Ethiopian capital market

@ethiopian_stockmarket


🚨በየትኛውም ፋይናንሽያል ማርኬት ላይ ንብረቶችን መግዛትም ሆነ መሸጥ ገንዘባችሁን ሙሉ ለሙሉ እስከማጣት ድረስ የሚደርስ ከፍተኛ የሆነ ሪስክ እንዳለው ታሳቢ በማድረግ የ ራሳችሁን የሆነ ምርመራ(reserch) እንድታረጉ እናሳስባለን።
https://t.me/ethiopian_stockmarket
🗣 ለጓደኞችዎም👫 መረጃዎችን #share በማድረግ ይተባበሩን ።

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:20


ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር (Ethio Telecom S.c) 10% በመቶ ድርሻውን መሸጥ የሚያስችለውን ሥርዓት (Mini App) በቴሌብር ሱፐር አፕ መተግበሪያው ላይ አካቷል።

ዜጎች ይህንን ሼር ከመግዛታቸው አስቀድሞ ስለ አጠቃላይ የሼር ሽያጭ የቀረበ ዝርዝር መረጃ (prospectus) አንብበው መስማማታቸውን መግለጽ ይኖርባቸዋል።

ይህ ዶክመንት ምን ይላል ?

ዶክመንቱ ፥ የሼር መጠን ፤ መግዛት ስለሚቻለው የሼር ብዛት፤ ስለ አክሲዮን ማኅበሩ ዳራ፤ የሂሳብ ሪፖርት መረጃዎችን፤ ቀነ ገደቦችን፤ ስጋቶችን፤ ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሂደቶችን፤ የሼር አከፋፈል ሥርዓቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ነው።

ሂደቶቹ ምን ይመስላሉ ?

ዜጎች በ prospectus ዶክመንቱ እንዲሁም ውል እና ሁኔታዎች (Terms and conditions) ከተስማሙ በኃላ መግዛት የሚፈልጉትን የሼር መጠን በመምረጥ ያመለክታሉ።

የመኖሪያ አድራሻ ፣ መታወቂያ ፣ ፎቶ ፣ ስልክ ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎችን ከተሞላ በኋላ ሼር ለመግዛት ማመልከት ይቻላል። እነዚህን መረጃዎች ለማስተካከል እና ክፍያ ለመፈጸም 48 ሰዓት ተሰጥቷል።

ሼር ለመግዛት ካመለከቱ በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም የክፍያ ሂደቱን እንዲሁም ያስገቡት ዝርዝር መረጃ የማጣራት ሂደት የሚያካሂድ ሲሆን ሂደቱን ካለፉ የተሳካ ማመልከቻ ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ። ሂደቱን ካላለፉ መሰረዞን የሚገልጽ መልዕክት ይደርሶታል።

(የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ እንዲሁም ፎቶ ሲያነሱት በሚታይ መልኩ እንዲሆን ይመከራል)

ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው በላይ ግዢ ከተፈጸመ ምን ይደረጋል ?

መሸጥ ከሚታሰበው በታች ሼር ከተሸጠ ሼር ለመግዛት ያመለከቱ በሙሉ የጠየቁትን የሼር መጠን የሚያገኙ ይሆናል።

ሆኖም የሼር ግዢ ጥያቄው ከተቀመጠው በላይ ከሆነ በprospectus ዶክመንቱ መሰረት የአክሲዮን ድልድል (Allotment of Shares) ይካሄዳል።

ይህም ሼር መሸጥ ከሚያበቃበት ታኅሣሥ 25 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል።

ይህ ድልድል በተመጣጣኝ ድርሻ ስሌት (Pro-rata Algorithm) የሚካሄድ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ነው። ይህም እያንዳንዱ አመልካች ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲደርሰው የሚያስችል ነው።

ለምሳሌ ፦  አንድ ሰው 100 ሼር ግዢ ለመፈጸም ጥያቄ አቀረበ። የተመጣጣኝ ድርሻ ስሌቱ (Pro-rata Algorithm) ሁሉም 70% እንዲደርሳቸው ቢወስን 100 ሼር ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበው ሰው የሚደርሰው 70 ሼር ይሆናል ማለት ነው።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ድልድሉ ጥር 23/2017 ዓ.ም በይፋ ለህዝብ በይፋ ይገለጻል።

ተመላሽ ክፍያ በተመለከተ ?

አመልካቾች ድልድል ከተደረገ በኋላ የደረሳቸው የሼር መጠን ያክል ክፍያ ተቆርጦለት ቀሪው ገንዘብ ከአገልግሎት ክፍያው ጋር ተደምሮ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

ገንዘቡ ድልድሉ ይፋ በሆነ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል። ዜጎች ሼር ለመግዛት ካመለከቱ እና ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ድልድሉን አለመቀበል አይችሉም።

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር 10% ድርሻ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሽያጭ የሚደረግበት ይሆናል። በተጨማሪም ዜጎች ለራሳቸው እና ህጋዊ ውክልና ላላቸው ዜጋ ግዢውን መፈጸም ይችላሉ።

ከዚህ የሼር ሽያጭ ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝ ሲሆን። ከአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 450 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል። መንግሥት ሙሉ ለሙሉ የቀረበው ሼር ተሸጦ ካለቀ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ብቻ 67.5 ሚሊዮን ብር ያገኛል።

አክሲዮን ማኅበሩ፥ በኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ገበያ ዝርዝር ውስጥ ለመካተት (Listing) የሚያስችለውን ዝግጅት የሼር ሽያጩ ካበቃ በ12 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን በዶክመንቱ ተገልጿል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:19


📣ቴሌብር ላይ ተካቷል ገብታቹ ማየት ትችላላቹ!

