gambella educational media

@gam051984


ትምህርታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ

gambella educational media

20 Oct, 15:20


Dear , we are pleased to inform that, result for the summer teacher's capacity building training have been officially released.
Trainees can check their result by visiting 
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://result.ethernet.edu.et and selecting the TDP option from the available list.

Note:
Candidates must use their registration number to access their result (e.g.: TDP0000016)
All candidates who sat for the exam can see their result
Only candidates who scored 70 and above will get an authorized certificate.

gambella educational media

17 Sep, 07:50


በጋምቤላ ክልል የትምህርት ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።

በክልሉ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

መስከረም 7/2017 ዓ.ም(የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ)

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ማበር ኮር እንዳሉት የትምህርት ጥራትን የማረጋገጡ ስራ ለመንግስት ብቻ የሚተው አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የህብረተሰቡ ድጋፍና እገዛ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለተጀመረው ጥረት መሳካት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ውጤታማ እንዲሆን የትምህርት ዘርፍ አመራሮች፣ መምህራን እና ወላጆች በቅንጅት እንዲሰሩም አቶ ማበር አሳስበዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ፖክ ካዊች በበኩላቸው በ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል።

በትምህርት ዘመኑ የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት እንዳይኖርና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቋረጡ የድጋፍ ስራዎችን እንደሚሰሩ  አስረድተዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ወላጆች እንዳሉት የተማሪዎች የውጤት ማጣት በትምህርት ዘመኑ እንዳይኖር ትምህርት ቤቶች በአግባቡ እንዲያስተምሩ ጠይቀዋል።

ተማሪዎች ከትምህርት ቤት መማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ ወደ ቤታቸው ሲመጡ እንዲያጠኑ የክትትል ስራዎችን እንደሚያከናዉኑ ወላጆቹ አረጋግጠዋል።

በዕለቱም የትምህርት ቁሳቁስ መግዛት ለማይችሉ ተማሪዎች ድጋፍ ተደርጓል።
@ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት