🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

@abuhafsayimam


«رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ»
@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

22 Oct, 04:28


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። አላህ መቼም ሰው
{ فَٱعۡبُدُوا۟ مَا شِئۡتُم مِّن دُونِهِۦۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

22 Oct, 04:23


~አሁን ላይ የኛ ሁኔታ

=»@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

21 Oct, 15:08


🔖አዲስ ተከታታይ  ደርስ

📚የተከበረው ቁርኣን ትርጉም
📄ክፍል:- 001 (የሱረቱል ፋቲሓ ቃል በቃል ትርጉም)
(تفسير سورة الفاتحة )
🎙አቅራቢ:-ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም 
*የቴሌግራም ቻናሎች፡-
@SheikhMuhammedZain
@SheikhMuhammedZainadam @abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

21 Oct, 04:07


የቁርኣን አወራረድ
ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 2)
~
ቁርኣን መልእክቱም ቃላቱም የአላህ ንግግር ነው። መነሻው ከጂብሪል አይደለም። ከአላህ እንጂ። ከዚህ አንፃር ሲታይ ቁርኣን የጂብሪል ንግግር አይደለም። በቁርኣን ላይ የጂብሪል ሚና ከአላህ ተቀብሎ አማናውን ጠብቆ ለነብዩ ﷺ ማድረስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ }
"(ቁርኣንን) 'ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው' በላቸው።" [አነሕል፡ 102]

ቁርኣን ሁለት አይነት መውረድ አሉት።

[1]:- የመጀመሪያው መውረድ፦

* አወራረዱ፦ በጅምላ በአንድ ጊዜ ነው።
* ከየት ወዴት? :- 7ኛው ሰማይ ላይ ካለው ከለውሐል መሕፉዝ - ቅርቢቷ ሰማይ ላይ ወደሚገኘው በይተል ዒዘህ ወረደ።
* ጊዜው፦ በረመዷን ወር፣ በተባረከችዋ ሌሊት ነው፤ በለይለተል ቀድር።

ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ብሏል፦
{ شَهۡرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِیۤ أُنزِلَ فِیهِ ٱلۡقُرۡءَانُ }
"የረመዳን ወር ያ ቁርኣኑ የተወረደበት ነው፡፡" [አልበቀረህ፡ 185]
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَـٰهُ فِی لَیۡلَةࣲ مُّبَـٰرَكَةٍۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِینَ }
"እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው። እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና።" [አዱኻን፡ 3]
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَـٰهُ فِی لَیۡلَةِ ٱلۡقَدۡرِ }
"እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው።" [አልቀድር፡ 1]

[2]፦ ሁለተኛው መውረድ፦

* አወራረዱ፦ በተከፋፈለ ሁኔታ ነው።
* ከየት ወዴት? :- ከበይተል ዒዘህ ወደ ነብያችን ﷺ
* ጊዜው፦ በ23 ዓመታት ውስጥ

ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَقُرۡءَانࣰا فَرَقۡنَـٰهُ لِتَقۡرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكۡثࣲ وَنَزَّلۡنَـٰهُ تَنزِیلࣰا }
"ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው።" [አልኢስራእ፡ 106]

{ وَقَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَیۡهِ ٱلۡقُرۡءَانُ جُمۡلَةࣰ وَ ٰ⁠حِدَةࣰۚ كَذَ ٰ⁠لِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَۖ وَرَتَّلۡنَـٰهُ تَرۡتِیلࣰا }
"እነዚያ የካዱትም 'ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም' አሉ። እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን አወረድነው)። ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው።" [አልፉርቃን፡ 32]

በሁለቱም መውረድ ላይ ጂብሪል አለ። ከአላህ ተቀብሎ አማናውን ጠብቆ ለነብዩ ﷺ አድርሷል። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَإِنَّهُۥ لَتَنزِیلُ رَبِّ ٱلۡعَـٰلَمِینَ (192) نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِینُ (193) عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِینَ (194) بِلِسَانٍ عَرَبِیࣲّ مُّبِینࣲ (195) }
"እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው። እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤ ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡ ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ።" [አሹዐራእ፡ 192-195]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

