንም ጥያቄ እና አስተያየት
@Dn_Aderu ላይ ማድረስ ይቻላል

ግእዝ የአዳም ቋንቋ
ግእዝ የቤተክርስቲያኗ ሀብት
ግእዝ የምስጢር ቁልፍ
ግእዝ …





…ብዙ ነው

መልካም ቆይታ!!!

የግእዝ ትምህርት ለሁሉም

31 Dec, 19:17


1ኛ ♥️ ተስዓ ወተሰዓቱ በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ነው?
ሀ.፱፱
ለ.፺፺
ሐ.፺፱✔️
2ኛ ♥️ ማርያም ወማርታ.......ይትቀበልዎ ለክርስቶስ።
ሀ.ሮጹ
ለ.ሮጻ✔️
ሐ.ሮጽክሙ
መ.ሮጸት
3ኛ ♥️ ፀሐይ በምሥራቅ ወጣች ለማለት በግእዝ ትክክለኛው የቱ ነው።
ሀ.ፀሐይ ሠረቀት በምስራቅ
ለ.ፀሐይ ሠረቀት በምሥራቅ✔️
ሐ.ጸሐይ ሰረቀት በምስራቅ
መ.ፀሐይ ሰረቀት በምሥራቅ
4ኛ ♥️ 982 በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ነው?
ሀ.፱፻፹፪✔️
ለ.፱፻፰፪
ሐ.፺፻፰፪
መ.፱፼፹፪
5ኛ ♥️ ውእቱ ብሎ ሀገሩ ካለ አነ ብሎ......ይላል
ሀ.ሀገርከ
ለ.ሀገርየ✔️
ሐ.ሀገራ
መ.ሀገርኪ
6ኛ ♥️ ማርያም.........እምኩሉ ፍጥረት
ሀ.የዐቢ
ለ.ተዐቢ✔️
ሐ.አዐቢ
መ.ነዐቢ
7ኛ ♥️ መጽአት ማርያም ምስለ ገብርኤል ለሚለው የአማርኛ ትርጉሙ......ነው
ሀ.ማርያምና ገብርኤል መጡ
ለ.ማርያም ወደ ገብርኤል መጣች
ሐ.ማርያም ከገብርኤል ጋር መጣች✔️
8ኛ ♥️ መሰረተ ዜማ.....ያሬድ ካህን
ሀ.ወጠነ (ነ ጠብቆ)
ለ.ወጠኑ
ሐ.ወጠነ (ነ ላልቶ)✔️
መ.ወጠንክሙ
9ኛ ♥️ አእመረ ብሎ አእመርኩ ካለ ሰበከ ብሎ ምን ይላል?
ሀ.ሰበክኩ
ለ.ሰበኩ (ኩ ጠብቆ✔️)
ሐ.ሰበኩ (ኩ ላልቶ)
10ኛ ♥️ መድኃኒ እና ዓለም ሲናበቡ....ይሆናሉ
ሀ.መድኃኒዓለም
ለ.መድኃኔዓለም✔️
ሐ.መድኃኒዓለመ
መ.መድኃኔዓለመ
11ኛ ♥️ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ በግእዝ.....ነው።
ሀ.ማእዜ ትመጽኢ ኀቤየ
ለ.ማእዜ ይመጽእ ኀቤየ
ሐ.ማእዜ ትመጽእ ኀቤሁ
መ.ማእዜ ትመጽእ ኀቤየ✔️
12ኛ ♥️ ኢይፈርሆ ለሞት ወደ አማርኛ ሲተረጎም..... ይላል።
ሀ.ሞትን አልፈራውም✔️
ለ.ሞትን አልፈራትም
ሐ.ሞትን አላስፈራውም
መ.ሞትን አላስፈራትም
13ኛ ♥️ ተሰቅለ ክርስቶስ....... መስቀል
ሀ.ላእለ
ለ.ዲበ
ሐ.መልእልተ
መ.ሁሉም✔️
14ኛ ♥️ ክርስቶስ ሞተ ሞተ ዚአነ የሚለው ሲተረጎም...... ይሆናል።
ሀ.ክርስቶስ የእኛን ሞት ሞተ✔️
ለ.የእኛ ሞት በክርስቶስ ሞተ
ሐ.የእኛ ሞት ክርስቶስ ሞተ
መ.መልሱ የለም
15ኛ ♥️ እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን የሚለው ወደ አማርኛ ሲተረጎም?
ሀ.ንሐነ ንሰብክ ክርስቶስ ዘተሰቅለ
ለ.ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሀ ዘተሰቅለ
ሐ.ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ✔️
መ.ንሕነ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ
16ኛ ♥️ ደብረ መድኃኒት ከሚለው ቃል ዘርፉ ማን ነው?
ሀ.ደብር
ለ.ደብረ
ሐ.መድኃኒተ
መ.መድኃኒት✔️
17ኛ ♥️ ......ተሰቅለ ክርስቶስ ፀሐይ ጸልመ።
ሀ.ሶበ
ለ.አመ
ሐ.ጊዜ
መ.ሁሉም✔️
18ኛ ♥️ እናንተን አያሳየኝ የሚለው ቃል ወደ ግእዝ ሲተረጎም.....ይሆናል።
ሀ.ኪያክሙ ኢያርእየኒ
ለ.ኪያክን ኢያርእየኒ
ሐ.ለሊክሙ ኢያርእየኒ
መ.ሀ እና ለ✔️
19ኛ ♥️ ንሕነ ብለን ለሊነ ካልን አንትን ብለን ምን እንላለን?
ሀ.ለሊክሙ
ለ.ለሊክን✔️
ሐ.ለልየ
20ኛ ♥️ የ "መርሐ" አሉታ.....ነው
ሀ.ኢይመርሕ
ለ.አኮ መርሐ
ሐ.ኢመርሐ✔️
መ.አልመርሐ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መ/ር በትረማርያም አበባው ካሣ