Orthodox Tewahedo Mezmur

@firstorthodoxmezemurchannel


Orthodox Tewahedo Mezmur

29 Apr, 10:08


እንኳን አደረሳችሁ
መልካም ጸሎትወስግደት

Orthodox Tewahedo Mezmur

06 Jan, 22:53


ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: 

የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣ የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣ ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ? የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? 

ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ? ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::

ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ

Orthodox Tewahedo Mezmur

06 Jan, 22:19


ቦሌ መድሃንያለም ::

Orthodox Tewahedo Mezmur

19 Apr, 07:37


https://youtu.be/pzR8_Ynyfic

Orthodox Tewahedo Mezmur

17 Apr, 19:29


መልክአ ሕማማት
በ pdf እንሆ ብለናል፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
ለሌሎች ሼር ማድረግዎን አይርሱ
https://t.me/firstorthodoxmezemurchannel

Orthodox Tewahedo Mezmur

17 Apr, 19:29


#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡
በሰሙነ ሕማማት የሚባሉትን በአጭሩ ስንቃኛቸው፡፡
(#ለዐርቡ_ጸሎት_እንደ_ዘማች_ስለሚያገለግል) ዐርብ ከምንለቀው የዐርቡ ጸሎት ጋራ አብረን የምንጠቀምበት ስለሆነ በቃል ጭምር አጥኑት፡፡
/ይህን ጽሑድ በአድካሚ ሁኔታ እንደ ንብ ቀስመንና ሰብስበን አዘጋጅተንላችኋል፤ ላልደሰረሰው አዳርሱ፤ ማተሚያ ቤት ያላችሁ አትማችሁ ስጡ፡፡/
፠የሰሙነ ሕማማት ጸሎት የሚደረገው በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት መሠረትነት 7ት ጊዜ ነው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ7ቱ ጊዜያት ከፋፍሎ የደረሰው መልክአ ሕማማትም አብሮ በዜማ ይደርሳል፡፡ (መልክአ ሕማማትን ለብቻው አዘጋጅተን ለጥፈንላችኋል)
#የጸሎቱ_አደራረስ_ሥርዐትም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፤
፠ደወልና ቃጭል ይመታል፤
፠ጸሎታት(ሙሉ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት)ና (የኦሪትና የነቢያት) ምንባባት ይደርሳል፤
፠የተአምር መቅድምና ምንባብ ይነበባል፤ የተአምራት መርገፍ በዜማ ይባላል፡፡
፠የወንጌል አቡን በቅብብሎሽ ይደርሳል፤
፠ምስባክ ይሰበካል ፥ ወንጌል ይነበባል፡፡
#1ኛ_ስግደት፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ›› እያለ ቃጭል ሲያሰማ 22ት ጊዜ ‹‹እግዚኦ ተሣሃለነ›› እየተባለ ይሰገዳል፡፡
#2ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለከ ኀይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን በቅብብሎሽ 6ት ፥ 6ት ጊዜ (በድምሩ 12)፤ 7ኛውን በኅብረት እየተሰገደ ይባላል፡፡
#3ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለአምላክ ይደሉ›› የሚለውን 1ኛውን ዙር በቅብሎሽ፤ 2ኛውን ዙር እያስተዛዘሉ፤ ከስግደት ጋራ ይባላል፡፡
#4ኛ_ስግደት፤ ‹‹ክርስቶስ አምላክነ…›› የሚለውን በመሪና ‹‹ንሰብሖ ..›› ወናልዕል ስሞ የሚለውን በቅብብሎሽ ብለው በዚያው ቀጥለው፤ ‹‹ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን›› የሚለውን በመሪ 21 ጊዜ፤ በተመሪ 20 ጊዜ (በድምሩ 41 ጊዜ) እየተሰገደ ይደርሳል፡፡
፠የየሰዓቱን (የሌሊት፣ የነግህ፣ የጠዋት 3 ሰዐት፣ የቀትር/6 ሰዐት/፣ የተሰዐት/9ኝ ሰዐት/፣ የሰርክ /11 ሰዐት/፣ የንዋም) መልክአ ሕማማት በዜማ ይደርሳል፡፡
፠ካህኑ ቡራኬ ሰጥቶ፤ ዲያቆኑ ደግሞ ‹‹ሑር በሰላም›› ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡

Orthodox Tewahedo Mezmur

15 Jan, 14:30


+እንዘ ሰለስቱ አሃዱ +

ግጥምና ዜማ :-ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በዘማሪ:-ሊቀዲያቆን ወንደሰን በላይ

+እንዘ ሠለስቱ+

ዓለምን በጥበብ ለፈጠረ ጌታ
ዘወትር እናቅርብ የክብር ሰላምታ
መላእክት በፍርሃት ለሚያመሰግኑት
ለሥላሴ እናቅርብ አኮቴት ስብሐት

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

በሃሳቡ ብቻ ዓለምን ለሠራ
በአምላካዊ ቃሉ ብርሃንን ላበራ
ሰውን በምሳሌው በአርኣያው ፈጥሮ
ከአፈር አበጀው ከሁሉ አክብሮ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

የሰው ልጅ ሲበድል አምላክ ልሁን ብሎ
የሰይጣንን ምክር አምኖ ተቀብሎ
አዳም አዳም ብሎ ፍለጋ ለወጣ
ለይቅር ባይ ጌታ ምስጋናን እናምጣ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ወደ ዓለም ልኮ አብ አንድ ልጁን
ወልድም በፈቃዱ መጣ ሰው ሊሆን
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተጸንሶ ተወልዶ
አክሊል አቀዳጀን በመስቀል ተዋርዶ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

እንዴት ላመስግንህ የቅዱሳን አምላክ
በልቤ ጉልበትም ለአንተ ልንበርከክ
ዓይኔን ከእጄ ጋር ወደ ላይ አንሥቼ
እዘምርልሃለሁ እንደ አባቶቼ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ዝማሬ : ሊቀ ዲያቆናት ወንድወሰን በላይ
ግጥምና ዜማ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Orthodox Tewahedo Mezmur

06 Sep, 09:31


+++ ይግባኝ! +++

አንድ ሰው ለብዙ ዘመናት አብሮት በፍቅር ይኖር የነበረ ወዳጁን በቅንዓት ተነሳስቶ ይገድለዋል፡፡ በዚህም የወንጀል ሥራው ተከስሶ የፍርድ ብይን ያገኝ ዘንድ ሰዎች ከችሎት ፊት አቆሙት፡፡ ዳኛውም ወንጀለኛው ለፈጸመው የጭካኔና ሰብአዊነት የጎደለው ክፉ ተግባር በሕጉ መሠረት የሚገባውን የዕድሜ ልክ እስራት ወሰኑበት፡፡ወንጀላኛውም በተሰጠው ፍርድ ፍትሐዊነት ላይ እንዳላመነበት እና ለፍርዱ ማቅለያ የሚሆን የይግባኝ ጥያቄን ማቅረብ እንደሚፈልግ በእጁ እየጠቀሰ ዳኛውን ተለማመነ፡፡

በዚህ ጊዜ ዳኛው ምን ዓይነት ይግባኝ እንደሚያቀርብ ለመስማት የጓጉ መሆናቸውን በሚያሳብቅ መልኩ ቸኩለው እድሉን ሰጡት፡፡

ወንጀለኛ፡-ክቡር ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትልኝ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፡፡በርግጥ ይህን ሰው መግደሌን አልካድኩም፣ ነገር ግን እርሱን ለመግደል የፈጀብኝ እኮ አፍታ ነች እንደው ቢበዛ ዐሥር ደቂቃ ቢሆን ነው፡፡ ታዲያ እንዴት በዚህች አጭር ጊዜ ላጠፋሁት ጥፋት ዕድሜ ልክ ይፈረድብኛል? በማለት ጥያቄውን አቀረበ፡፡

ዳኛው ምን ብለው የሚመልሱለት ይመስላችኋል? መቼም ወንጀሉን ለመፈጸም ከፈጀበት ጊዜ ጋር ተነጻጽሮ ፍርዱ ሊቀልለት ይችላል የሚል የየዋሕ ሰው ግምት እንደማይኖራችሁ አልጠራጠርም፡፡ በፍርዱ ሂደት የሚታየው ወንጀሉን ሲፈጽም የወሰደበት የጊዜ መጠን ሳይሆን በዚያች ሰዓት የፈጸማት የወንጀሏ ክብደት ናት፡፡