21 Oct, 04:03


دعاء مهم للنساء 🌿
د. عبدالرزاق البدر

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

20 Oct, 17:48


አል -አማናOnline የገበያ ማህከል

~አልባሳት ከህፃን እስከ አዋቂ
~የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን
~የወጥ ቤት እቃዎችን
~ብርድልብሶችን፣ኮንፎርቶችን
~ፍራሽናትራስ፣የፍራሽና የትራስ ልብሶችን
~ የቤት አስቤዛዎችን፣
~ኪታቦችን፣ቁረአንኖችን ማንኛውም ለስጦታ የሚሆኑ እቃዎችን ጨምሮ እንልካለን።
~ከሀገር ውጭም ወደ ዱባይ ወደ ሳኡዲም እንልካለን።
~ማንኛውንም እቃ  ከውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ ተቀብለን ወደ ፈለጉበትም እንልክልዎታለን።
~አድራሻ ደሴ  በወሎ ውስጥ በማንኛውም ቦታ እንልካለን።
        ስልክ ☎️0985452588
                ☎️ 0967007992
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/Albuyue
እቃ መምረጫ
👇👇👇👇
https://t.me/albuyua

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

19 Oct, 18:17


=»እህቴ ሆይ ሰውነትሽ ላይ ባዕድ ነገር እየጨመርሽ እራስሽን አታርክሺ። አላህ በሰጠሽ ውበት ተብቃቂ።
ኦርጅናል ሰውነትሽ በአርቴፊሻል ነገርና ሰው ሰራሽ የሆነ ነገር እየጨመርሽ ሰውነትሽን አታበላሺ።

@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

19 Oct, 14:12


‹‹ሪዝቅ አይነቱ ብዙ ነው።››

[ርዚቅን ገንዘብ ብቻ አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው።]
||
~ኢስላምን፣ተውሂድን፣ኢማንን መታደል እርዚቅ ነው።
~ሱናን፣ስነምግባርን፣ሶብርን መታደል እርዚቅ ነው ።
~አፊያን፣ ሰላም፣ጤናን ፣መረጋጋትን መታደል እርዚቅ ነው።
~ጥሩ ትዳርን፣ልጅ መውለድን መታደል እርዚቅ ነው።
~እውቀትን፣እውቀት መፈለግን፣እውቀት መውደድን መታደል እርዚቅ ነው።
~የተውሂድ፣የሱና፣የኢስላም ወንድምና እህቶችን መታደል እርዚቅ ነው።

=»@AbuHafsaYimam
@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

19 Oct, 06:49


~ጠንቋዮችና መሰሎቻቸው

»»ሽይኽ ሀጂ መሀመድ ወሌ

=»@AbuHafsaYimam
@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

18 Oct, 18:31


[ أعظم المحرمات ... ]

قال الشيخ العلامة صالح الفوزان حفظه الله تعالى :
~ሽኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ:–

فأعظم المحرمات هو : الشرك بالله سبحانه .
~ከሃራሞች ሁሉ ሃራም #በአላህ  ማጋራት  ነው።
فإذا قيل لك : ما هو أعظم المحرمات؟
تقول : الشرك بالله عز وجل .
~ከሃራሞች ሁሉ ትልቁ ሀራም ምንድነው ተብለህ ከተጠየክ   #በአላህ  ማጋራት ነው ትላለህ።  
وإذا قيل لك : ما أعظم ما نهى الله عنه؟
تقول : الشرك بالله .
~አላህ ከከለከለው ትልቁ ነገር ምንድን ነው ተብለህ ከተጠየክ #በአላህ  ማጋራት  ነው ትላለህ።
وإذا قيل لك : ما أعظم المنكرات؟
تقول : الشرك بالله .
~ከሚጠላና (ከሙንከር) ነገር ሁሉ ትልቁ ሙንከር ምንድን ነው ተብለህ ከተጠዬክ #በአላህ  ማጋራት  ነው ትላለህ።
وإذا قيل لك : ما هو أكبر الكبائر؟
تقول : الشرك بالله .
~የትልልቆች ሁሉ ትልቅ ወንጀል ምንድን ነው ተብለህ ከተጠየክ  #በአላህ ማጋራትነውትላለህ ።
كما قال النبي صلى الله عليه وسلم :
《 أكبر الكبائر : الشرك بالله 》 .
~ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት:–
«ከትልልቆች ሁሉ ትልቁ ወንጀል በአላህ ማጋራት ነው።»
📚 إعانة المستفيد بشرح كتاب التوحيد .
📋 صفحة رقم ( ٣٢ ) .
__
=
»@AbuHafsaYimam
@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