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


አንድ ሰው ከኢትዮ ቴሌኮም የገዛውን አክሲዮን ድርሻ ማዘዋወር፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ቢፈልግ ይችላል ወይ ?

አትዮ ቴሌኮም አሁን የሚጀመረው የአክሲዮን ሺያጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህ ምዕራፍ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ብቻ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።

ዜጎች ድርሻቸውን ማዘዋወር ፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም የሚችሉት ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ምዕራፍ ብሎ ባስቀመጠው ሲሆን ይህም ገና በሂደት ላይ እንዳለ ተጠቅሷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌኮም በ " listing " ሂደት ላይ እንደሚገኝ እና ይህም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የጠቀሱ ሲሆን ይፋዊ ቀን ግን አልተቆረጠለትም።

የሁለተኛው ዙር አክሲዮን ሽያጭ ሲጀመር ደግሞ ዜጎች ድርሻ ማዘዋወር ፣ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ያስችላቸዋል።

እንዴት ነው አክሲዮን የሚገዛው ?

በቴሌብር ላይ ነው መግዛት የሚቻለው። ቴሌብር ላይ ሲገቡ አክሲዎን ለመግዛት የሚል አማራጭ ይገናኛል (ልክ ላውንች ሲደረግ) በዛ አማካኝነት ነው መግዛት የሚቻለው። በዛ ዝርዝር መረጃ ይገኛል፤ የደብንበኝነት ውልን ስለሚኖር አንብቦ መቀጠል ይችላል ከተስማሙ።

(እስካሁን ድረስ ቴሌብር ላይ ይህ የአክሲዎችን ሽያጭ አማራጭ አልመጣም ልክ ሲመጣ እናሳውቃችኃለን)

ፎርሙን በ48 ሰዓት ውስጥ ማስተካከል  ይቻላል ፤ በተመሳሳይ ክፍያም በ48 ሰዓት ውስጥ መከፈል አለበት። ከ48 ሰዓት በኃላ ፎርሙን ማስተካከል አይቻልም።

ፎርሙን መጀመሪያ በመደበኛ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት መሙላት የሚቻል ሲሆን መጨረሻ ላይ የሼር ባለቤት ለመሆን የናሽናል አይዲ (ፋይዳ) ያስፈልጋል።

ሼር ገዢ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ለሽያጭ ከቀረበው ሼር በላይ ከመጣ ከዛ ውስጥ እነማን የሼሩ ባለቤት ይሆናሉ የሚለውን ለመለየት የሚያስችል አሰራር ተቀምጧል። (በቀጣይ በዚህ ላይ መረጃ እናቀርባለን)

➡️ ሼር መግዛት ማመልከይ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና እዚሁ ሀገር ውስጥ በአካል ያለ ነው።

2016 ዓ/ም በወጣ የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ የካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

በመጀመሪያ ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ደግሞ 100 ሚሊዮን ሼር ነው። የአንድ ሼር ዋጋም 300 ብር ነው። ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል። ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።
-tikvah

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


$2.6 billion usd valuation

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


📣- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


💠A prospectus is a written document that provides information about a security offering to potential investors:

Purpose
A prospectus is a primary sales tool for companies that issue securities, such as stocks, bonds, or mutual funds. It's a disclosure document that outlines the financial risks and guarantees for potential investors.

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


🔻Ethiotelecom prospectus document

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:18


📣- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  🔹 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

💠 ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 🔹999,900 ብር ይሆናል።

💠መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

💠የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

💠ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:14


⚠️የ ስቶክ/አክሲዮን ዋጋ እንዴት ካልኩሌት ማድረግ ይቻላል?
የ አንድ አክሲዮን ዋጋን ለማወቅ በቀላሉ Market capitalization ÷ number of shares በማድረግ ማወቅ እንችላለን
🔺MARKET CAPITALIZATION ማለት ተቋሙ / ድርጅቱ ያለው አሁናዊ ዋጋ ሲሆን
NUMBER OF SHARES ማለት ደግሞ ለገበያ የወጣው የ አክሲዮን ብዛት ማለት ነው ::
ስለዚህ
የ ኢትዮቴሌኮም MARKET CAP = approximately 119 billion ETB ሲሆን
🔺NUMBER OF SHARE ግን አይታወቅም ስለዚህ ሊሆን ይችላል ተብሎ በሚገመት ቁጥር ስናሰላ
HYPOTHETICALLY
📌IF 1% IS 10,000 SHARE
1% of 119 Billion = 1.19 billion
1.19 billion ÷ 10,000 = 119,000 ETB
📌IF 1% IS 100,000 SHARE
1% OF 119 BILLION = 1.19BILLION
1.19 BILLION ÷100,000 = 11900 ETB
📌 IF 1% IS 1,000,000 SHARE
1% OF 119 BILLION = 1.19BILLION
1.19 BILLION ÷ 1,000,000 = 1190 ETB
ይህ ለ ምሳሌ የተጠቀምኩበት ነው :: ዋጋው exactly እንደዚህ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል
ምክኒያቱም market evaluation(cap) እና NUMBER of share ሊለያይ ስለሚችል exact ቁጥሮቹን ስታገኙ የየትኛውንም ድርጅት አክሲዮን ለመግዛት ይህን አይነት አካሄድ መጠቀም ትችላላቹ::
መልካም ሰኞ❤️

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:13


📌ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:13


📌ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል ::

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:13


" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)

ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።

የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።

ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።

የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።

የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። #ሪፖርተርጋዜጣ

Ethiopian capital market

21 Jan, 00:09


📌Ethio Telecom to kick off Ethopian stock trading with 10% flotation next week
- Reuters

1,297

subscribers

139

photos

2

videos