ውድ ምዕመናን! አሁን እኛ የፍርድ ቤት ዘገባ ምን ይጠቅመናል ትሉ ይሆናል? ከዚህ በኋላ ግን የምንነጋገረው ፍትሕ ስለማይገኝባት ስለዚህች ምድር ፍርድ አይደለም፤ ስለ ሰማያዊው ፍርድ ነው እንጂ። ስለ ሥጋዊው የዳኝነትም ሥርዓት አይደለም፤ ስለመንፈሳዊው ፍርድ ነው እንጂ፡፡ ብዙ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ዘላለማዊነት (eternal punishment) ባሰቡ ቁጥር ‹የሰው ልጅ በዚህች ምድር የሚኖረው የዕድሜ ልክ ስልሳ እና ሰባ ቢበዛም ሰማንያ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ የዕድሜ ወሰን ውስጥ ለተሠራ ኃጢአት እንዴት እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍርድን ይፈርዳል?› የሚል ጥያቄ በኅሊናቸው ይላወስባቸዋል፡፡

አንዳንዶቹም ለተገፉ ጠበቃ የሚሆን የእውነት ፈራጅ እግዚአብሔርን ፍርዱ ኢ-ፍትሐዊ (unfair judgment) ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ምንም ስለ ‹ዘላለማዊ ሽልማቱ› (eternal reward) ‹ለምን ዘላለማዊ ሆነ?› የሚል ጥያቄን አለማቅረባቸው ትዝብት ውስጥ የሚጥላቸው ቢሆንም እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ግን ከላይ ባለው አጭር ምሳሌ መልሳቸውን ያገኛሉ፡፡

አስተውሉ! ለወንጀለኛ መቼም ፍርድ እንደሚገባው ማንም የሚያምንበት ጉዳይ ነው፡፡ ወንጀለኛ ከወንጀል እስካልጸዳ ድረስ ፍርድ ከእርሱ ጋር እንደ ጥላ ትከተለዋለች፡፡ ቅጣትንም እንደ አክሊል በራሱ ላይ ደፍቶ ይመላለሳል፡፡ ለኃጢአተኛም እንዲሁ ነው፡፡ ራሱን በንስሓ መርምሮ ፣ወድቆ ተነሥቶ ፣በሥጋው በደሙ(ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል) አምላኩን እስካልታረቀ ድረስ ሁል ጊዜም ኃጢአተኛ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ኀዘኑን እጥፍ የሚያደርገው ያ ኃጢአተኛ በዚህ አቋሙ እያለ በሞት ከተወሰደ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው የሚድንበትን መንፈሳዊ ተግባር ማከናወን የሚችለው በምድር በሕይወተ ሥጋ እስካለ ድረስ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከራሷ ከክርስቶስ ከታነጸችበት የሐዋርያት ትምህርትም አላገኘችውምና ሰው ከሞተ በኋላ በሰማይ የሚሰግድበት ፣መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያደራጅበትና ኃጢአቱን የሚያስወግድበት ሥፍራ አለ ብላ አታምንም፡፡ ‹እም ድኅረ ሞቱ ለሰብእ አልቦቱ ንስሓ›/ ‹ለሰው ከሞቱ በኋላ ንስሓ የለውም› የሚለውን የአበው ቃል መመሪያዋ ታደርጋለች እንጂ፡፡

ስለዚህም በዚህ መልኩ የሞተ ሰው ኃጢአተኝነቱ ለዘላለም ነውና ፍርዱም ለዘላለም በማይጠፋ በዲንና በሚቃጠል የእሳት ባሕር ይሆናል፡፡ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው፡፡(ራእይ 21፤8) ከእንግዲህስ ከነኃጢአታችን ብንሞት የምንድንበት መሥዋዕት የለምና፣ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ አምላክ በዓይነ ምሕረቱ እንዲመለከተን የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደተባሉት ወደ ተሾሙ ካህናት እንገስግስ። ንስሓ እንግባ፣ ቀኖናችንንም እንፈጽም። መጠየቅን በሚወድ በእርሱ ፊት ለፍርድ በቆምን ጊዜ መልስ የሚሆነንን የጽድቅን ጥሪት እናከማች!

‹አቤቱ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁንብን!›

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]

@dnabel

Orthodox Tewahedo Mezmur

21 Aug, 17:35


Channel photo updated