18 Oct, 11:32


💫ብስራት  💫ብስራት  💫ብስራት

🫧[[ ታላቅ የደዕዋእና የኢጅቲማእ ፕሮግራም ]]🫧

🌃 በዉቢቱ'ና የሙስሊሙች መናገሻ በሆነቺው "በደቡብ ወሎ ዞን" አልብኮ ወረዳ ሶባና ጀብል በ013 ቀበሌ ሶባ ቢላል መስጅድ ታላቅ የደዕዋ እና የኮንፈረንስ ፕሮግራም ✈️

📢 ለመላው ደዕዋ ናፋቂ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ ጥቅምት -10/02/2017- በአይነቱ ለየት ያለ የደዕዋ ፣የኢጅቲማእ ፣የዚያራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እየጠበቃቹህ ይገኛል።

🔄የእለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ፦

❶ ሸይኽ ሙሀመድ መኪን -ሐፊዞሁሏህ - [ከደሴ]

     ❷ ኡስታዝ ሀሰን ኢድሪስ(አቡ ሙአዝ) -ሐፊዞሁሏህ -[ከሀርቡ]

          ❸ ሸይኽ ሙሀመድ ሰኢድ- ሐፊዘሁሏህ [ከደሴ]

❹ ሸይኽ ጀማል አዘ ሀቢ -ሐፊዞሁሏህ -[ከደሴ]

      ❺ ሸይኽ ኢማም ፔፕሲ -ሐፊዞሁሏህ -[ከደሴ]

           ❻ ሸይኽ አህመድ አወቀ -ሐፊዞሁሏህ - [ከደሴ]

❼ ሸይኽ ሀሰን ቃዲ -ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

❽. ሸይኽ ሙሀመድ አሚን-ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ) (ከደሴ) (ከደሴ)

❾. አቡ ሶላሁዲን ሸይኽ ሁሴን- ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

❿ ወንድም አቡ ሀሳን አሊይ -ሐፊዘሁሏህ (ከኮ/ቻ)

❶❶ ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሴን- ሐፊዘሁሏህ(ከደሴ)

❶❷ ወንድም አቡ ዑበይዳህ ሰኢድ-ሐፊዘሁሏህ(ከኬሚሴ)

❶❸ ወንድም አብደል መሊክ-ሐፊዘሁሏህ (ከኬሚሴ)

❶❹ ሸይኽ ኢስማኢል-ሀፊዘሁሏህ(ከኮ/ቻ)

❶❺ ሸይኽ ሙሀመድ ኡመር ''ጀሜ''-ሐፊዘሁሏህ (ከደሴ)

እና በሌሎችም ተናፋቂና ብርቅየ መሻኢኾች እና ኡስታዞች 'ሶባ'' ደምቃ እና ተውባ ትውላለች-ኢንሻ አሏህ- ስለሆነም የሶባ(የአሸዋው) እና   እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ብሎም ተወላጆችም ጭምር በየትም የምትገኙ የደዕዋ ናፋቂዎች  በሙሉ በክብር ተጋብዛችኋል።

🕌 አድራሻ ፦ አልብኮ ወረዳ ጦሳ ፈላናን ተሻግሮ በተለምዶ "አሸዋው " በመባል የሚጠራው ሰፈር "ቢላል መስጅድ" ወንዙን ተሻግሮ ከጁኒየር ትምርት ቤቱ አጠገብ።

አዘጋጅ = የሶባ ቢላል መስጅድ ጀመአ

በአካል መገኘት የማትችሉ ኔት ካለ -ኢንሻ አሏህ- በዚህ ቻናል ለማስተላለፍ እንሞክራለን!
ወይንም እሪከርድ ይለቀቃል
👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4305
https://t.me/Sobabilalmesjid/4305

የፕሮግራሙ ሰዓት፦ ጠዋት 3:00-4:00 ባለው ሰአት ይጀመራል

🚙እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል

መልዕክቱን ሸር እና ኮፒ አድርጉልን
ሸር ሸር ሸር

ይህ ቻናል ዳእዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል 013 የቴሌግራም ቻናል ነው። ይቀላቀሉ👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

18 Oct, 07:22


የሸይኽ ሙሐመድ ዘይን የነሕው ደርሶች !
~~
አልሙቀዲመቱል ኣጁሩሚያ
ሙልሐቱል ኢዕራብ
ከሽፋ ኒቃብ
አልፈዋኪሁል ጀንያ 1
አልፈዋኪሁል ጀንያ 2
አልፍየቱ ኢብኒ ማሊክ ከኢብኑ ዐቂል ሸርሕጋር

የሸይኽን የተጠናቀቁ ዱሩሶችን ለማግኘት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ :-
https://t.me/SheikhMuhammedZain

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

18 Oct, 04:18


“ቲላዋ”

=»@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

17 Oct, 18:31


«~አትፍሩ- ውለዱ»


↪️ኡስታዝ ሳዳት ከማል

=»@AbuHafsaYimam
=»@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

17 Oct, 06:58


~የምትጠላው ሰው ፈተናና መከራ አግኝቶት ስታይ  አላህ የተበቀለልህ አስመስለህ   የምትደሰተው ወንድሜ ሆይ ተጠንቀቅ !ነገም በኔ አለ ብለህ እሰብ።

~እሱ የደረሰበት መከራና ፈተና  የአላህ ውሳኔ ሆኖ ነው። በአላህ ውሳኔ አምኖ መቀበል የሱ ድርሻና ግዴታ ነው። ያንተ በሱ መደሰት ግን ምን የሚሉት ነው?

=»@AbuHafsaYimam

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

17 Oct, 05:20


ወዳጄ ሆይ!
አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ .... እያልክ ሰዎችን በጃሂሊያ መስፈሪያ አትስፈር ! ከየትኛውም ዘር ብትሆንም ከማንም የተሻልክ አይደለም! ያነስክም አትሆንም! ቁልቁል የምትወርደው ፈጣሪን ማመፅ በጀመርክ ግዜ ነው! ሰዎችን በዘር ሚዛን መመዘን የጀመርክ ወቅት ነው! ከፍ የምትልው ፣ የባለይነትን የምትጎናፀፈው የነብዩን ሱና አጥብቀህ በያዝክ ግዜ ነው! መስፈሪያህ ተውሒድና ሱና ሆኖ ባነጋ ግዜ ነው!!

ወንድሜ ፣ ሰው ፖለቲካን ነጋ ጠባ ሲናገረውና ሲፅፈው አንተ ግን ተውሒድን ፣ ዲንህን ስበክ ።
የማንነትና የድንበር ጥያቄ በማለት ዘረኝነትን ቀንና ሌት ሲሟገትለት አንተ ይህንን የገማ የስብከት መንደር ፊት ንሳውና ወደ ነብዩ صلى الله عليه وسلم
ሱና ተጠጋ ፣ ስለሱም ተሟገት! ! ቀብርህ ላይ የሚጠቅምህ ይሄው ነው ወዳጄ! ! ነገ አላህ ፊት እርቃህን ስትቆም የፈጣሪህን እዝነት ለማግኘት ሰበብ የሚሆንህ ተውሒድና ሱና ነው ወንድሜ ! ሰንቀው !!

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

17 Oct, 04:16


- ياسر الدوسري
#بدون_مايك

🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]

16 Oct, 19:07


~የሰዎችን ችግር ሳታረጋግጥ ከሰው በሰማኽው ብቻ አትጥላ። ስለኔ ከኔ ውጭ ከሆነ ሰው አትስማ።ስለኔ ከኔው ስማ።ከኔው አረጋግጥ ተብሏል።

~ዛሬ ዛሬ ሳናረጋግጥ፣ሳናጣራ ከሰዎ ሲወራ ስለሰማን ብቻ ፣በሀሜት የመጣን ብቻ በመስማት ሰውን መጥላትና መጠላላት ውስጣችን ላይ ሰፍኗል።

=»@AbuHafsaYimam
=»@AbuHafsaYimam

2,098

subscribers

415

photos

95

videos